“በመጨረሻ ሰዓት የምን መልቀቂያ ነው ? አብረን እንሞታታለን !!” (ዮናስ ሃጎስ)

26/12/2017 ትናንት EBC የምሽት ዜናዎቹ ላይ አቶ አባዱላ ገመደ የስራ መልቀቂያ ተሰጣቸው እየተባለ በተለይ በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው የሃሰት ወሬ ነው ሲል ነበር ። ከዚህ “ዜና” (ዜና ከተባለ) የሚከተሉትን ልብ ትላለህ ፦ አንደኛ የአቶ አባዱላ መልቀቂያ ማስገባት ስርዓቱን ምን ያህል እንዳሸበረውና ብርድ ብርድ እንዳለው ያሳበቀ “ዜና” ነው ! ሰውዬው ስርዓቱን ለመልቀቅ መጠየቃቸው ራሱ አስገራሚ ሆኖ ሳለ […]
አማርኛን እናዘምን! እናሰልጥን!

አማርኛን እናዘምን! እናሰልጥን! አማርኛ ከዘመናዊው አኗኗርና አስተሳሰብ በተለይም ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ጋር በብቃት አብሮ ሊራመድ አለመቻሉ በተለይ አሁን በዘመነ ‘ኢንተርኔት’ እጅግ አግጥጦ የወጣ ሃቅ ነው። አገሪቱም ለአማርኛ ቋንቋ የልማት እቅድ የላትም። የተያዘው የደመነፍስ ጉዞ የተቻለውን በአማርኛ የልተቻለውን በእንግሊዝኛ እያደባለቁ መሄድ ነው። የዚህ አካሄድ መድረሻው ለብዙዎቻችን የተሰወረ አይደለም። በሌላ በኩል በህሊና እንመራ የሚሉ ጥቂት ዜጎች ዘመናዊ አስተዳደር […]
የህወሃት ልምምጥ – ስልታዊ ግን ከተመዘዘው የለውጥ ሰይፍ ለማምለጥ

[ወንድወሰን ተክሉ-ጋዜጠኛ] **መነሻ- ህወሃት የፖለቲካ ማርሹን ለውጫለሁ ብላል። እንደ አባባሉ ከሆነ ምናልባትም ከባለ 5ፖለቲካዊ ማርሽ አነዳድ ወደ 3እና 4ፖለቲካዊ ማርሽ ላይ ለውጦ ለውጦ ሊሆን ይችላል እንጂ ሞተሩን አቀዝቅዞ ወደ ዜሮ ማርሽ ሊቀየር ቀርቶ ዝግ ወደሚለው ፍጥነት ቁጥር ሁለት ማርሽ እንዳላስገባ ይታወቃል። ህወሃት እየተናገረ ያለውን የመለማመጥና ብሎም ሰጥቶ የመቀበልን ፖለቲካዊ ለውጥ ማድረጉን እየገለጸ ያለው በሁለቱ የሀገሪቱና […]
“ኽርማን ኮኽን ስለዛሬ የኢትዮጵያ ሁኔታ”

አስተያየት ከዶ/ር ዳንኤል ተፈራ የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር፤ ኤመረተሰ። በአሜሪካን ድምፅ ሬድዮ ጋዜጠኛ፤ በአቶ ሰሎሞን አባተና በቀድሞው አምባሳደር፤ ሚስተር ኽርማን ኮኽን መካከል ከዚህ በላይ በተጠቀሰው አርእስት ላይ፤ በታህሳስ 22/ 2017፤ የተካሄደውን ቃለመጠይቅ በጥሞና አዳምጫለሁ። ሰለአምባሳደሩና ባነሷቸው ጉዳዮች ላያ አስተያዬትን ለመስጠት እሞክራለሁ። የአማባሳደር ኽርማን ኮኽንን ስም ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት፤ የዛሬ ሀያስድስት ዓመት ነው። የአሜሪካን፤ የጆርጅ ኤች ቡሽ አስተዳደርን […]
የሽግግር ጊዜ ሰነድ ጋጋታ -አንዱዓለም ተፈራ

December 25, 2017 እሁድ ታህሣሥ ፲ ፭ ቀ ፳ ፻ ፲ ዓመተ ምህረት ሁላችንም የትግሬዎች መንግሥት አይቀሬ መውደቂያው መቃረቡን እናምናለን። በዚህ ላይ ምንም ዓይነት ጥርጥርም ሆነ ብዥታ የለም። ከዚያ በኋላ የሚከተለውን፤ ከዚያ በፊትም፤ ይሄ እንዴት ሊከሰት እንደሚገባውና እንደሚችል፤ የአንድነት ግንዛቤ መኖሩን ግን እጠራጠራለሁ። ጥቂት ግለሰቦች የሽግግር ጊዜ ሰነድ ረቂቅ በማዘጋጀት፤ ለአንባቢዎች አቅርበዋል። አንዳንድ ድርጅቶችም የሚቀርቧቸውን […]
በአዲስ አበባ አብዛኞቹ አረጋውያን የምግብ እጥረት ይገጥማቸዋል

24 December 2017 ታደሰ ገብረማርያም በአዲስ አበባ ከተማ 74 ከመቶ የሚሆኑት አረጋውያን ለከፍተኛ፣ እንዲሁም 97 ከመቶ ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ መዳረሻ የምግብ እጥረት እንደሚገጥማቸው ተነገረ፡፡ ‹‹የመገናኛ ብዙኃን ትኩረት ለአረጋውያን›› በሚል ርዕስ ታኅሣሥ 12 ቀን 2010 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ጡረተኛና አረጋውያን ብሔራዊ ማኅበር ባካሄደው ዓውደ ጥናት ላይ እንደተመለከተው፣ ለምግብ እጥረቱ የቤተሰብና የማኅበረሰብ ድጋፍ አናሳ መሆን እንደምክንያት ተጠቅሷል፡፡ በጉዳዩ ላይ ጥናት […]
መረጋጋት ያልቻሉት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት

26 ዲሴምበር 2017 ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተማሪዎች መካከል የሚከሰቱ ግጭቶች የትምህርት መቋረጥን በተደጋጋሚ ከማስከተላቸው በተጨማሪ ተማሪዎች ተረጋግተው ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ ሥጋት ፈጥረዋል። በተለይም በተማሪዎች መካከል ማንነትን መሰረት አድርገው የሚነሱ ግጭቶችን ተከትሎ በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። የአካል ጉዳት ከመድረሱም በተጨማሪ ንብረትም ወድሟል። ይህ ክስተትም የመማር ማስተማር ሂደቱን […]
በዋሺንግተንዲሲ የዲሴምበር 17/ 2017 የተደረገ የሕዝባዊ ሥብሰባ ዘገባ

