የወያኔ አገዛዝ ለወዳጁ የሱዳን መንግስት ከኢትዮጵያ ድንበር ቆርሶ ለመስጠት ደፋ ቀና እያለ ባለበት በዚህ ወቅት ይህንን የድንበር መካለል በመቃወም በዋሽንግተን ዲሲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሱዳን ኤምባሲ ደጃፍ የተቃውሞ ድምጻቸው አሰሙ:: ሱዳን ሰላም ከፈለግሽ ዛሬ ከወያኔ ጋር የምታደርጊውን የድብቅ የድንበር ውል ማቆም አለብሽ ለድንበራችን ህይወት እንገብራ አንፈራም በማለት ሰልፈኛው ቁጣውን ገልጿል::


በሰልፉ ላይ የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ግንባር የዲሲ ግብረሃይል እና የሞረሽ ወገኔ ትወካዮች ንግግር አድርገዋል::
ድንበሩ ሲካለል ከ1200 ኪሎ ሜትር በላይ ግዛት እንዲሁም አፄ ቴድሮስ የተማሩበት የቋራው ገዳም እና አፄ ዮሃንስ የተሰዉበት የመተማ ከተማ ለሱዳን ተላልፎ ይሰጣል::#MinilikSalsawi

 

Leave a Reply