ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ በፈረንሳይ ጋዜጣ (ታደለ ጥበቡ)

02/01/2019 ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ በፈረንሳይ ጋዜጣ ታደለ ጥበቡታህሳስ 1867 ዓ.ም ” La Lune “የተባለ የፈረንሳይ ጋዜጣ “THÉODOROS II, ROI D’Abyssinie ” በሚል ርዕስ የፊት ሽፋን ስለ ዳግማዊ ቴዎድሮስ እንዲህ ጽፏል!!! ዳግማዊ ቴዎድሮስ በአቢሲኒያ ግዛት 14 አውራጃዎች 5 ሚሊዮን ህዝብ ያስተዳድራል።የ50 አመቱ ቴዎድሮስ ጦረኛ፣ሊቅ፣የማሰብ ልዕልናው ከፍ ያለ፣የሥነ-መለኮት እውቀት ያለው፣ደፋር፣አሸናፊ፣ተክለ ሠውነቱ ግርማ ሞገስ የታደለ እና የአባቶችን ወግ […]

“ትግራይ ተከባለች!!!” (በፍቃዱ ኃይሉ)

02/01/2019 “ትግራይ ተከባለች!!!” በፍቃዱ ኃይሉ አገር ሲንቀሳቀስ በዚህ “ትግራይ ተከባለች፣ ልንጠቃ ነው” ፕሮፓጋንዳ የተነሳሳው ሕዝብ መንገድ ዘግቶ ሠራዊቱን አላሳልፍም እስከማለት ደርሷል። (ተቃዋሚዎቹን ባለመታገስ የሚታወቀው የትግራይ መንግሥትም ወጣቶቹን ባለማስቆሙ፣ ምንም እንኳን የኋላ ኋላ ለማስተባበል ቢሞክርም ሕወሓት ራሱ ያስተባበረው የመንገድ መዝጋት እንደሆነ ተገምቷል።) በተመሳሳይ፣ በታኅሣሥ ወር 2011 የሱዳኑ መሪ ከኢትዮጵያ መሪ ጋር ጅማ ላይ በተገናኙበት ወቅት ላይ […]

” ህግ መከበር አለበት ሲባል ለአባገዳም ይሰራል!!!” (ቦጋለ ሰለሞን ዘውጋ)

02/01/20190 ” ህግ መከበር አለበት ሲባል ለአባገዳም ይሰራል!!!”     ቦጋለ ሰለሞን  ዘውጋ     ሰሞኑን  በመንግስት እና በኦነግ መካከል በተደረገው የሰላም ስምምነት ዙሪያ አንዳንድ ነጥቦች ማንሳት አስፈላጊ ነው። በስምምነቱ መሰረት መንግስት የራሱን ሐሳብ ያቀረበ ሲሆን ፣ ኦነግም የሚደራደርበትን ጉዳይ አቅርቦአል። ከዚህ በተጨማሪ በአደራዳሪነት የተገኙት የአባገዳ ሽማግሌዎች ከሽምግልናው ባለፈ ውሳኔ እንዳስተላለፉ እየተነገረ ነው!!    ከአባገዳ ውሳኔዎች እንዱ […]

አዲስ አበባ ከኦ.ዴ.ፓ ሞግዚትነት – ከታከለ ኡማ መስተዳድር መላቀቅ አለባት !!! (አብነት እንግዳ)

02/01/2019 አዲስ አበባ ከኦ.ዴ.ፓ ሞግዚትነት – ከታከለ ኡማ መስተዳድር መላቀቅ አለባት  !!!  አብነት እንግዳ …ታከለ፣ በኦሮምኛ “እንኳን በፊንፊኔ ዛሬ ተገናኘን። ለፊንፊኔ ተብሎ ብዙ ሰው ታስሯል። ተሰቃይቷል። ከሃገር ተሰዷል። በአባቶቻችን ሃገር ቀና ብለን መሄድ  እየቻልን፤ እየፈለግን ከዩኒቨርሲቲ ተባረናል። ዋጋ ለፊንፊኔ ከፍለናል” ሲል አዲስ አበባን የኦሮሞ መሬት እንደነበረች፣ ተነጥቀው እንደነበረና አሁን ግን  በእጃቸው እንደወደቀች አይነት የ”ድል” ንግግር ነበር ያደረገው።—አንደኛ – […]

የሕዝብና ቤቶች ቆጠራን በተመለከተ ቅድመ ማስጠንቀቂያ! (ቹቹ አለባቸው)

02/01/2019 0 የሕዝብና ቤቶች ቆጠራን በተመለከተ ቅድመ ማስጠንቀቂያ! ቹቹ አለባቸው1. ሌላ አማራጭ ካለ ንገሩኝ!  አንዳንድ ወዳጆቸ አዴፓ እንዲህ ቢያደርግ፤እንዲህ ደግሞ ባያደርግ እያልኩ ምክር አዘል ሃሳብ ስሰጥ፤ አዴፓ አለ ወይ? በአዴፓ ተስፋ አለመቁረጥህ ይገርመናል! አዴፓን ለማጀገን ትሞክራለህ! ሹመት ፈልገሀል መሰል ! ወዘተ…የመሳሰሉትን ሃሳቦች በመሰንዘር፤አዴፓን እንድረሳው ይመክሩኛል፡፡ የእነዚህ ወንድም/ እህቶቸ ሃሳብ ይገባኛል፤ በአዴፓ ላይ ተስፋ በመቁረጣቸው ነው፡፡ […]

ቶ ” ባለትንቢቱ ንጉስ ቶዎድሮስ ማነው ?? ” (ሶሎሞን መቅደላ)

01/31/20190 ቶ ” ባለትንቢቱ ንጉስ ቶዎድሮስ ማነው ?? ”  ሶሎሞን መቅደላ  –  እነሆ  ቶ …!!!        ከቀደሙት ኢትዮጵያውያን አባቶች የጥበብ አሻራ አንዱ የሆነውን ፍካሬ ከዋክብትን መሰረት ያደረጉ አንዳንድ ግለሰቦች የቶዎድሮስን መወለድ በቀጥታ በዓለማችን ላይ ጥሩም ይሁን መጥፎ ነገር ሰርተው ካለፉ ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ከተወለዱበት ክስተት ጋር ያገናኙታል፡፡ የፍካሬ ከዋክብት ሊቃውንት በዓለማችን ታዋቂ የሆኑ ተጽእኖ […]

የዶክተር አቢይና የኢትዮጵያ ፅኑ ጠላቶች – ሁሉም ሊያውቀው የሚገባ! (ይኄይስ አእምሮ)

ሰላም ውድ አንባቢያን! ሀገራችንን ከከበቧት ውስብስብ ችግሮች አንጻር ብዙ ከሚጨነቁ ዜጎች መካከል አንዱ ነኝ፡፡ እንደለመደብን በዝምታ ተውጠን በአርምሞ የፈጣሪን ተዓምራዊ ሥራ በጉጉት የምንጠብቅ ብዙ ዜጎች ብንኖርም አንዳንዴ የሚያስጨንቁንን የምንተነፍስ አንጠፋምና ዝም ብዬ ዝም ከምል ከምታዘባቸው መጥፎ ነገሮች መካከል አንድ ሁለቱን ያህል አሁን ባጭሩ ልናገር ወደድኩ፡፡ አስቀድሜ ግን ዓመት ሊሞላው ከሦስት ያነሱ ወራት በቀሩት አዲሱ ለውጥ […]

ኢትዮጵያን ያያችሁ “ና ወዲህ” በሉኝ! አሁን የት ናት? ፟ – (ዳግማዊ ጉዱ ካሣ)

በሁሉም ቦታ ውጥረት ነግሦኣል፡፡ ሰላም ያለችው በአንደበትና በመንግሥት ሚዲያዎች ብቻ እንጂ በተግባር የለችም፡፡ ሀገር በከፍተኛ ፍጥነት እየፈራረሰች ባለችበት በአሁኑ ሁኔታ ሕዝቡም ፀጥ ረጭ ብሎ የመርከቢቱን መስመጥ በትግስት እየተጠባበቀ ይገኛል፡፡ በትብታብ የተያዝን ይመስል (ተይዘንም ሊሆን ይችላል) ሁላችንም ፈዘንና ደንግዘን እንገኛለን፡፡ ተመልከቱ – ስግብግብ ነጋዴዎች በጀሶና በሴጋቱራ እንጀራ ሆዳችንን እየቆዘሩ ላልታወቁ በሽታዎችም እየዳረጉን ሆስፒታሎችንና መቃብር ሥፍራዎችን እያጨናነቅን […]

ሞት የማይቀር የሁላችን እርስት ነው

ከመንግስቱ ሙሴ ፌስ ቡክ የተወሰደ ስም ያለው ስሙ ከመቃብር በላይ እንዳበበ ይኖራል የሌለው ስሙ በተነሳ ቁጥር ይረገማል። አቶ ዳዊት ዮሐንስን እልፈት በተመለከተ እዚህ በማህበራዊ ሚዲያ የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰጡ ተመለከትሁ። አንዳንዶችም ባህላዊውን ነፍስ ይማር እያሉ ያለፉም አየሁ። የሰው ልጅ እድሜው ይህችን ያክል መሆኗ በዚህ ሰው መርዶ የሚታይ ነው። ለዚህች አጭር እድሜ ግን ሰው የራሱን ክብር አጉድሎ፣ […]