በአምስት ወራቸው የተወለዱት መንትዮች በጊነስ መዝገብ ሰፈሩ
March 8, 2023 – BBC Amharic 7 መጋቢት 2023 በ22 ሳምንት (አምስት ወር ከሳምንት) እርግዝና የተወለዱት ካናዳዊ ወንድምና እህት በጊነስ የድንቃ ድንቅ መዝገብ ሰፈሩ። ጨቅላዎቹ የዓለማችን ያለጊዜያቸው የተወለዱ መንትዮች የሚል ስያሜም አግኝተዋል። አዲያህ እና አድሪያል በተጸነሱ በ126ኛ ቀናቸው ነው የተወለዱት። ጨቅላዎቹ ከ22 ሳምንታቸው በአንድ ሰዓት ባነሰ ጊዜ ቢወለዱ ኖሮ በህይወት የመወለድ ተስፋቸው የመነመነ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ሆስፒታሉም […]
በአፍሪቃ ቀንድ ለሚደጋገመው ድርቅ መፍትሄ
March 8, 2023 – DW Amharic በአፍሪቃው ቀንድ አካባቢ የሚደጋገመው ድርቅ ባለፉት ሦስት ዓመታት ደግሞ ተጠናክሮ በሰውም በእንስሳትም ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ቀጥሏል። ቆላማውን አካባቢ በተቀናጀ ስልት በድርቅ ተደጋግሞ ከመጎዳት መከላከል እንደሚቻል የደን እና የተፈጥሮ አካባቢ ተመራማሪዎች ይናገራሉ።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
ጀርመን ያቀደችው የፍልሰት ሕግ ማሻሻያ
March 8, 2023 – DW Amharic ጀርመን በተለይም ከፍተኛ ክህሎት ያላቸውን የውጭ ዜጎች ለማስገባት ሕጎችን ብታወጣም መስፈርቶቹ የሂደቱ ውስብስብነትና አዝጋሚነት ብዙዎችን ሊስብ አልቻለም። ሚኒስትር ኃይል በዚህ ረገድ ችግሮች መኖራቸውን አምነው የትምህርት ማስረጃዎች እውቅና አሰጣጥ ፣ የቪዛ መጓተትና የመሳሰሉት ከተስተካከሉ ሁሉም ወገን ተጠቃሚ ይሆናል የሚል ተስፋ ሰጥተዋል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
በጉጂ ዞን የቀጠለው የአዲስ አስተዳደራዊ ዞን ምስረታ ተቃውሞ
March 8, 2023 – DW Amharic ይህ የህዝብ ቁጣ መንገድ በመዝጋት ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን አስተጓጉሏል፡፡ በተነሳው አመጽም እስካሁን ከቦሬ ሦስት ከአዶላ አንድ ሰው ህይወታቸው አልፈዋል፡፡… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
የተባበሩት መንግሥታት የአዳጊ አገሮች ስብሰባ
March 8, 2023 – DW Amharic «ቃል ሁልግዜም ይገባል ለምሳሌ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት ወይም ድህነትን ለማስወገድ፣ ክትባቶችን ለማምረት ሊሆን ይችላል። ግን ተግባራዊ ለማደረግ ቁርጠኘነት አይታይም።»… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
የደቡብ ኦሞ ዞን ድርቅ ተጋላጮች በቂ የሰብዓዊ እርዳታ እንዳልቀረበላቸው ተናገሩ
March 8, 2023 ደቡብ ኦሞ ዞን ለድርቅ የተጋለጡ አርብቶ አደሮች በቂ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዳላገኙ በደቡብ ክልል ምክር ቤት የሐመር እና የኛጋቶም ብሄረሰብ ተወካዮች ገለፁ። በዞኑ በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የክልሉና ፌዴራል መንግሥታት እንዲሁም አጋር ድርጅቶች አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ተወካዮቹ ጥሪ አሰምተዋል። የሐመርና ኛንጋቶም ወረዳን ጨምሮ በዞኑ ከ330 ሺህ በላይ ዜጎች አስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ፈላጊዎች መሆናቸው […]
ከደቡብ ሱዳን የሚነሱ ታጣቂዎች በኢትዮጵያውያን ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሱ ነው
March 8, 2023 ከደቡብ ሱዳን የሚነሱ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግረው በመግባት “በተደጋጋሚ ጥቃት ያደርሳሉ” ሲል የክልሉ መንግሥት አስታወቀ። ጥቃቶቹን ለማስቆም በደቡብ ሱዳንና ጋምቤላ ክልል ድንበር አካበቢ ሰላም ዙሪያ በጋራ ለመሥራት ሥምምነት ላይ መደረሱንም የክልሉ መንግሥት አመልክቷል። በተያያዘ ርዕስ ታጣቂዎቹ ባለፈው ሳምንት ውስጥ በተመሳሳይ የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግረው ገብተው በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ውስጥ ባደረሱት […]
በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ የሚገኙ ሕፃናት የዓድዋ በዓል አከባበር
March 8, 2023 ዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የሚገኙ ህፃናት 127ኛ ዓመት የዓድዋ ድል በዓልን ቅዳሜ ምሽት ቨርጂኒያ ውስጥ በተከናወነ ልዩ ዝግጅት አክብረዋል። ከኢትዮጵያ ውጪ የተወለዱና በልጅነታቸው ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የመጡ ህፃናትና አዳጊዎች የመጡበትን ቋንቋ፣ ባህል፣ ልማድ እና መከባበር አውቀው እንዲያድጉ ለማገዝ የተቋቋመ አቡጊዳ የቋንቋና የባሕል ተቋም የመርኃ ግብሩ አሰናጅ ነበር። ከአራት ዓመት በፊት ዩናይትድ ስቴትስ ቨርጂንያ […]
በሲዳማና ኦሮሚያ አዋሳኝ ቀበሌዎች ግጭት ተቀስቅሶ 12 ሰዎች ተገደሉ
March 8, 2023 በሲዳማና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ ቀበሌዎች ሰሞኑን ግጭት ተቀስቅሶ 12 ሰዎች መገደላቸውን ከሟቾች ቤተሰቦች ሰምቻለሁ ሲል ቪኦኤ ዘግቧል። በኦሮሚያና ሲዳማ ክልል አዋሳኝ በሚገኙ ጉቦሄማና ቦጨሣ በተባሉ አከባቢዎች በተከሰተ ግጭት 12 ሰዎች መገደላቸውን የተጎጂ ቤተሰቦች መሆናቸውን የገለፁ ነዋሪዎች ተናገሩ። በጉዳዩ ላይ ከአካባቢው ባለሥልጣናት መረጃን ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም። በሌላ በኩል የጭሪ ወረዳ ጤና […]
በኢትዮጵያ ባሉ ነባራዊ ወቅታዊ ሁኔታዎች ሳቢያ አለም አቀፍ የቡና ጥራት ውድድርና ጨረታ ታገደ
March 8, 2023 – Konjit Sitotaw Ethiopia Cup of Excellence Program Suspended for 2023 “አሊያንስ ፎር ኮፊ ኤክሰለንስ” የተሰኘው ዓለማቀፍ ኩባንያ ኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን የዘንድሮው የቡና ጥራት ውድድርና ጨረታ እንደማይካሄድ እንደገለጠለት አስታውቋል። የዘንድሮው ውድድርና ጨረታ የማይካሄደው፣ በኢትዮጵያ ባሉ “ነባራዊ ወቅታዊ ሁኔታዎች” ሳቢያ እንደሆነ ኩባንያው ገልጧል። ኩባንያው ባለፉት ሦስት ዓመታት ባካሄዳቸው የቡና ጥራት ውድድሮችና ጨረታዎች ለአርሶ አደሮች […]