ግንቦት 20 የወለደው የመለያየት አደጋ!

የግንቦት ሃያ 23ኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ነው፡፡ ኩነቱን ምክንያት በማድረግ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃንና የድርጅቱ (ኢሕአዴግ) አመራሮች ግንቦት ሃያ ለሀገራችን “አስገኝቷቸዋል” የሚሏቸውን ትሩፋቶች እየዘረዘሩ የተለያዩ ዘገባዎችን በማቅረብ ላይ ናቸው፡፡ የዕንቁ ባልደረቦች በበኩላቸው ግንቦት ሃያ “መጣብን ወይስ መጣልን?” ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ ግንቦት ሃያን በሚመለከት፣ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃንና የኢሕአዴግ አመራሮች የሚያስቀምጧቸው የተለመዱ ተረኮች አሉ፡፡ “ሀገራችን የዛሬ ሃያ ሶስት ዓመት መስቀለኛ መንገድ ላይ ነበረች፤ የብተና አደጋ ተጋርጦባት ነበር፤ ከዚህ ሁሉ አደጋ የታደጋት ኢሕአዴግ የሚመራው መንግሥት ነው” ወዘተ ይባላል፡፡ የኢሕአዴግ መሪዎች እንደሚሉት አሁንም ቢሆን ሀገራችንን ከአደጋ ሊታደጋት የሚችለው የኢሕአዴግ መስመር ብቻ ነው፡፡ ሕዝቡም ወይ የኢሕአዴግን ‹‹ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ›› መስመር ወይ ደግሞ የተቃዋሚዎችን ‹‹ፀረ-ልማትና ፀረ-ዴሞክራሲያዊ›› መንገድ ሊመርጥ እንደሚችል፤ የተቃዋሚዎችን መስመር መከተል ግን ሀገሪቱን ወደ ጥፋት እንደሚወስዳት አበክረው ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡ ለመሆኑ በአገዛዙ በኩል ሲነገሩ የቆዩትና በመነገር ላይ ያሉት ነጥቦች ምን ያህል ውሃ የሚቋጥሩ ናቸው? የተወሰኑትን እንመርምራቸው፡፡ የኢኮኖሚው ሁኔታ አገዛዙ በተለያዩ ሰነዶቹ እንደሚገልጸው ከተሃድሶው በፊት ባሉት 10 ዓመታት ውስጥ ያለምንም የጠራ ርዕዮተ-ዓለምና ስትራቴጂ ሲንገዳገድ ቆይቶ በድርጅቱ በተለይ በሕወሓት ውስጥ የተከሰተው መከፋፈል (የተወሰኑትን አመራሮች ከአባልነት በማስወገድና የተወሰኑትን በማሰር) ከተወገደ በኋላ በተሃድሶው ወቅት የተለያዩ የልማት ስትራቴጂዎችን ቀርፆ መንቀሳቀስ በመጀመሩ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ማስመዝገብ ችሏል፡፡ በተለይ ላለፉት ስምንት ዓመታት በተከታታይ ሲመዘገብ የቆየው ዕድገት የስትራቴጂውን ትክክለኛነት ያረጋገጠ እንደሆነ በሰፊው ይነገራል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ መንግሥት የሚለውን ያህል ባይሆንም ኢኮኖሚዊ ዕድገት መኖሩን ብዙ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መስክረዋል፡ ፡ በቅርቡ ሙዲስና ፊችና ስታንደርድ ኤንድ ፑር የተባሉት የተባሉት ታዋቂ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ሁኔታና ብድር የማግኘት ዕድሏን ገምግመው ሁለቱም ድርጅቶች ቢ አንድ (B1) ሰጥተዋታል፡፡ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት መኖሩን ላለፉት አሥርት ዓመታት የተሠሩትን መንገዶችና፣ ግድቦችና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን እንዲሁም በግሉ ዘርፍ የሚሠሩ ፕሮጀክቶችንና ሌሎች እንቅስቃሴዎችን በመመልከት ማንም ሊመሰክርለት ይችላል፡፡ መጠኑ ቢያከራክርም ዕድገት ስለመኖሩ የ ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ ጥያቄ የሚነሳው ዕድገቱ ምን ዓይነት ዕድገት ነው? ከዕድገቱ ተጠቃሚ የሆኑት ወገኖች እነማን ናቸው? ወዘተ በሚሉት ነጥቦች ላይ ነው፡፡ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅትና ዓለም ባንክ በተደጋጋሚ እንደገለጹት የኢትዮጵያ መንግሥት በኢኮኖሚው ውስጥ ያለው ተሳትፎ እጅግ የተጋነነና አሳሳቢ ነው፡፡ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የኢትዮጵያ መንግሥት በኢኮኖሚው ውስጥ ያለው ተሳትፎ እጅግ የተጋነነ (በዓለም በኢኮኖሚ ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ ከሚያደርጉ ሶስት መንግሥታት አንዱ ነው) በመሆኑ የግሉን ዘርፍ ዕድገት እያቀጨጨው ነው፤ ስለዚህም ተሳትፎውን መቀነስ እንዳለበት ሲያሳስብ ቆይቷል፡፡ ስለዚህ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ቢኖርም ዕድገቱ በግሉ ሴክተር እንቅስቃሴ የተመዘገበ አለመሆኑ ደግሞ ግልጽ ነው፡ ፡ ይህ አንዱ ችግር ነው፡፡ ሌላም ነጥብ አለ፡፡ የግል ዘርፍ የሚባለው አካልም በብዙ መልኩ ሊታይ የሚገባው ነው፡፡ በአንድ በኩል አቶ ክቡር ገና በአንድ ጽሑፋቸው እንዳሉት ከመንግሥትና ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር አብረው በመሥራት በጣም በአጭር ጊዜ የከበሩ ‹‹ፓራሹት ነጋዴዎች›› አሉ፡፡ እነኝህ አካላት በጥቂት ዓመታት ውስጥ በሚያስገርም ፍጥነት የብዙ መቶ ሚሊዬን ባለንብረቶች የሆኑ ናቸው፡፡ ከዕድገቱ በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ የሆኑት እነኝህ አካላት ናቸው፡፡ በኢንዶውመንት ስም የሚንቀሳቀሱት ግዙፍ የፓርቲ ድርጅቶችም በግሉ ዘርፍ ሥር የሚጠቃለሉ ናቸው – በመንግሥትም በዓለም አቀፍ ድርጅቶችም፡፡ ይሁን እንጂ እነኝህን ግዙፍ ድርጅቶች በኃላፊነት የሚያንቀሳቅሷቸው የኢሕአዴግ መሪዎች መሆናቸው ደግሞ የታወቀ ነው፡፡ የአገዛዙ መሪዎች የሚመሯቸው ድርጅቶች ከሌላው የግል ዘርፍ አኩል ይንቀሳቀሳሉ፤ የበለጠ እንክብካቤ አይደረግላቸውም ማለት በጭራሽ አይቻልም፡፡ እንደሚታየውም በግል ጥረቱ የሚፍጨረጨረው ነጋዴ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከገበያ ውጪ ሲሆን እነኝህ ድርጅቶች በአንጸሩ እየገነኑ በመሄድ ላይ ናቸው፡፡ አቶ ስብሃት ነጋ በአንድ ወቅት ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ እንደገለጹት ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ የኤፈርትን ያህል ትልቅ ሀብት የሚያንቀሳቅስ ድርጅት የለም፡፡ ድርጅቱ ይህን ያህል ግዙፍ ሀብት ያፈራው ባለፉት ሃያ ሶስት ዓመታት ውስጥ ነው፡፡ እንዴት እንደዚህ ሊያድግ ቻለ? በኢኮኖሚው ውስጥ ያለ ያልተፈታ ጥያቄ ነው፡፡ ኢኮኖሚያው ዕድገቱ በጥረቱ የሚንቀሳቀሰው የግል ባለሀበት የተመዘገበ አለመሆኑ ዋናው የሀገሪቱ ራስ ምታት ነው፡፡ ዕድገቱ የተገኘው በአብዛኛው በመንግሥት እንቅስቃሴ ነው፡፡ መንግሥት ለተለያዩ የልማት ተግባራት የሚያወጣው አብዛኛው ገንዘብም በብድር የተገኘ መሆኑም ይታወቃል፡፡ ከዕድገቱ የሚጠቀሙት አካላት ደግሞ የመንግሥት አካላትና ከእነሱ ጋር አብረው የሚሠሩት ‹‹የፓራሹት ነጋዴዎች›› ናቸው፡ ፡ ሌላው ሁሉ የበይ ተመልካች ነው፡፡ በዚህ ዓይነት ግልጽነትና ተጠያቂነት በሌለበት የቢዝነስ ከባቢ ውስጥ ሕገ-ወጦች ሲያድጉ በጥረታቸው ለማደግ የሚንቀሳቀሱት ከገበያ ውጪ ይሆናሉ፡፡ ብሔራዊ ከበርቴ መፍጠር አይቻልም፤ አልተፈጠረም፡፡ ‹‹ግብርና መር የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂው በጣም ውጤታማ ነው፤ ሚሊየኖችን ሚሊየነር አድርጓል›› ሲባል የቆየ ቢሆንም አርሶ አደሩ አሁንም እንደድሮው (ወይም ከዚያ በባሰ ሁኔታ) ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ሕይወት በመምራት ላይ ነው፡ ፡ የታየ መዋቅራዊ ለውጥ የለም፡፡ እንደታቀደው እንኳን ግብርናው አድግ ኢንዱስትሪውን ሊመራው ይቅርና ራሱን አርሶ አደሩንም መመገብ አልቻለም፡፡ በአጠቃላይ፣ አንደኛ ዕድገቱ በራስ ሀብት እና/ወይም ባለሀብት የተገኘ አይደለም፡፡ በዚህ ምክንያት በመንግሥትና በብድር ላይ የተንጠለጠለ በመሆኑ ቀጣይነቱ አጠራጣሪ ነው፡፡ ከሁሉ በላይ ደግሞ፣ ዕድገቱ ፍጹም ፍትሃዊ አይደለም፡፡ ከገዥው ኃይል ጋር ንክኪ ያለው ቡድን ፍጹም ባልተጠበቀ ፍጥነት ሲመነደግ አብዛኛው ሕዝብ አሁንም የበይ ተመልካች ነው፡፡ በሀገራችን ባለፉት ሃያ ሶስት ዓመታት ከታዩት አዳዲስ ጉዳዮች አንዱ የፖለቲካ ሥልጣኑን የያዘው ኃይል ራሱን በከፍተኛ ደረጃ በኢኮኖሚው እንቅስቃሴ ውስጥ ማስገባቱ ነው፡፡ በጣም የተደራጀ የፖለቲካ መደብ ተፈጥሯል፡ ፡ ዕድገቱ እንደሚባልለት አይደለም፡፡ እንዲያውም አደጋ ያረገዘ ነው ለማለት ነው፡፡ የፖለቲካው ሁኔታ በእርግጥም የአገዛዙ መሪዎች እንደሚሉት ባይሆንም ሀገራችን የዛሬ ሃያ ሶስት ዓመት ችግር ላይ ነበረች፡፡ ሕዝቡ ለአሥርት ዓመታት ጨቁኖና አስጨንቆ ሲገዛው የነበረው የደርግ አገዛዝ በመውደቁ ቢደሰትም (መደሰቱን ተቃዋሚዎችን በመርዳትና ለአገዛዙ ድጋፉን በመንፈግ ገልጿል) ሽምቅ ተዋጊዎች በያዙት አቋም ላይም ከፍተኛ ጥርጣሬ ነበረው፡፡ በዚህ ምክንያት ብዙ ስጋቶች ነበሩ፡፡ ይህ እውነት ነው፡፡ መረጋጋት የተፈጠረው ግን አሸናፊ የሆነና የታጠቀ ብቸኛ ኃይል (ኢሕአዴግ) በመኖሩ እንጂ እንደሚባለው ሁሉንም ያሳተፈ የሽግግር መንግሥት በመፈጠሩ ቅሬታ ያለው አካል በመጥፋቱ አልነበረም፡፡ በኃይልም ቢሆን ግን ሠላም በመፈጠሩና ኢሕአዴግ ሥልጣን ከጨበጠ በኋላ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ለመመስረት እንደሚሠራ፣ የመደራጀትና የመናገርና የመጻፍ ነጻነትን እንደሚያከብር ወዘተ በመግለጹ ብዙዎች ተስፋቸው ከፍተኛ ነበር፡፡ ይህን ተስፋ አንግበው ወደሀገራቸው የገቡ ብዙ ወገኖችም ነበሩ፡፡ ከእነኝህ ውስጥ አንዳንዶቹ ተመልሰው የአገዛዙ ጠንካራ ተቃዋሚዎች ለመሆን በቅተዋል፡፡ ይህ ሁሉ ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ የኢሕአዴግ መሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የርዕዮተ-ዓለም ለውጥ ምክንያት ጥርሳቸውን የነቀሉበትን የኮምኒስት (በተለይ “የአልባንያ ሲሻሊዝም”) ትተው ‹‹ነጭ ካፒታሊዝም›› ያሉትን ርዕዮትና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን እንደሚከተሉ ቢያውጁም ሃቀኛ ለሆነ የመድበለ-ፓርቲ ሥርዓት ፍቅር እንደሌላቸው በብዙ ከመጀመሪያው ጀምሮ ታይቷል፡፡ በሽግግሩ ወቅት ሁሉም ድርጅቶች በፖለቲካ ሂደቱ እንዳይሳተፉ ከማድረግ ጀምሮ የተሳተፉትም ቢሆኑ በልዩ ልዩ
“ከግንቦት ሃያ 1983 ዓ.ም. በኋላ በኢትዮጵያውያን መካከል መለያየት፣ ጥላቻና ቁርሾ ነግሷል፡፡ ዜጎች በኢትዮጵያዊነታቸው በሁሉም አካባቢዎች ተንቀሳቅሰው መሥራት የማይችሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ሁሉም በየክልሉ ተጠርንፎና ታጥሮ እንዲቀመጥ ተፈርዶበታል፡፡ ከክልሉ ወጪ የሚሄድ ካለ ያለቦታው እንደተገኘ ይቆጠራል፡፡ ምን ያህል አካባቢውን ቋንቋ ጠንቅቆ ቢያውቅም የመንግሥት ሥራ አያገኝም፤ የቤት መሥሪያ ወይም የንግድ ቦታ አይሰጠውም፤ እንዲያውም ‹‹አካባቢህ አይደለምና ውጣ›› ይባላል”
ጥላቻውና ቂም በቀሉም አለ፡ ፡ የተፈጠረውን የፌደራል አደረጃጀት ተጠቅመው በየክልሉ የከበሩ የመንግሥት ኃላፊዎች እና/ወይም ‹ኤሊቶች› ሕዝቡ እርስ በርሱ እንዲናከስ አበክረው ይሠራሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ባልተለመደ መልኩ ብዙ የብሔረሰብ ግጭቶች ተከስተዋል፡፡ አሁንም በብዙ ቦታዎች በቋፍ ላይ ያሉ ግጭቶች አሉ፡፡ ሁሉም በየቤቱ ቂም በቀል እያረገዘ ‹‹እህህ›› ማለት ጀምሯል፡፡ አገዛዙ እንደሚለው ሳይሆን አሁንም ከዩጎዝላቪያ፣ ሩዋንዳ ወይም ሶማሊያ ሁኔታ ብዙም ፈቀቅ አላልንም፡፡ እንዲያውም አሁን ሁኔዎችን ይበልጥ ለመለያየት ምቹ አድርገናቸዋል ማለት ይቻላል፡፡ መለያየቱም በሠላም ሊፈጸም የሚችል አይሆንም፡፡ የቤት ሥራቸውን ያልሠሩ ሀገራት ምን ያህል ዕድገት ቢያስመዘግቡ፣ ምን ያህል የዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ ቢያድግ፣ ግሩም ግሩም መሠረተ ልማቶችን ቢገነቡ፣ ምን ያህል ለረዥም ጊዜ የዘለቀ ሰላም (በጭቆና ውስጥ ያለ ሰላም ሰላም ከተባለ) ከብጥብጥ እንደማያመልጡ እነሊቢያ አሳይተውናል፡ ፡ ትልቅ አብነቶች ናቸው፡፡ ያች ዜጎቿን እየከፈለች ታስተምር የነበረችው ሊቢያ በጎሣ ከአምስት ስድስት ተከታትፋ፣ እነዚያ የሚያማምሩ ወደቦቿና ከተሞቿ ወድመው የጦር አበጋዞች መፈንጫ ሆናለች፡፡ ዜጎቿ በየጎሣው ተቧድነው መተጋተጉን ይዘውታል፡፡ የሶሪያም ሁኔታ ተመሳሳይ ነው፡፡ እኛስ ወዴት እያመራን ነው? አንዳንዶች ኢሕአዴግና ኢሕአዴግ የዘረጋው ብሔረሰብ-ተከል የፌደራል ሥርዓት ለሁለት አሥርት ዓመታት መዝለቁ በራሱ የተዘረጋው ሥርዓት ጥንካሬ እንደሆነ አድርገው ይገልጻሉ፡፡ ይህ ግን በጭራሽ ውሃ የሚቋጥር አመክንዮ አይደለም፡፡ ለመሆኑ ጋዳፊ የሚመሩት ሥርዓት ለስንት ዘመን ኖረ? የአሳድ ቤተሰቦች የሚመሩት ጨቋኝ ሥርዓት ለስንት ጊዜ ቆየ? ራሳችንን ካላሞኘን በስተቀር መንገዳችን እጅግ ፈታኝና ተስፋ አስቆራጭ እየሆነ ነው፡፡ ለዚህ ነው ግንቦት ሃያ መጣልን ወይስ መጣብን ብሎ መጠየቅ አስፈላጊና ወቅታዊ የሚሆነው፡፡ ከዋቢዎች 1. ኢሕአዴግ፣ ዴሞክራሲና ዴሞክራሲያዊ አንድነት በኢትዮጵያ (1997 ዓ.ም.) 2. ኢሕአዴግ፣ አገራዊ ለውጦች ቀጣይ ፈተናዎችና አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ መፍትሔዎች (2000 ዓ.ም.) 3. Oktay F. Tanrisever, why are Federal arrangements not a panacea for containing ethnic nationalism? Lessons from the post-soviet Russian experience (2009) 4. ገብሩ አስራት፣ የኢሕአዴግ አብዮታዊ ዴሞክራሲና ችግሮቹ (2002) 5. Samuel Huntington, political Development in Ethiopia: a peasant based dominant party democracy (1993)
ፊቸር መንገድ ከሂደቱ እንዲወጡ ተደርጓል፡፡ ከቀዝቃዛው ጦርነት ማብቃት በኋላ ሊብራል ዴሞክራሲ አሸናፊ ሆኖ በመውጣቱና ምዕራባውያን ሀገራትና የገንዘብ ድርጅቶች ብድርና ዕርዳታን ከዴሞክራሲ/ ዴሞክራታይዜሽን ጋር በማያያዛቸው ምክንያት ኢሕአዴግ ገንነው እስካልወጡ ድረስ የሌሎችን ድርጅቶች መኖር በተወሰነ ደረጃ ይፈልገው ነበር፡ ፡ የምርጫ- አምባገነን የሚባሉትን ሀገራት ፈለግ ሲከተል ቆይቷል፡፡ ኢትዮጵያ ባለችበት ሁኔታ ጠንካራ መንግሥት እንደሚያስፈልጋት እና ያንን ጠንካራ መንግሥት ሊመራ የሚችል ጠንካራ ድርጅት እንደሚያስፈልግ ለኢሕአዴግ መሪዎች ምክር ከለገሱ ምሁራን መካከል የታወቁት የሀርቨርድ ዩኒቨርሲቲ ምሁር ፕሮፌሰር ሳሙኤል ሃንቲንግተን ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ የፕ/ር ሃንቲንግተን ምክር በሃሳብና በተግባር ልዕልናን/የበላይነትን (hegemony) ስለመያዝ እንጂ በጠብ-መንጃ እያስፈራሩ ወይም አንድ ለአምስት እያደራጁ ወዘተ በሁሉም ምርጫ ማሸነፍን አያካትትም፡ ፡ ሌሎች የምርጫ አምባገነኖች እንደሚያደርጉት ሁሉ የኢሕአዴግ መሪዎች የመረጡት ጠንካራ ፓርቲዎችን በጠብ-መንጃ አፈሙዝ ማዳከምና ማጥፋት፣ ለሥልጣን የማያሰጉ ድንክየና የተዳከሙ ድርጅቶች እንዲኖሩ ሁኔታዎችን ማመቻቸትና ወቅቱን የጠበቀ ምርጫ እያደረጉ መመረጥን ነው፡፡ የምርጫ-አምባገነናዊ ሥርዓቱን በአብዮታዊ ዴሞክራሲ፣ በልማታዊ መንግሥት ወይም ደግሞ በአውራ ፓርቲ ወዘተ ሥርዓታት ስም ለመቀባባት ይሞከራል፡፡ አገዛዙ በ1997 ዓ.ም ከደረሰበት አስደንጋጭ ውድድር ወዲህ በርግጎ የወሰዳቸው እርምጃዎች እውነተኛ ማንነቱን የሚያስገነዝቡና የሃሳብ ብዝኃነትን ለማስተናገድ ፍላጎት የሌለው መሆኑን የሚያጋልጡ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ በግሉ መገናኛ ብዙኃንና በሲቪክ ማኅበራቱ ላይ የደረሱትና የሚደርሱት አሉታዊና ዴሞክራታይዜሽኑን የማያግዙ እርምጃዎች ሁኔታውን ይበልጥ ግልጽ ያደርጉታል፡፡ አገዛዙ በዚኸው አስተሳሰብ እየተመራ ዋና ዋና ተቃዋሚዎችን አዳክሞ (ከራሳቸው የውስጥ ችግር ጋር) በምርጫ 2002 ዓ.ም. ማንነቱን በሚያጋልጥ መልኩ 99.9 በመቶ አሸነፍኩ አለ፡ ፡ ብዙዎች ይህን የምርጫ ውጤት ከታዘቡ በኋላ ከምርጫ-አምባገነናዊ ሥርዓት ወደ ብቸኛ ፓርቲ ሥርዓት እየሄድን ነውን ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ስለዚህ ኢሕአዴግ ጨቋኙን አገዛዝ የታገለው ለሕዝብ ነጻነትና ሉዓላዊነት እንደሆነ አበክሮ ቢገልጽም ያለፉት ሃያ ሶስት ዓመታት ተመክሯችን እንደሚያስገነዝቡን ከግንቦት 20/1983 ዓ.ም. በኋላም ቢሆን ያው በአምባገነን አገዛዝ ሥር መሆናችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ግልጽ እየሆነ መጥቷል፡ ፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከመሻሻል ይልቅ የተለየ ሃሳብ ያላቸውን ወገኖች የማይታገስ፤ የሃሳብ ብዝኃነትን የማይታገስ ደርጅት እየሆነ ነው ማለት ይቻላል፡ ፡ አሁንም እንደ ድሮው በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት ወደ ሀገራቸው የማይገቡ ኢትዮጵያውያን በዓለም ዙሪያ ይገኛሉ፡፡ አሁንም እንደ ድሮው ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎች ይሰደዳሉ፤ ገለልተኛ ማኅበራት እንዲጠፉ ይደረጋል ወዘተ፡፡ ምናልባት የተቀየረው ጭቆናው ሳይሆን የጭቆናው መንገድ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ችግሩ ‹‹ሠላም ሰፍኗል፤ ልማት ላይ ነን፤ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መሥርተናል፤ በትክክለኛው የህዳሴ ጎዳና ላይ ነን›› ወዘተ በሚባልበት በአሁኑ ወቅት ሀገራችን መስቀለኛ መንገድ ላይ መሆኗ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ወዴት? ‹‹ኢሕአዴግ ወደ ሥልጣን በመምጣቱና ትክክለኛ ስትራቴጂ በመከተሉ ምክንያት ኢትዮጵያ ብዙዎች እንደገመቱትና እንደጠበቁት እልቂት አልተከሰተም፡፡ ሀገሪቱም እንደነ ዩጎዝላቪያ፣ ሩዋንዳ ወይም ሶማሊያ አልሆነችም፡፡›› ይላሉ የኢሕአዴግ ሰዎች፡፡ ኢትዮጵያ ከግንቦት ሃያ 1983 ዓ.ም. ወዲህ በዘረጋችው የፌደራል ሥርዓት ምክንያት ሠላም እንዳገኘች፣ በሕዝቡ መካከል ዴሞክራሲያዊ አንድነት እንደተፈጠረም ይነገራል፡፡ አሁን የአፈጻጸምና ዴሞክራሲው ታዳጊ በመሆኑ ምክንያት እዚህም እዚያም ከሚፈጠሩ ጥቃቅን ግጭቶች በስተቀር ችግር እንደሌለ፣ ሀገራችን በህዳሴ ጉዞ ላይ ስለመሆኗም በብዛት ይወራል፤ ይጻፋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን የገጠማት አደጋ ልክ እንደድሮው አንድ ጨቋኝ አምባገነናዊ አገዛዝን መሸከሟ አይደለም፡፡ የወቅቱ ችግር በእጅጉ ከዚያ ያልፋል፡፡ ሁሉንም ዜጋ ሊያሳስበው የሚገባም ነው፡ ፡ ግንቦት ሃያ ሕዝቡ ከአንድ አስከፊ አምባገነናዊ አገዛዝ ተላቅቆ ወደተሻለ አገዛዝ የተሸጋገረበት ወሳኝ ምዕራፍ ነው ለማለት አይቻልም፡፡ ባለፉት አሥርት ዓመታት የተከሰቱትና አሁንም በመከሰት ላይ ያሉት ሁኔታዎች ይህን አያሳዩም፡፡ ሕዝቡ የጠበቀውን ዴሞክራሲ አላገኘም፡፡ ሲካሄዱ የቆዩት ምርጫዎች በአብዛኛው የአገዛዙ የቅቡልነት ማግኛ ወይም የመግዣ መሣሪያዎች ናቸው፡ ፡ የተሻለ ነጻነትና ውድድር የነበረው የ1997ቱ ብሔራዊ ምርጫም እንደታየው በገዥው ኃይልና በራሳቸው በተቃዋሚዎች ችግር ምክንያት በአሳዛኝ ተደምድሟል፤ እንዲያውም የዚያ ምርጫ ጦስ እስካሁንም ብዙ ችግሮችን እየወለደ ቀጥሏል፡ ፡ ሕዝቡ የተገባለት በነጻነት የመደራጀትና ሃሳቡን በነጻነት የመግለጽ መብቱ አልተከበረም፡፡ አሁንም ጋዜጠኞቸ ይታሠራሉ፤ ይሰደዳሉ ወዘተ፡፡ ይህ ሁሉ ግን የችግሩ በጣም አነስተኛው ክፍል ነው፡፡ ሌላ ሁሉንም ዜጋ የሚያሳስብና ሊያሳስብም የሚገባ የሀገሪቱን በሀገርነት መቀጠል አለመቀጠል የሚመለከት ችግር አለ፡፡ እንደሚባለው ግንቦት ሃያ የዴሞክራሲያዊ አንድነት መገንባት የተጀመረበት ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ ቢሆን መልክም ነበር፡ ፡ ግን አይደለም፡፡ እንደሚባለው ሳይሆን በገቢር እንደሚታየው ከግንቦት ሃያ 1983 ዓ.ም. በኋላ በኢትዮጵያውያን መካከል መለያየት፣ ጥላቻና ቁርሾ ነግሷል፡፡ ዜጎች በኢትዮጵያዊነታቸው በሁሉም አካባቢዎች ተንቀሳቅሰው መሥራት የማይችሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ሁሉም በየክልሉ ተጠርንፎና ታጥሮ እንዲቀመጥ ተፈርዶበታል፡፡ ከክልሉ ወጪ የሚሄድ ካለ ያለቦታው እንደተገኘ ይቆጠራል፡፡ ምን ያህል አካባቢውን ቋንቋ ጠንቅቆ ቢያውቅም የመንግሥት ሥራ አያገኝም፤ የቤት መሥሪያ ወይም የንግድ ቦታ አይሰጠውም፤ እንዲያውም ‹‹አካባቢህ አይደለምና ውጣ›› ይባላል፡፡ እንደነዚህ ያሉ እጅግ የበዙ አጋጣሚዎችን ታዝበናል፤ ሁኔታው አሁንም ቀጥሏል፡፡ ቀደም ሲል በናይጀሪያና በሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ስንሰማቸው የቆየናቸው ሁኔታዎች በሀገራችን እየታዩ ናቸው፡፡ ዛሬ በሚያሳዝን መልኩ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ተፈጥሯል በሚባልባት ኢትዮጵያ፣ ከአንዱ ወደ ሌላው ክልል መንቀሳቀስ ልክ ወደሌላ ሀገር እንደመሄድ እየተቆጠረ ነው፡ ፡ እንዲያውም ወደ ሌላ ሉዓላዊ ሀገር የሚሄዱት ወገኖች መብታቸው የተጠበቀ ነው ማለት ይቻላል፡፡ አንዱ አስፈሪ እውነታ ይህ ነው፡፡
ቻላል፡፡አንዱአስፈሪእውነታይህነው፡፡

Leave a Reply