(ቢቢኤን ራድዮ) የኢትዮጵያ መንግስት በሙስሊሙ ማህበረሰብ የእምነት ጉዳዮች በይፋ ጣልቃ መግባቱን ተከትሎ ህዝበ ሙስሊሙ በድምጹ የመረጣቸዉ የህዝብ ወኪሎች በአለም አቀፍ ደረጃ ተጽእኖ መፍጠራቸዉ የሚታወቅ ነው። በአይነቱ ልዩ የሆነንን የሰላማዊ ትግል ዘይቤን የቀየሱት የህዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች፤ በኢትዮጵያ መንግስት የደህንነት ባለስልጣናት ለከፍተኛ መከራና ስቃይ መዳረጋቸዉ የሚዘነጋም አይደለም። ከማእከላዊ የማሰቃያ ግዞት ጀምሮ በቂሊንጦና በቃሊቲ እስርቤቶች ዉስጥ ያለፉት የህዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች ሰላምን በመስበካቸዉ እስከ 22 አመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ካንጋሮ በሚባለዉ ፍርድ ቤት ተበይኖባቸዋል።

የነዚህን የህዝብ ወኪሎች ንጹህነትና የሰላም አምባሳደርነት አያሌ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በመመስከር በነጽ መለቀቅ አለባቸዉ ሲሉም ድምጻቸዉን በይፋ እያሰሙ ይገኛሉ።

የህዝበ ሙስሊሙ ሰላማዊ ትግል ከጅመረበት ጀመሮ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የሚደርሰዉ በደል የሚዘግበዉ የ አሜሪካ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ መንግስት በተለያዩ አጋጣሚዎች በሚወስዳቸዉ እርምጃዎች ስጋት እንዳለዉ በመግለጫ ቢገልጽም ከጨቋኙ የኢትዮጵያመንግስት ጋር በዲፕሎማሲያዊ አሰራር ያብራል የሚል ትችት ይቀርብበታል።
usa
ወደ አዲስ አበባ ክፍተኛ የሉካን ቡድን የላከዉ የ አሜሪካ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ከህዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች ከኡታዝ ያሲን ኑሩ፣ ከሳቢር ይርጉና ከህግ አማካሪዎቻቸዉ ጋር በመገናኘት ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መወያየቱን ቢቢኤን ለማወቅ ችሏል። በሜሪካዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጃን ኬሪ የተላኩትና ከህዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች ጋር የተገናኙት የመስሪያቤቱ ከፍተኛ ባለስልታናት የዲሞክራሲና፣የሰብዓዊ መብትና የሰራተኞች ዱዳይ ረዳት ሴክረታሪ፣ራልፍ ኦልሰን የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተርና ሮዝ ጃክሰን የዲሞክራሲ፣ የሰብዓዊ መብትና የሰራተኞች ጉዳይ ሐላፊ ናቸዉ።

እነዚህን የህዝብ ወኪሎች የኢትዮጵያ መንግስት ማእከላዊ አስገብቶ በቶርቸር ያሰቃያቸዉና ደህንነቶች ይቆታጠሩታል በሚባለዉ ፍርድ ቤት እስከ 22 አመት ጽኑ እስራት የፈረደባቸዉ ቢሆነም የአሜሪካ መንግስት የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት (ሚኒስቴር) በሙሉ እዉቅናና ክብር እንደ ህዝብ ወኪል እነርሱን ማናገሩ የኢትዮጵያ መንግስትን ፍረጃ ዉድቅ የሚያደርግ የዲፕሎማሲ እርከን ነዉ በማለት አስተያየት እየተሰጠበት ነዉ። ሌሎቹም አእስር ላይ የሚገኙት የህዝብ ወኪሎች መፍትሔን ለማፈላለግ ህዝብ ዉክልና የሰጣቸው በመሆናቸዉ ነጻነታቸዉን በይፋ ተቀዳጅተዉ በመሰል አገራዊና ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ላይ አምባሳደር ሆነዉ የሚሰሩበት ቀን እሩቅ አይደለም።ሁሉም በአቅሙ፣ሁሉም በችሎታዉ ተጠናክሮ መስራት አለብት ተብሏል። በተለይም በዋሽንግተን ዲሲና በአካባቢዋ ያሉ ኢትይጵያዉን ለዚህ ዲፕሎማሲያው ተሞክሮ ያደረጉት አስተዋ የላቀ በመሆኑ ጥረታቸዉ ሊቀጥል ይገባል የሚል ገንቢ አስተያየት አለ።

Related Posts:

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48370#sthash.3qFXXrSy.dpuf

Leave a Reply