“ሲኖዶሱ” ቀኖናውንና ዶግማውን ማፍረሱን በተመለከተ የተደረገ ውይይት
ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ በአደባባይ ሚዲያ
ለበርካታ ዓመታት “ህገ ቤተ ክርስቲያን ተጣሰ፣ ምዕመናን ላይ ክህደት ተፈጸመ፣ ቤተክርስቲያኒቷ የአድርባዮችና የፖለቲካ ተላላኪዎች መጠቀሚያ ሆነች” እያሉ ሲጮሁ ከነበሩ ጥቂት የተዋህዶ አባቶች መካካል አንዱ የሆኑት ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ናቸው። ቤተክርስቲያኒቱ ወደ ቀደመ ክብሯ እንድትመለስ ምዕመናን ተገቢውን አባታዊ አገልግሎትና ጥበቃ እንዲያገኙ እንዲሁም ህገ ቤተክርስቲያን እንዲጠበቅ ቀሲስ አስተርአየ የምድረበዳ ጩኸት ሲያሰሙ እንደነበር ይታወቃል (a lone voice in the wilderness)። ከዚህም በተጨማሪ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ በገንዘብ ጵጵስና የገዙ፣ በዝሙት የተጨማለቁ፣ የቤተክርስቲያንን ገንዘብ የዘረፉ፣ ምዕመናንን ለገዳዮች አሳልፈው የሰጡና የተለያዩ ህገ ቤተክርስቲያን የጣሱ “ጳጳሳትንና ካህናትን” ሲያወግዙና ሲኮንኑ መኖራቸው ይታወቃል። በእርግጥ በገንዘብ የተሸመተ “ጵጵስና” የያዙ፣ በዝሙት፣ በሌብነትና በሌሎችም ወንጅሎች የተዘፈቁ ግለሰቦች ትክክለኛ ጳጳሳት ስላልሆኑ “ጳጳሳት” ተብለው መጠራት አይገባቸውም። እነዚህ “ጳጳሳት” መጠሪያውንና ማዕረጉን ይዘውታል እንጅ ተራ ዱሪዬዎችና ማጅራት መቺዎች እንጅ መንፈሳዊ ተልዕኮና ሥነ ምግባር የላቸውም። እነዚህ የሐሰት “ጳጳሳት” ከ2000 ዓመታት በፊት የተነገረው ትንቢት ተፈጽሞባቸዋል። የሐዋርያት ስራ ምዕራፍ 20 ቁጥር 28 እስከ 29 ላይ ስነእነሱ ድርጊት በግልጽ ተጽፎልናል። “በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።”
ሀሰተኛው ሲኖዶስ ምዕመናኑን ለደበኛ ጠላቶቹ ፈርሞ ያስረከበበት “ስምምነት” ብለው የሚጠሩት ጸረ ክርስትና ሰነድ የቤተክርስቲያኒቱን ዶግማና ቀኖና ተክቶ እንደሚሰራ አውጇል። ከዚህ በኋላ ሲኖዶስ የሚባል ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ የለም። ይህ ሲኖዶስ የሚመራው በመንፈስ ቅዱስ ሳይሆን በአብይ እህመድ ነው። ከገዥዎች ጋር በተደረግ መመሳጠር ምዕመናንን በጠራራ ጸሀይ የሸጡ “ጠማማ ነገርን የሚናገሩ” ጩሉሌዎች የተለያየ ነገር በቀባጠር ምዕመናንን እንደለመዱት ለማወናበድና ለማደንዘዝ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። ምዕመናን ለሞት ከዳረጉ በኋላ ሞት እነሱ በራፍ አጠገብ ሲደርስ ተገልብጠው የተፉትን ልሰው ከገዳዮች ጋር አብረው ተሰለፉ። እነዚህን “ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች” አባት ብሎ የሚጠራ እነሱን ተከትሎ ገደል እንዳይገባ እራሱን ከነሱ አርቆ ከትክክለኛና ህጸጽ ከሌለባቸው ካህናት ጋር መንፈሳዊ ህይ ወቱን መቀጠል አለበት። እይናማ ሰው ማየት የማይችለውን መምራት ይገባዋል እንጅ ማየት የማይችል ሰው አይናማውን ቢመራው ተያያዘው ገደል መግባት ስለሆነ መጠንቀቅ ይገባል።
“ሲኖዶሱ” የሰራውን የዶግማና ቀኖና ጥሰት አስመልክተው ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ በአደባባይ ሚዲያ የሰጡትን ቃለ ምልልስ አቅርበንላችኋል። እንዲሁም ቀሲስ አስተርአየ በርካታ መጣጥፎችና ቪዲዮዎች ምዕመናን እንዲታነጹበትና እራሳቸውን “ለመንጋው ከማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች” እንዲጠብቁ በተለያየ ጊዜዎች አስተላልፈዋል። ከነዚህም መካካል የተወሰኑትን ሊንሎች እዚህ ላይ አስቀምጠንላችኋል።