ብስሚላሂ-ኣልረህማን-ኣልረሂም
በጠላት ተደልለው የህዝቦችን ፍትሃዊ ትግል ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀሱ
ሃዲያን ፍትሃዊ ትግሉን ሊቀለብሱ ኣይችሉም!
ከቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ
የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ባለፉት ረጅም ዓመታት ህዝቦቻችን ላይ ሲደርስ የነበረውንና ኣሁንም ስልጣኑን በያዘው ኣምባገነኑ የወያኔ መንግስት እየደረስ ያለውን ጭቆናና የመብት ጥሰት በማስቆም እኩልነት፣ ፍትህ፣ ዱሞክራሲና ነጻነትን በማረጋገጥ ህዝቦች በሃገራቸው ላይ የነጻነትና የሰላም ኣየር እንዱተነፍሱ ለማድረግ ትግል በማካሄድ ላይ ይገኛል ። እያካሄድን ያለነው ትግልም ከጊዜ ወደ ጊዜ ህዝባዊ ፍቅርና ድጋፍ እያገኘና እያደገ ሲሆን በዚህም በርካታ የቤኒሻንጉል ተወላጆች ወደ ድርጅታችን በመቀላቀል ድርጅቱ የሰጣቸውን ግዳታ በመወጣት ላይ ናቸው። ሃገር ቤት ያለው ወገናችን ወደ ሰራዊታችን በመቀላቀል የትጥቅ ትግሉን ከማካሄድና በተለያየ መልኩ እየደገፈ እንዲለው ሁሉ የኢትዮጵያ መንግስትን ጭቆና በመሸሽ በተለያዩ የውጪ ሃገራት የሚገኙ የቤኒሻንጉል ተወላጆችም ወደ ትግላችን በመቀላቀል ከድርጅታችን በሚሰጣቸው መመሪያ መሰረት ትግለን በማፋጠን ላይ ይገኛለ።
በሌላ በኩል ደግሞ ቀደም ሲል በድርጅታችን ኣባልነት ታቅፈው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ኋላ ላይ ግን በጠላት ፕሮፓጋንዲና መደለያ ተታልለው የህዝቦችን ትግል ለማኮላሸት የሚንቀሳቀሱ ኣንዲንድ ግለሰቦች የወያኔን ተልዕኮ ለማሳካት ሲሰሩ ታይተዋሌ። ድርጅታችን እነዚህ ኣባላት ከስህተት መንገዲቸው ተመልሰው ትላንት መስዋዕትነት የተከፈሉበትንና ኣሁንም ውድ የህይወት ዋጋ እንዱሁም የተለያዩ መስዋዕትነቶች እየተከፈሉበት ባለው የህዝቦች ትግል የዜግነት ድርሻቸውን እንዱወጡ ሲያደርግ ነበር። ሆኖም ግን እንዲንድ ግለሰቦች ከዚህ የወያኔን ስውር ዓላማ ካነገበ ድርጊታቸው ለታቀቡ ባለመቻላቸው ድርጅታችን የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ ተገድዷል።
በዚሁ መሰረት በየመን የወያኔ ኣምባሳደር የነበረው ዩሱፍ ሃሚድና ልጁ ኻሊድ ዩሱፍ እንዱሁም ኢብራሂም ዩሱፍ የተባሉ ግለሰቦች እስከ 2013ዓም ድረስ የድርጅታችን ኣባል የነበሩና በድርጅቱ ዓላማና መመሪያ ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም ግን እነዚህ ግለሰቦች ከቅርብ ጊዜ ወዱህ የድርጅታችን፡ የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄን ዓላማ የሚጻረር ድርጊት ሲፈጽሙ የታዩ ሲሆን ከዚህ እኩይ ተግባራቸው ታቅበው የድርጅታችን ህግና ድንብ በሚፈቅደው መሰረት እንዱንቀሳቀሱ ምክርና ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ሊታቀቡ ኣልቻሉም። እንዱያውም ድርጅታችን ፍትሃዊ ትግሉን በኣፋጣኝ ከግቡ ለማድረስና ህዝቦቻችንን ከጭቆና ለማላቀቅ በተለያየ መልኩ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ለማደናቀፍና የጠላትን ዓላማ ከግቡ ለማድረስ በገሃድ በመስራት ላይ ናቸው።
በመሆኑም ድርጅቻችን እነዚህ የህዝቦቻችን ቀንደኛ ጠላት ከሆነው የወያኔ መንግስት ጋር በመመሳጠር ትግላችንን ለማደናቀፍና በጀግኖቻችን መስዋዕትነት ያገኘነውን ድል ለመቀልበስ የሚሯሯጡት ሶስቱ ግለሰቦች ላይ የመጨረሻ እርምጃ በመውሰድ ዛሬ ህዳር 18 ቀን 2015 ዓም ከደርጅቱ ኣባልነት ሙሉ ለሙሉ ያባረረ መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል። ከዚሁ ጋር በማከልም የድርጅታችን ኣባላትና ደጋፊዎች እንዱሁም ህዝባችንና ኣጋሮቻችን እነዚህ ግለሰቦች በየትኛውም እንቅስቃሴያቸውና ድርጊታቸው ድርጅታችንን የማይወክሉ፡ የጠላት ተላላኪ ከሃድያን መሆናቸውን እንዱገነዘቡ እንፈልጋለን።
በመጨረሻም የጠላትን ድብቅ ተልዕኮ ይዘው በተለያዩ ወጪ ሃገራት በሚኖሩ የሃገራችን ዜጎች ዘንድ በመሄድ ወያኔያዊ መርዝ ለማሰራጨትና የትግል እንቅስቃሴያችንን ለማደናቀፍ ለሚጥሩ ማናቸውም የጠላት ተላላኪ ሃዱያን ድርጊታቸው ፍትሃዊ ትግሉን እንደማይቀለብስና ከታሪክ ተጠያቂነት የማያወጣቸው መሆኑን እያሳሰበ፡ ህዝቦች እያካሄዱት ያለው ፍትሃዊ ትግል ደግሞ በጠላትና በከሃዲያን መደለያና መሰረተ-ቢስ ወሬ የማይደናቀፍ መሆኑንም ቤ.ህ.ነ.ን በጥብቅ ያስገነዝባል።
የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ
Source =Zehabesha