በዘመናዊት ኢትዮጵያ ከዘመነ ሚኒሊክ እስከ ደርግ ከየትኛውም የኢትዮጵያ ግዛት ተወላጆች በበለጠ በሃገሪቱ ላይ የስልጣንና የፈላጭ ቆራጭነት ሚና ባለቤት የነበረው የሸዋ ኦሮሞ ጨቋኝና ወራሪ በሚል አማራን እየጨፈጨፈ ነው። ይህ የኢሰመጉ ሪፖርት በሸዋ የሚኖሩ አማሮችን አሳዛኝ የመከራ ህይወት ፍንትው አድርጎ ያጋለጠ ነው።
~———–~———–~———-~———-~—–
“ብልታችንና የሴቶቻችን ጡት በፒንሳ እየተጠመዘዘ በወረዳው ፖሊስ ጣቢያ ከተሰቃየን በኋላ ተባረናል” ከምዕራብ ሸዋ የመጡ የአማራ ተወላጆች
ሰሚ ያጣው የሰመጉ ጩኸት
( በሙሉቀን ተስፋው )
ሰብአዊ መብት ጉባኤ ጽሕፈት ቤት ስደርስ ቤቱ በጋዜጠኞችና በውጭ ዲፕሎማቲክ ቡድን ተወካዮች ተሞልቶ ነበር። ሰመጉ “ብሔር ተኮር ማፈናቀልና እንግልት እንዲሁም በልማት ስም በዜጎች ላይ የሚፈጸም የማፈናቀልና የንብረት ማውደም በአስቸኳይ ይቁም!” በሚል ያዘጋጀውን መግለጫ ለመስማት ነበር። ከአፋር ክልል መንግሥት የቴምር ዛፍ የወደመባቸውንና በምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ሀብት ንብረታቸው ተቃጥሎ የተባረሩ አማራ አርሶ አደር ተወካዮችን ጭምር በማስመጣት ምስክርነት እንዲሰጡ ፊት አካባቢ ተቀምጠዋል። የተለያዩ የሰመጉ የሥራ ኃላፊዎች መግለጫውን ካነበቡ በኋላ ከሁለቱም ቦታ የመጡ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች የነበረውን ሁኔታ ሲናገሩ የሚያሳዝንም ተስፋ የሚያስቆርጥም ነበር።
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ በእርሻ ሥራ የሚተዳደሩ የአማራ ተወላጆች የተለያየ ዓይነት ሰብሎችን በመዝራት ራሳቸውን፣ ቤተሰባቸውንና ክልሉን በአጠቃላይ ለአገሪቱ ገበያ የሚቀርብ ምርት በማምረት የሚታወቁ ውጤታማ አርሶ አደሮች ነበሩ። ይሁንና በአካባቢው የሚገኙ ባለሥልጣናትና የጸጥታ ኃፊዎች እነዚህን አርሶ አደሮች “እናንተ የዚህ አካባቢ ተወላጅ ሳትሆኑ ሀበት እያፈራችሁ የአካባቢው ተወላጅ ግን ከእናንተ ያነሰ ገቢ ያላቸው ናቸው፤ ይህን ገቢ ያገኛችሁት በእኛ መሬት ላይ ነው፤ ስለዚህ የክልሉ ተወላጆች ባለመሆናችሁ ክልሉን ለቃችሁ ውጡ” በማለት ንብረታቸውን በተለያየ ጊዜ በመንጠቅ እነዚህን አርሶ አደሮች በተለያየ ጊዜ ለእስራት ዳገዋቸዋል። የአካባቢውን ሕዝብም “በእናንተ መሬት ነው ሀብት ያፈሩት” እያሉ ጥላቻና ግጭትን ሲሰብኩ እንደቆዩ በሰመጉ በ136ኛ መግለጫና ምስክርነታቸውን በሰጡ አርሶ አደሮች ተነግሯል።
ምስክርነታቸውን ከሰጡት መካከል በአካባቢው ተወልዶ ያደገው አቶ አለሙ አስፋው “በ1996 ዓ.ም. በዞኑ መዳሉ ወረዳ 52 እንዲሁም በ2002 ዓ.ም. ደግሞ በዳኖ ወረዳ 152 የአማራ ቤትና ንብረት ሲቃጠል ምንም የተወሰደ እርምጃ የለም” ሲል ከዚህ በፊትም ስለነበረው ብሔር ተኮር ጥፋት ይናገራል። የሰመጉ መግለጫና ገበሬዎቹ እንደሚያረጋግጡት መጋቢት 27 ቀን 2007 ዓ.ም. አቶ ዘውዱ እንዳለ የተባለ የኦሮሞ ተወላጅ ተገድሎ ይገኛል። ተገድሎ የተገኘውን ገዳይ ሁሉም ኀብረተሰብ ወንጀለኛውን ለማገኘት እየተረባረበ ባለበት ሰዓት “ይህ ግድያ የተፈጸመው በአማራ ብሔር ተወላጆች ነው” በማለት የኖኖ ወረዳ የፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ኃይሉ ድሪባ፣ የኖኖ አሎ ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ ጎሳየ ገችና መቶ አለቃ ገነነ በየነ የተባሉ የፖሊስ አባላት የቀበሌና የፖሊስ አባላትም በማስተባበር የአካባቢው ሕዝብ በአካባቢው በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ እንዲነሳሳ በማድረግ ሚያዚያ 9 ቀን 2007 ዓ.ም. 85 አርሶ አደር አባውራዎችን ለእስራት ከዳረጓቸው በኋላ ቅዳሜ ማለትም ሚዚያ 10 ቀን 2007 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት አካባቢ ዘር በመምረጥ የአማራ መኖሪያ ቤትና ንብረት ነው ያሉትን እየመረጡ በእሳት እንዲቃጠል አድርገዋል።
የታሰሩትን ወንዶችና ሴቶችም ብልታቸውንና ጡታቸውን በፒንሳ እየጠመዘዙ ቤቱን ለሚቃጠልበት የሚውል ለነዳጅ በማለት ከእያንዳንዳቸው 300 ብር ተቀብለዋቸዋል። ከ27 ገበሬዎች ብቻ 8100 ሰብስበዋል። ገበሬዎቹ ሲወጡ ሀብት ንብረታቸውም ሆነ የነበራቸው ነገር ሁሉ ወድሞ ነው ያገኙት። በንግድ ሥራ የምትተዳደር ወ/ሮ ጽጌ የተባለች የአካባቢው ነዋሪ የነበረውን ሁኔታ ስትገልጽ “ቤታቸው ሲቃጠል ልብሳቸውን ሁሉ አጥተው ራቁታቸውን ደብቂን እያሉ ወደኔ በርካታ ልጆች መጡ። ማጀት አስገብቼ ወደ ፖሊስ አዛዡ ቢሮ በመሄድ ‹ኧረ ተው በሰው ስቃይ እንዲህ አትደሰት?› ስለው ገና አንቺም ትቃጠያለሽ አለኝ” በማለት የነበረውን ሁኔታ ትናገራለች።
አቶ ዓለሙ አስፋው በበኩላቸው “የሚሊሻ ኮማንደር ነኝ። በጊዜው ሰላሳ ጎራሽ ክላሽ ይዤ ነበር። የፖሊስ አዛዡ አቶ ደመና ግዘውን ሲገድላቸው ቆሜ እየተመለከትኩ ‹እንዴ ተው ሕግ ባለበት አገር› ስለው ‹አማራ እኮ ነው አይመለከትህም› አለኝ፤ በያዝኩት ጠመንጃ አይደለም እርሱን 30 ሰውም መግደል እችል ነበር፤ ግን ያን ባደርግ የሁሉም ችግር መንስኤው እርሱ ነው ስለምባል እያነባሁ ዝም አልኩ፤ እኔ ሰላም ለማስከበር ላይቤሪያ ድረስ ሄጃለሁ፤ ሆኖም በአገሬ ሰላም የለም። የሰው አገር ሰላም ሳስከብር በአገሬ ላይ ግን ስለሰላም መናገር እንኳን አልቻልኩም” ሲል በምሬት ገልጿል።
አቶ ደመና በሚያዚያ 12 ቀን 2007 ዓ.ም. ልጃቸውን ሊድሩ ዘመድ አዝማድ ሁሉ ተጠርቶ ዝግጅቱ ሁሉ አልቆ ነበር። ሆኖም የልጃቸውን ደስታም ሳይመለከቱ ሰርጉ አንድ ቀን ሲቀረው በመንግሥት የፖሊስ አዛዥ ተቀጥቅጠው ሞተዋል። የሟች ወንድም “ወሊሶ ሆስፒታል ሳይደርስ ነው የሞተው፤ የግፋቸው ግፍ ራሳቸው የገደሉትን አስከሬን ለምርመራ አዲስ አበባ መላክ አለብን ብለው 6000 (ስድስት ሽህ ብር) አምጣ አሉኝ። የለኝም ስላቸው አስከሬኑን አውላላ ሜዳ ላይ አስቀምጠው መውሰድ እንደማልችል ተነገረኝ። አስከሬኑ ሜዳ ላይ ፈራርሶ ከሚቀር በማለት ተበዳድሬ ሰጠው። የራሴን እንኳ እንዳልሰጥ ያለኝን በሙሉ አቃጥለውታል። የግፍ ግፍ ነው የተሰራብን” በማለት በእንባ ነው የተናገሩት።
ሰመጉ በ136ኛ መግለጫው የአንድ ሰው ማለፉን፣ 10 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ 99 የእሳር ክዳን ቤቶች በእሳት መቃጠላቸውንና 25 የቆርቆሮ ክዳን የመኖሪያ ቤቶች በእሳት መውደማቸውን ገልጿል። የአርሶ አደሮቹን መኖሪያ ቤትና ንብረት ቃጠሎ ተከትሎ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሴቶች፣ ሕጻናትና አቅመ ደካሞች የሚገኙባቸው ተፈናቃዮች በአካባቢው በመሰደድ ወደ ደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን አበሸጌ ወረዳ ድንኳን ውስጥ ተጠልለው ሲረዱ መቆየታቸውንም አስታውሷል። ሰመጉ በጋዜጣዊ መግለጫው ጥፋት የፈጸሙት የመንግሥት አካላት ምንም አይነት ሕጋዊ እርምጃ እስካሁን እንዳልተወሰደባቸውና የተፈናቀሉ ገበሬዎችም ተመልሰው በሰላም መኖር ለመቻላቸውን ጠቅሷል። ይባስ ብሎም ነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ ሮንድ እንዲጠብቅ የተመደበውን አቶ አቢ ተክለማርያም በጥይት ተደብድቦ ተገድሏል። ገበሬዎቹ እንደሚናገሩት ከሚለብሱት ልብስ ጀምሮ በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ያስጠጓቸው የአካባቢው ሰዎች እንደሰጧቸውና ተመልሰው ግን ለመኖር እስካሁን አዳጋች እንደሆነባቸው ነው ለዝግጅት ክፍላችን የገለጹት።
በአዲሱ ዓመት ዋዜማ በጥይት ተደብድቦ የተገደለውን አቶ አቢን ተክለማርያምን አገዳደል በተመለከተ ሲናገሩ “የሌሊት ጥበቃ ሮንድ ከአራት ኦሮሞዎች ጋር ተመደበ። ሆኖ ተብሎ እንደዚህ እንደተመደበ የሚያውቀው ነገር አልነበረም። ነገር ግን በጥይት ተደብድቦ ተገደለ” በማለት የተሰራውን ሴራ ይገልጻሉ። እንደአርሶ አደሮች ገለጻ ከሆነ ይህን በዋናነት ሲያስተባብሩ የነበሩ የኦሕዴድ/ኢሕአዴግ ባለሥልጣናት ምንም ዓይነት ሕጋዊ እርምጃ አልተወሰደባቸውም። አርሶ አደሮቹም የወደመባቸው ንብረት ሊሰጣቸው ቀርቶ ተመልሰው እንኳን ሕጋዊ መሬታቸውን ለማልማት እንዳልቻሉ ነው የሚገልጹት። በተያያዘም በአፋር ክልል በአሳይታ ወረዳ ዋሙሌ ቀበሌ በስኳር ኮርፖሬሽን ለሸንኮራ አገዳ ልማት በሚል የቴምር ዛፍ የወደመባቸው ከፊል አርብቶ አደሮችን ሕይወት አመሰቃቅሏል። የተንዳሆ ስኳር ፕሮጀክት የነዋሪዎቹን ፈቃደኛነት ሳይጠይቅ ካሳም ሳይፈጽም ከ8300 በላይ የቴምር ዛፎች እንደተመጠሩና ነዋዎቹም ችግር ላይ መሆናቸውን ሰመጉ በ138 ልዩ መግለጫው