ቁርጠኝነት – አዲሱ የወያኔ የማዘናጊያ እና የማጭበርበሪያ ዲስኩር – ጊዜው የስር ነቀል ለውጥ ነው::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

የውስጥ አጣብቂኟ ሲበረታ ወያኔ አዲስ ፋሽን ይዛ መታለች -ቁርጠኝነት- የሚሉት::በሃሰተኝነት እና በፕሮፓጋንዳ ማጭበርበር ወያኔን የሚችለው የለም::ወያኔ እያወቀ አላወቀም እንጂ በጠንካራ የስትራቴጂ ሰንሰለት የሚያደራጀው ያጣው ሕዝቡ ከሱ ቀድሞ በመሄድ ፕሮፓጋንዳ የሚተፉ ማሽኖቹን መስማት ካቆመ ቆይቷል:: ባለፉት 25 አመታት ያልተሰራ ስራ እና ያልተተገበረ ፖሊሲ እንዴት በአምስት አመት(ከቆየ)ውስጥ ተኣምር ሊፈጠር እንደሚችል የሚገርም ነው::ወያኔ የገባበት የውስጥ አጣብቂኝ እለመውጣት ቢቧጥጥም እስከዛሬ እዛው እንደተነከረ ስላለ የውስጥ ችግሮቹን እስኪፈታ ድረስ ሕዝብን ማጭበርበር እና ማዘናጋት የሚሉትን ጠንካራ የማይተገበሩ ቃላቶች በመናገር ለማሳመን ይፍጨረጨራል::ብየአምስት አመቱ ትራንስፎርሜሽን እድገት ፕላን ምናምን በሚሉት የወረቀት ቀበኛ በሆነ ደካማ ፖሊሲያቸው ለውጥ ማምጣት ያልቻሉ የወያኔ ጀሌዎች ዛሬ ደግሞ በአዲስ ስልት “ቁርጠኝነት” በሚል ዲስኩር ከች ብለዋል::

 ቁርጠኝነት ቁርጠኝነት … ቢባልም ለመተግበር እጅግ ፈታኝ እና አስቸጋሪ በሆኑ የሕወሓት ሌቦች ደንቃራነት እንደማይቻል የታወቀ ጉዳይ ነው::ይህን ቁርጠኝነት ሕወሓት ለማዘናጊያነት የፈጠራት ነገር ነች እንጂ እንዸት ተደርጎ የአንድ አከባቢ ሰዎች በበላይነት በዘመድ አዝማድ እና በአብሮ አደግነት በተቧደኑበት እኩይ አገዛዝ ውስጥ በቁርጠኝነት አዲስ መፍትሄ መፍጠር እንደሚቻል የማይገባ ነገር ነው::የመልካም አስተዳደርን ለመፍጠር እና ሙስናን ለማስወገድ ሕወሓት በየትኛው ሞራሉ ተነስቶ እንደሚተገብረው መልስ የማይገኝለት ጉዳይ ሲሆን በከፍተኛ የሙስና ኔትወርክ የተያያዙት የሕወሓት ባለስልጣናት እና ባለሃብቶች ከነቡድኖቻቸው ለማስወገድ የሚቻለው በኢሕኣዴግ የቁርጠኝነት ቲሪሪም ሳይሆን በለውጥ ሃይሎች ብቻ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል::

የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልግው ስር ነቀል ለውጥ እንጂ ቁርጠኝነት የሚሉት ዝባዝንኬ ማታለያ አይደለም::ቁርጠኝነትን ለመፍጠር ሌላ 25 አመት አያስፈልግም::ስርነቀል ለውጥ ለማድረግ ግን የሚያስፈልገው ጊዜ አናሳ ነው::ዜጎቹን በአሸባሪነት ሲሻው በአደገኛ ቦዘኔነት የሚፈርጀው አገዛዝ ፍትሕን በትእዛዝ የሚገድል አገዛዝ በሃሰት ክስ እና በሃስት ምስክሮች ሕዝብን የሚያንገላታ አቃቢ ሕግ እና በዘረፋ ራሳቸውን ከቱጃር ተርታ ያሰለፉ ባለስልጣናት ባሉበት አገዛዝ የማፊያ ቡድን መስርተው የሃገር ሃብት የሚዘርፉ የሕወሓት ጋሻ ጃግሬዎች ኔትወርክ በተዘረጋበት ስርኣት ሃሰተኛ እና ትላንት ያሉትን ዛሬ የማይደግሙት ባለስልጣኞች በወረሩት ቤተመንግስት እና ፓርላማ ወዘተ .. ባለበት አገር ላይ በቁርጠኝነት ለውጥ አመጣለሁ ማለት አንድም ራስን ማጃጃል ሁለትም ወደ ገደል እየገሰገሱ እንደሆነ ስለሚጠቁም ስርነቀል ለውጥ እንዲመጣ ጠንክረን በመታገል በኢትዮጵያ ውስጥ የነጻነት ፍሬ እንዲጎመራ ትግሉ የበለጠ ሊጠነክር ይገባል::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Leave a Reply