የትጥቅ ትግሉን መንገድ መርጠው ታግዬ አታግላለው ብለው አስመራ የወረዱት የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የፊታችን ማክሰኞ ዲሴምበር 2 በአውሮፓ ፓርላማ ንግግር እንዲያደርጉ መጋበዛቸውን ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች አመለከቱ::

ከአስመራ ወደ ብራሰልስ እንደበረሩ የሚነገርላቸው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለሕዝብ ክፍት በሆነው በዚሁ የአውሮፓ ፓርላማ ላይ ንግግር እንዲያደርጉ የተጋበዙት በወ/ሮ አና ጎሜዝ ነው ተብሏል:: በዚህ ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ መገኘት ለሚፈልጉ – የአውሮፓ ነዋሪዎች በምርጫ 97 ወቅት የአውሮፓ የምርጫ ታዛቢ ለነበሩት ወ/ሮ አና ጎሜዝ ደብዳቤ
ፕሮግራሙ ለሕዝብ ክፍትና ነፃ በመሆኑ አስቀድማችሁ:-

  • ስማችሁን
  • የተወለዳችሁበትን ቀን/ ወር/ ዓ.ም
  • ዜግነታችሁን
  • እና የፓስፓርት ቁጥራችሁን በ Anamaria.gomes@europarl.europa.eu በመላክ መመዝገብ እንደሚቻል የደረሰን መረጃ ጠቁሟል::

euro

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሚገኙበት በዚሁ የአውሮፓ ፓርላማ ላይ ለመገኘት ምዝገባው እስከፊታችን አርብ ድረስ የሚቀጥል ሲሆን በፓርላማው ላይ ማክሰኞ የሚገኙ ሰዎች ፓስፖርት ወይም ሕጋዊ ወረቀት መያዝ እንደሚኖርባቸው ተጠቁሟል::

የኢትዮጵያ አገዛዝ ፕሮፌሰር ብርሃኑን አሸባሪ እንዲባሉለት የየሃገራቱን መሪዎች በሚለምንበት በዚህ ወቅት ፕሮፌሰሩ በአውሮፓ ፓርላማ መጋበዛቸው ለስርዓቱ ትልቅ የፖለቲካ ኪሳራ ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ::

Source  =  Zehabesha

Leave a Reply