በወሊሶ ከተማ ተማሪው ገበሬው እና አጠቃላይ ነዋሪው ለለውጥ ባነሳው ተቃውሞ አንድ የስምንት አመት ልጅን ጨምሮ 8 ሰዎች መገደላቸውን የወሊሶ ነዋሪዎች ተናግረዋል::ከትላንትና ጀምሮ ብወሊሶ በተደረገው ተቃውሞ በከተማው ያለውን አስተዳደር ከማፍረስ ጀምሮ እስከ እስር ቤት ሰብሮ በግፍ የታሰሩ ንጹሃንን እስከማስለቀቅ ድረስ የተሳካ ስራ በሕዝቡ ተሰርቷል::ተቃውሞው የቀጠለ ሲሆን የአጋዚ ወታደሮችን የጫኑ ሰባት ከባድ መኪናዎች ወደ ቦታው ቢያመሩም በህዝቡ በተወሰደው የመንገድ መዝጋት እና የተቃውሞ መበርታት ወደ ከተማው መግባት አልቻሉም::
ይህ የሕዝብ ብሶት የወለደው ተቃውሞ ማንም የፖለቲካ ድርጅት ያልወልደው መሆኑ ሕዝቡ በጋራ እና በአንድነት ቆሞ በማሳየት ሃያልነቱን አስመስክሮበታል::ሕዝቡ ለአምባገነን እንደማይተኛ በተግባር አሳይቷል::በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚያደርሱ መንገዶች መዘጋታቸው የታወቀ ሲሆን እስካሁን አለመከፈታቸው ታውቋል::ተማሪዎችና አርሶ አደሮች ወደ ከተሞች የሚወስዱትን ዋና ዋና መንገዶች በትላልቅ ድንጋዮችና ግንዶች ዘጋግተዋል። የፌደራል ፖሊሶችና የወያኔ አጋዚ ቅልብ ወታደሮች እንደልባቸው ለመንቀሳቀስ ተቸግረዋል:: #ምንሊክሳልሳዊ