ድርቅ እና ረሃብ የፈጠረው ሰብኣዊ ቀውስ የሚሊዮኖችን ሕይወት ለማዳን ሃላፊነት ሊሰማን ይገባል::
ድርቁን ለፖለቲካ ጨዋታ ማዋል አደጋ አለው::ለጋሽ አገሮችም እርዳታ ላለመስጠት እጃቸውን ከመሰብሰብ አልፈው ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን እስከማቅረብ ደርሰዋል::በአለም የዜና ማሰራጫዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ረሃብ እና ድርቁ የፈጠረው ሰብኣዊ ቀውስ የሶሪያ ጦርነት ከፈጠረው ቀውስ የባሰ ነው ተብሎ አለም በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሃዘን በተቀመጠበት ወቅት በኢትዮጵያ ያለው አገዛ ግን በምግብ እሕል ራሳችንን ሽለናል የሚሉ ሽልማቶች እና የተሰናባች ባለስልጣኖቹን አዳዲስ ምቾቶች እየነገረን ይገኛል::ይህ ሃላፊነት የጎደለው የመንግስት አስተዳደር ለዜጎቹ ደንታቢስ በመሆኑ ለብሄራዊ ውርደት ዳርጎናል::ማእዳቸው ባዶ የሆኑ በድርቅ የተጠቁ ወገኖቻችን አስቸኳይ እርዳታ በሚያስፈልጋቸው በዚህ ወቅት ቅድሚያ ሊሰጣቸው እየተገባ ያለውን እውነት መካድና ለፖለቲካ ፍጆታዎች መሯሯጥ በሕዝብ ሕይወት ላይ መቀለድ ነው::
በርግጥ ይህ ጉዳይ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ግዴታ እና ሃላፊነት ቢሆንም አገዛዙ ባለበት የፖለቲካ ትኩሳት ምክንያት ከራሱ ውጪ በዚህ ጉዳይ ላይ ሌሎች ኢትዮጵያውያን እንዳይሳተፉ በማድረግ ከፍተኛ ጋሬጣ ፈጥሯል::ይህ ጋሬጣ በድርቅ የተጎዱ ወገኖች አስፈላጊውን እርዳታ እንዳያገኙ ሲያደርግ የውጪ እርዳታ ድርጅቶችም በስራቸው ላይ እክል በመፍጠር አቅጣጫ በማሳት አገዛዙ በድርቅ የተጠቁ ወገኖች እንዳይረዱ እንቅፋት እየሆነ ይገኛል::ይህ ሁሉ እና ሌሎች በገሃድ የሚታዩ ችግሮች በመከሰታቸው ዜጎች ከረሃብ ሸሽተው የሚበሉት ለማግኘት ሕይወታቸውን ለማዳን ወደ ከተማ በመሰደድ ላይ ናቸው::ባለፉት 60 አመታት በኢትዮጵያ ተከስቶ የማያውቅ አደገኛ የሰብኣዊ ቀውስ አገሪቷን እያመስት ይገኛል::
አገሪቷ አድጋለች ተመንድጋለች ይህን ያህል የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግበናል በሚል ሃሰተኛ ፕሮፓጋንዳ የአገዛዙ መሪዎች እየፎገሩን እስክመቼ ራሳችንን እየሸወድን እንኖራለን::ተአምር ልንፈጥር ነው በተባለበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ልትወጣበት የማትችልበት ቀውስ ውስጥ ገብታለች::ለጋሽ አገሮችም እርዳታ ላለመስጠት እጃቸውን ከመሰብሰብ አልፈው ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን እስከማቅረብ ደርሰዋል::የአገዛዙ ፖሊሲ የፈጠረው በፖለቲካ ጫና በሃሰት የኢኮኖሚ እድገት እና በማህበራዊ ዝቅጠት በፈጠረው አጣብቂኝ ውስጥ የሚገኘው የኢትይኦጵያ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል::ብዙሃኑ እስር ቤት ታጉረዋል::የሃገሪቱ ኢኮኖሚ አሽቆልቁሉ ደሃ ብቻ ሳይሆን የደሃ ደሃዎች ተፈጥረዋል ጥቂት ቱጃሮች ዘረፋውን ተያይዘውታል::በሃገሪት የተከሰተው ድርቅ ሕዝብን እየፈጀ ነው::በቅድመ ማስተንቀዊያ መዘጋጀት ሲገባ በመሸፋፈል ለትልቅ አደጋ ያጋለጡን ወገኖቻችንን ለሞት እና ለስደት ያበቁ የሃስት ፕሮፓጋንዲስቶች ስልጣኑን ለሕዝብ የማስረከብ ግዴታ አለባቸው::ድርቅ እና ረሃብ የፈጠረው ሰብኣዊ ቀውስ የሚሊዮኖችን ሕይወት ለማዳን ሃላፊነት ሊሰማን ይገባል::