ህወሓት ክፍፍልዋ በጣም ተባብሶ በረሃብ እየሞተ ያለው ህዝብ እስከ መርሳት ኣድርስዋታል። ከሶስት ሳምንት በላይ የዘለቀ ስብሰባ እያካሄዱ ለማመን የሚያስቸግሩ ወንጀሎች እንደተሰሩ እየሰማን ነው። ስለ ግምገማዎቹ ሌላ ቀን እመለስበታለው።

ሰሞኑ ኣቶ ኣባይ ወልዱ ኣፅቢ፣ ሳዕሲዕ ፃዕዳእምባ፣ ኢሮብ በረሃብ የተጠቁ ወረዳዎች እየጎበኙ ይገኛሉ።
በጉብኝታቸው ወቅት ኣንድ ግራ የሚያጋባ ተማፅኖ በረሃብ ተቆፍድዶ እየሞተ ላለው ለህዝባችን ” እርዳን” የሚል ኣስገራሚ ንግግር ኣድርገዋል። ስለዚህና የሚልዮኖች ሂወት እንዴ ኣደጋ ውስጥ እንዳለ መረጃ ልስጣቹ።
” የመጣው የእርዳታ ኮታው ትንሽ ስለሆነ ህዝባችን ተባበረን፣ ቅድምያ ሊረዳ የሚገባው ራስህ በመጠቆም ለባሰው እንዲዳረስ እርዳን ” ኣቶ ኣባይ ወልዱ በጉብኝታቸው የተናገሩት።
” ድርቅ ያጠቃን ቤት ሳይለይ ነው። እገሌ ከእገሌ ይሻላል የሚያስብል ምክንያት የለንም። መንግስት እንደምንም ብሎ ሊረዳን ይገባል፣ ልጆቻችን በረሃብ እየሞቱብን ነው። ” የሳዕሲዕ ፃዕዳ እምባ ኑዋሪዎች የተናገሩት።
” የውሃ ችግር ድሮም የ7 ሰዓት መንገድ ተጉዘን በማምጣት ነው የምንጠጣው። ኣባይ ይሄ ነገር ኣንተራስህም ታውቀዋለህ። ኣሁን ምንጮቻችንም ደርቀዋል። ችግሩ ከኣቅማችን በላይ ሆኖብናል ” የኢሮብ ኑዋሪዎች።
የኣቶ ኣባይ ጉብኝት መረጃ ለመሰብሰብ ካልሆነ በስተቀር ለህዝቡ ያመጣለት ለውጥ የለም።
እርዳታ ከመስጠት ይልቅ ” ኮታው ትንሽ ስለሆነ ትንሽ በቤትህ ያለህ ህዝብ እርዳታ ባለመውሰድ ተባበረን ” የሚል ተማፅኖ ብቻ ነው።
እነ ዶክተር ደብረፅዮንም ችግሩ ለነ ኣባይ ወልዱ በመጣልና በማላከክ በሚፈጠር ህዝባዊ ተቃውሞ ለጥቅማቸው ለማዋል በፖለቲካዊ ቁማር ዓይን ትርፍ ለማስገኘት ብለው ሰው እየሞተ እያዩ እንዳላዩ ሆነው እያለፉት ነው።
ኣቶ መለስና ኣንጃቸው በ77ቱ ድርቅ በሰው ሞት እንዳተረፉት ዓይነት እነ ደብረፅዮንም ለማትረፍ ኣሰፍስፈው ይገኛሉ።
በዚህ ድርቅ የሚጠፋ ሂወት የክልል መንግስት ብቻ ሳይሆን እነ ኣቦይ ስብሓት፣ ደብረፅዮን፣ ጌታቸው ኣሰፋ፣ ቴድሮስ ኣድሓኖም የመሳሰሉ በፌደራል ስልጣን የሚገኙም እኩል እንጠይቃቹሃለን።

እነ ኣባይ ወልዱም ብቻቹ ተጨንቃቹ የተራበው ህዝብ “እርዳን” ከምትሉ ሓቁ ኣፍረጥርጣቹ በማውጣት ለነ ት.እ.ም.ት፣ ማ.ረ.ት፣ ደደቢት፣ መለስ ፋውንዴሽን፣ የብኣዴን ድርጅታዊ በኣል ስፖንሰር እየሆኑ ያሉት መቐለና ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች፣ ለባለሃብቶች፣ ነጋዴዎች ፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ ላልተደረቀ ህዝብ የእርዳታ እንዲያደርግ ጥሪ ኣቅርባቹ ተገላገሉ።
እውነት የነ ኣባይ ወልዱ ቤት ዘግቶ ጭንቀት ለህዝቡ ምንም ፋይዳ የለውም። ይልቅ ይሉኝታ ሳይዛቹ የእርዳታ ጥሪ ኣቅርቡና ሰብኣዊ ርህራሄ ያለው ሰው ሁሉ የተቻለው ድጋፍ ያድርግና ህዝቡ ከእልቂት እናድነው።
ይሄ ጉዳይ በኣማራ ክልልም ተመሳሳይ መሆኑ የደረሱኝ መረጃዎች ያረጋግጣሉ።
የተከበራቹ ኢትዮጵያውያን ሆይ……! በትግራይ ክልል ያለው በረሃብ የተያዘውና ኣስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልገው ህዝብ ከ2.5 ሚልዮን በላይ መሆኑ እየታየ ነው። በሌሎች ክልሎችም ተመሳሳይ እንደሆነ እየታየ ነው።

ለኣንድ ሚልዮን ህዝብ ተብሎ የመጣው እርዳታ እዚህ ግባ የሚባል እንዳል ሆነና እጥረቱ ፍንትው ብሎ እየታየ ነው። ለስደት የሚነሳ ህዝብም እየተከለከለ ይገኛል።
ስለዚ ኣሰቃቂ ትእይንት ሳናይ፣ ያ በ77 ያጋጠመን የገፅታ መበላሸት እንዳይገጥመን ካሁኑ እንረባረብ ።
መንግስትም ታሪካዊ ሃላፊነት ኣለህና ኣቅም ያለው እህዝብ የሚችለው እንዲያበረክት የእርዳታ ማሰባሰብያ መድረኮች እንድታስተባብርልን እናሳስባለን።
የተራበና ምንም የሚላስ የሚቀመስ የሌለው ህዝብ “እርዳን” ብሎ ከመማፀን ለተቀረው ህዝብ እንዲረዳ ማስተባበር ይሻላል።
#Ethiopia_Faminr
#ክፉ_ቀን
#ዘበን_ኣካሒዳ