ወይዘሮ ኣልጋነሽ ገብሩና ሌሎች 6 የዓረና ኣባላት የሆኑት የእንደርታ ወረዳ፣ እግሪሓሪባ ቀበሌ ኑዋሪ የዓረና ኣባላት ቀበሌው ወደ መቐለ ከተማ መግባትና ኣለመግባት ተፈጠረ ባሉት ኢ ፍትሓዊ ውሳኔ ምክንያት ከቀበሌ እስከ ፌደራል መንግስት ኣብዮቱታቸው ኣቅርበው። መንግስት መፍትሄ ከማበጀት ይልቅ ተደፈርኩ ብሎ ገበሬዎቹ ማንገላታትና ማጥቃት ስራየ ብሎ ተያያዘው።
እነ ወይዘሮ ኣልጋነሽ እስከ ፌደራል የሄዱበት ኣብዮቱታ ኣጥጋቢ መልስ ሳያገኝ ለ4 ዓመታት ያለ መንግስታዊ ኣስተዳደር የቆዩ ሲሆን “በሽብር” ክስ እንዲለጠፍባቸው ምክንያት የሆነባቸው በዓረና ኣባልነት ከተመዘገቡ በኋላ ነበር።
እነ ወይዘሮ ኣልጋነሽ “በሽብርተኝነት” ተከሰው ለኣራት ወር ያህል የዋስትና መብታቸው ተከልክለው ታስረው ከከረሙ በኋላ የክሱ ይዘት “ከሽብርተኝነት” ወደ “ህዝብ ለዓመፅ ማነሳሳት” የሚል ክስ ቀይረው ለያንዳንዳቸው በ15 ሺ ብር የዋስትና ኣቅርበው ከእስር ወጥተው ነበር።
ኣራት ወር ሲታሰሩ በተለይ ለወይዘሮ ኣልጋነሽ ከክልል ቢሮ ሃላፊዎች እስከ ፖሊስ ኮማንደሮችና የሃይማኖት መሪዎች ከዓረና እንድትወጣ ሲያስፈራሯት፣ ሲያባብሏትና ሲያስገዝትቷት “ከዓረና ኣባልነቴ በምንም ተኣምር ኣልወጣም” ብላ ኣሳፍራ መለሰቻቸው።
የህወሓት ትኩረት በዋነኛነት በኣልጋነሽ ይሁን እንጂ እያንዳንዱ ታሳሪ ኣባል የተለያየ ማስፈራርያና ማባበያ እያቀረቡ ከዓረና ኣባልነቱ ሊያስወጡት ሞክረዋል።
ወይዘሮ ኣልጋነሽ ” ኣገር ውስጥ ከሚንቀሳቀሱና ካገር ውጪ ያሉ ኣሸባሪዎች ግንኙነት በመፍጠር” የሚል ክስ የተጣበቀባት ቢሆንም ሁሌ የምትጠየቀው ከዓረና እንድትወጣ ነበር።
ኣልጋነሽ የ3 ኣባታቸው በሞት ያጡ ህፃናት ጠላ እየሸጠች ጧሪና ኣሳዳጊ እናት ናች። በነገራችን ላይ ወይዘሮ ኣልጋነሽ ማንበብና መፃፍ የማትችል ገበሬ ናት።
ፍርደኞቹ “ህዝብ ለዓመፅ በማነሳሳት” በሚል ኋላ የተሻሻለ ክስ በ07 / 03 / 2008 ዓ/ም በዋለው የክልል ከፍተኛ ፍርድቤት ችሎት 7ቱ የዓረና ኣባላት የ3ና 4 ዓመት ፅኑ እስራት ፈርዶባቸዋል።
1) ወይዘር ኣልጋነሽ ገብረ በ 3 ዓመት
2) ቐሺ ብርሃኑ ቖባዕ በ 3 ዓመት
3) ኣያሌው ጣዕምያለው በ 3 ዓመት
4) ሙዑዝ ፀጋይ በ 3 ዓመት
5) ሓጋዚ ካሕሱ በ 4 ዓመት
6) ሓለፎም ገብረዝጊ በ 4 ዓመት
7) ከለል ሕሸ በ 4 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶባቸው መቐለ ወኽኒ ቤት ገብተዋል።
የእግሪ ሓሪባ ህዝብ በማስተርፕላኑ ጥያቄ ምክንያት ለ4 ዓመታት ያለ መንግስታዊ ኣገልግሎት፣ የህክምናና የህፃናት ክትባት፣ ትምህርት፣ ምርጥ ዘርና ማደበርያ ተነፍጎባቸው ተገልለው ቆይተዋል።
እግሪሓሪባ በድርቅ ከተጠቁ ኣከባቢዎች ኣንዱ ሲሆን ህዝቡ “ወደ መቐለ መስተዳደር እንገባለን ብላቹ ካልፈረማቹ እርዳታ ኣንሰጥም” ተብለው በከፍተኛ ረሃብ ተጠቅተዋል።
“ኣሸባሪዋ” ኣልጋነሽ ገብሩ በመንግስት ዓይን እንድትገባ ያደረጋት ኣንዱ ምክንያት በተደራዳሪነቱና በኣሳማኝነቱ የሚታወቀው ኣባይ ፀሃየ ከበየነ መክሩ ሁኖ የመራው ስብሰባ ሞግታና ተከራክራ ረትታና ኣሳፍራ በመመለስዋ መሆኑ ይታወቃል።
ኣሳዛኙ ዜና 15 ሚልዮን ህዝብ በድርቅ በተጠቃበት ሰዓት ኣቤትና እናት ሁና ያሳደገቻቸው 3 ህፃናት ልጆችዋ ያለጡዋሪ መቅረታቸው ነው።
#Ethiopia_Famine
#ክፉ_ቀን
#ዘበን_ኣጋሒዳ