መንግስት፤ አቶ አባዱላ በሃላፊነታቸው እንዲቀጥሉ ይፈልጋል

Sunday, 29 October 2017 00:00 Written by  አለማየሁ አንበሴ የባለሥልጣናት በገዛ ፍቃድ ከሥራ መልቀቅ መለመድ አለበት ተባለ አቶ በረከት ስምኦን፤ የመልቀቂያ ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቷል። የመንግስት ባለሥልጣናት በገዛ ፍቃዳቸው ከስራ መልቀቃቸው ዲሞክራሲዊ በመሆኑ መለመድ አለበት ያሉት ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ፤ በቅርቡ የስራ መልቀቂያ ጥያቄ ያስገቡት የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር አቶ በረከት ስምኦን፣ ጥያቄያቸው ተቀባይነት ማግኘቱን ጠቁመው፣ የአቶ አባዱላ […]

የኢሠማኮ ጠቅላይ ምክር ቤት እስከ ሥራ ማቆም አድማ የሚደርስ ዕርምጃ ለመውሰድ ወሰነ

29 October 2017 ዳዊት ታዬ የደመወዝ ማስተካከያ ያስፈልጋል ብሏል የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ጠቅላይ ምክር ቤት እንደ አዲስ ተረቅቆ የተዘጋጀውን የአሠሪና ሠራተኛ ረቂቅ አዋጅ ፈፅሞ እንደማይቀበለው፣ ረቂቁ እንዲሻሻል በተደጋጋሚ ያቀረበው ጥያቄ ምላሽ ካላገኘ የሠራተኛውን መብትና ጥቅም ለማስከበር በአገር አቀፍ ደረጃ እስከ ሥራ ማቆም አድማ የሚደርስ ዕርምጃ ለመውሰድ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ የአሠማኮ ጠቅላይ ምክር ቤት ይህን ውሳኔ […]

ሶስተኛውን መስቀለኛ መንገድ እንዴት እንሻገረው? ክፍተቱን ለመሙላት እንዳይረፍድብን..  – መስቀሉ አየለ

  October 28, 2017  አንጻራዊ በሆነ መልኩ ለግማሽ ምእተ አመት አገሪቱን አረጋግተው መግዛት የቻሉት ንጉስ ሃይለስላሴ ነበሩ። ገና ወደ ስልጣን መንበር ሲመጡ አገሪቱ የነበሩዋት የተቋማት ደረጃ እዚህ ግባ በማይባሉባትና የህዝቡም አስተሳሰብ ገና ፊውዳላዊ በነበረበት በዚያ የጨለማ ዘመን ደረጃቸውን የጠበቁ የአየር መንገድ፣ አለማቀፋዊ የሆነ የፍታብሔር እና የወንጀለኛ መቅጫ ድንጋጌዎችን ፣የመጀመሪያውን ህገመንግስታዊ ፓርላማ፣ የባህር ሃይል፤ የአየርና የምድር […]

በቤኒሻንጉል ክልል በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ

October 28, 2017  (BBN) በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ፡፡ ጥቃቱ በክልሉ ልዩ ኃይል ፖሊስ እገዛ የተፈጸመ መሆኑም ተገልጿል፡፡ እስካሁን ባለው መረጃ የሟቾች ቁጥር ሃምሳ መድረሱ የተነገረ ሲሆን፣ ከ300 በላይ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውም ተነግሯል፡፡ በጥይት ተመትተው የተጎዱ ሰዎች ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውንም ስለ ጉዳዩ የተከታተሉ የመረጃ አካላት ተናግረዋል፡፡ አንዳንድ የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች […]

Ethiopia: Political prisoners and their accounts of Torture

October 28, 2017 Part One Association for Human Rights in Ethiopia (AHRE) is deeply concerned about the ongoing and consistent allegations concerning the use of torture, ill-treatments, and harsh prison condition in Ethiopia against opposition party members, journalists, human rights activist, other political dissidents and terrorism suspects by security forces. AHRE has received numerous reports […]

Somalia Mogadishu: Explosions rock capital

The aftermath of the latest bomb blast in Mogadishu The aftermath of the latest bomb blast in Mogadishu Two explosions have killed at least 14 people in the Somali capital Mogadishu, two weeks after a bomb killed 350. The first blast was caused by a car bomb being driven into a hotel. Militants then stormed […]

የሟች እናት እያለቀሰች የገዳይ እናት እየሳቀች መኖር ይቻላል ብሎ ማሰብ ከንቱነት ነው! (ሃብታሙ አያሌው)

28/10/2017 ዛሬ በደም የመነከር ተረኛዋ አምቦ ሆነች! ሃገር እየቀየሩ መግደል የነገስታት መብት መስሏል፨ ጥይታቸው የወገኖቻችንን ግንባር ሲነድል የኛ ልብ ይደማል ! በአራቱም ማዕዘን የሚወድቀው ወገናችን ለሃገሬ ያገባኛል ስላለ ብቻ ነው፤ የአባቱ ቤት ሲዘረፍ አብሮ ስላልዘረፈ ፨ ዛሬ በአሳዛኝ ሁኔታ መግባቢያችን ቋንቋው ጥይት ሆኗል…!! በኢትዮጵያችን ሁኔታ አንድ ልጅ ወልዶ ለአቅመ አዳም ለማድረስ የሚያስከፍለውን ዋጋ ብረት አንጋች ሎሌም […]

የዋልድባ መነኮሳት ጥሪ!

Posted by admin | 28/10/2017 “እኛ ውጊያችን ከህዝብና ከፈጣሪ ጠላት ጋር ነው !” ካላፉት ቀናት መካከል በአንዱ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ታስረው ያሉትን የዋልድባ በተለየ መጠሪያው የአብረንታት ገዳም መነኮሳት የኾኑት አባ ገ/ሥላሴ ወልደ ሃይማኖት ገ/መድኅን እና አባ ገብረ ኢየሱስ ኪዳነ ማርያም ካሣዬን ለመጠየቅ ሄጄ ነበር፡፡ መነኮሳቱ በማዕከላዊ ከ ፬ ወራት ስቃይ በኃላ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት […]

ከ17 በላይ  ዜጎች አማራ ናችሁ ተብለው በአንድ ቀን ሕይወታቸው ረገፈ  – ግርማ_ካሳ

ከ17 በላይ  ዜጎች አማራ ናችሁ ተብለው በአንድ ቀን ሕይወታቸው ረገፈ #ግርማ_ካሳ   October 28, 2017 15:32 ገዢው ፓርቲ ሕወሃት ስልጣን ከተቆጣጠረ ጀመሮ ላለፉት 26 አመታት የጥቃት ኢላማ ካደረጋቸው መካከል በዋናነት ራሱን አማራ ብሎ የሚጠራዉን ማህበረሰብ አንዱ ሲሆን  ከተለያዩ ብሄረሰቦች የተወጣጣው አማርኛ ተናጋሪ የኢትዮጵያ ብሄረተኛ የሆነው ማህበረሰብ በቀዳሚነት የሚቀመጡ ናቸው። እነዚህን ማህበረሰባት ለማዳከም፣ ከጎንደር የሰሊጥ አገር የሆነችዋን […]

በህንድ ሀገር የሚገኙ 1000 የኢትዮጲያ መምህራን በዶላር እጥረት ምክንያት ትምህርታቸውን ሊያቋርጡ ነው! – ስዩም ተሾመ

October 28, 2017 10:53 መንግስት ትኩረት ሰጥቸዋለሁ ለሚለው “የትምህርት ጥራት” በተለይም “የከፍተኛ ትምህርት ጥራት” የመምህራን ልማት ዋና የትኩረት አቅጣጫ እንደሆነ በተለያዩ ጊዚያት ሲለፍፍ ቆይቷል። ይህን ለማሳካት የከፍተኛ ት/ት ተቋማት መምህራን የትምህርት ደረጃ፤ 0% የመጀመሪያ ዲግሪ፣ 75% የሁለተኛ ዲግሪ እና 25% የሶስተኛ ዲግሪ እንዲሆን እየሰራ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለፁ ይታወሳል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር አመታዊ እቅድና ሪፖርቶች ይህን ያመለክታሉ። በዚህ መሠረት፣ […]