Photo :-Sudan Tribune
December 15, 2015

ከትናንት በስቲያ እሁድ ታህሳስ 3/2008 ዓም  በሱዳን አየር ኃይል ማዘዣተገኝተው ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት አልበሽር ሱዳን ወደ ወታደራዊ ቴክኖሎጂመሸጋገር አለባት ብለዋል።ከእዚህ በተጨማሪም እጅግ በፈጣን ሁኔታ የሱዳንንደህንነት ሊያስከብር የሚችል የአየር ኃይል መገንባት አለብን ብለዋል።የሱዳኑፕሬዝዳንት አገራቸው ለመከላከያ የምታወጣው በጀት በዝቷል የሚሉተቺዎቻቸውን በቁጣ ተናግረዋል።በመቀጠልም ”በዙርያችን ያሉ ፀጥታቸው የተናጋአገሮችን ተመልከቱ። የአገሪቱ በጀት 100% ለመከላከያ ቢውልምአይበቃንም።የእራሳችን የጦር መሳርያ ፋብሪካ ያስፈልገናል….እጅግ በፈጠነሁኔታ ትልቅ አቅም ያለው የአየር ኃይል መገንባት አለብን” ብለዋል ፕሬዝዳንትአልበሽር።በሌላ በኩል በሱዳን የእንግሊዝ አምባሳደር አሮን ”አሲያስ” ለተሰኘ ጋዜጣ ሲናገሩ ”የሱዳንን ዕዳ መቀነስ ፈፅሞ አይታሰብም።ምክንያቱም እስከ 70% በጀት ለመከላከያ እና ለፀጥታ ጉዳይ እንጂ ለሌሎች የልማት ዘርፎች እንደ ትምህርት፣ጤና ለመሳሰሉት አታወጣም።” ብለዋል።

ፕሬዝዳንት አልበሽር ባለፈው ሳምንት ጋምቤላ ኢህአዴግ/ህወሃት ”የብሔርብሔረሰቦች በዓል” የብሔር ብሔረሰቦች እስር ቤት ባደረጋት አገር  በከፍተኛ ደረጃየአገሪቱን ገንዘብ በሚያባክንበት ዝግጅት ላይ ተገኝተው ምሽቱን አዲስ አበባመመለሳቸው እና ከህወሃት ባለስልጣናት ጋር መገናኘታቸውን የሱዳኑ ”ሱዳንትሪቡን” መዘገቡ ይታወሳል።በአሁኑ ወቅት ህወሃት እና የሱዳን መንግስትየኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፎ በሚሰጥ እና ሕዝብን፣አገርንና ታሪክን በሚያዋርድመልኩ በኢትዮጵያ ላይ በጥምር ሴራ እየሸረቡ መሆኑ የአደባባይ ምስጢርነው።ህወሃት የኢትዮጵያ ህዝብን አንድነት በሚያናጋ መልኩ ጎሳ ከጎሳ የማጣላት እናከውስጥ ሆኖ ኢትዮጵያን የማዳከም ሥራ እየሰራ ለመሆኑን ብዙ እማኞችን መጥቀስይቻላል።በአገሪቱ ላይ የታወጀው የጎሳ ፌድራሊዝም ለ25 ዓመታትያክል  ኢትዮጵያን ሰላም የነሳ መሆኑ እየታወቀ እና ውጤቱም በኦሮምያ እናበሌሎች ቦታዎች የበለጠ ፀጥታ የነሳ መሆኑ እየታየ ለችግሩ የበለጠ ”ቤንዚንየማርከፍከፍ” ሥራ አሁንም በህወሃት እየተፈፀመ ነው።በሰሜን ጎንደር የ”አማራእና የቅማንት” ሕዝብ በሚል ሕዝቡን የመከፋፈል ‘መንግስታዊ የዘር ፍጅት’እንዲፈፀም መደረጉን እና እስካሁን ከአንድ መቶ በላይ  ሕዝብ ማለቁን ኢሳትራድዮ በታህሳስ 4/2008 ዓም ከአካባቢው ያነጋገራቸውን ነዋሪዎች ጠቅሶገልጧል።

የእዚህ የ”አማራ እና የቅማንት” ሕዝብ በሚል የመከፋፈል ሥራ ላይ የሱዳንየሞራልም ሆነ የገንዘብ ድጋፍ ከወያኔ ጋር ሊኖርበት እንደሚችል የብዙዎች ጥርጣሬነው።ሱዳን ሰፊ የሆነውን የኢትዮጵያ ለም መሬት እና ወንዞች ወደ ግዛቷ ለማካለለከህወሃት ጋር መስማማቷ እና ሰሞኑን ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚችል ሲገለጥ ነውየሰነበተው። ዛሬ ታህሳስ 5/2008 ዓም በዋሽንግተን ኢትዮጵያውያን በሱዳንኢምባሲ በር ላይ የድንበር ውሉን በመቃወም ትልቅ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደረግይታወቃል።
ጉዳያችን GUDAYACHN
ታህሳስ 4/2008 ዓም (December 15/2015)

Leave a Reply