(ከስሜነህ ጌታነህ በድሬቲዩብ)
በምስሉ ላይ የምትመለከቱዋቸው 6 ሰዎች ለሀገሬ የደከሙ ምርጥ ሰዎች ናቸው ፤፤ ከስድስቱ ውስጥ ሁለቱ ብቻ ናቸው በህይወት ያሉት ፤፤ የሰዎቹ ምስል እጄ ሲገባ ብዙ ሃሳቦች ውስጤ መጡ ፤፤ ሀገሬ እውነትም ምርጦች ነበሩዋት አልኩ በሆዴ ፤፤ ምስሉን እያያችሁማን እንደሆኑ መገመት ትችላላችሁ ፤፤ አንድ ቀን በዝርዝር ስለ ሰዎቹ አወጋችሁ ይሆናል ፤፤ ዛሬ ግን በጨረፍታ ባቀምሳችሁ የምትከፉ አይመስለኝም ፤፤
በቀዳሚነት በምስሉ ላይ የምታዩት አቶ ደበበ ሀብተዮሀንስን ነው ፤፤ እርሳቸው ስለ ባንክ ሙያ ሲነሳ በመጀመሪያ ስማቸው ይጠቀሳል ፤፤ የባንክ ሙያንም በጥልቀት ስለመውደዳቸው በስፋት ይነገራል ፤፤
ከእርሳቸው በመቀጠል ያለው ሰአሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ ሲሆን እርሱም ከሚሰራቸው የአበስትራክት ስእሎች ባሻገር ገራሚ ግጥሞችንም እንደሚጽፍ ይወራለታል ፤፤
ከገብረክርስቶስ ደስታ ለጥቀው ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ናቸው ፤፤ ፖለቲከኛና የጂኦግራፊ ባለሙያ የሆኑ ፕሮፍ በርካታ መጽሃፍትና የምርምር ስራዎችን በማቅረብ ይታወቃሉ ፤፤
ቀጥሎ ያሉት የአንድ ለአምስት መጽሃፍ ደራሲ አቶ አስፋው ዳምጤ ናቸው፤፤ አቶ አስፋው በሂስ ስራዎቻቸው የሚታወቁ ሲሆን በኩራዝ አሳታሚ ድርጅት ውስጥም በሃላፊነት ሰርተዋል ፤፤
ከጋሽ አስፋው ጎን ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዮ ገብረመድህን አለ ፤፤ ሎሬት ጸጋዮ በቴአትር ፤ በቅኔ ስራዎቹ ሀገራችንን በስነ ጽሁፍ ዘርፍ ለማስጠራት የቻለ ሰው ነው ፤፤
በመጨረሻ ላይ የአለም ሎሬት አፈወርቅ ተክሌን እናገኛለን ፤፤ የሚደንቃችሁ የስድስቱም ሙያ ለየቅል መሆኑ ነው ፤፤ የባንክ ባለሙያ ፤ ሰአሊና ገጣሚ ፤ ፖለቲከኛና ጂኦግራፈር ፤ ሃያሲና ደራሲ ፤ ባለቅኔና ሰአሊ ፤፤
ሀገር ማደግ ካለባት ሁሉም ሙያ እንደሚያስፈልግ ይህ ምስል ማሳያ ይመስለኛል ፤፤ ክብር ለሊቆቻችን