የወያኔ አገዛዝ በጀግኖቹ የኦሮሞ ተማሪዎች እና ገበሬዎች ላይ ይፋ ጦርነት አወጀ::ሁላችንም ከጀግኖቹ ጎን ልንቆም ይገባል::

የሕወሓቶች ምስጢራዊ ያሉት የተወጠሩበት ስብሰባ መጠናቀቁን ተከትሎ በወረደ ትእዛዝ መሰረት የወያኔ ጸረ ሽብር ግብረ ሃይል ገዳይ ቡድን በተቆጣጠረው ሚዲያ ላይ መግለጫ የሰጠ ሲሆን የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም ድምጻቸውን ያሰሙትን የኦሮሞ ተማሪዎች እና ገበሬዎችን በሙሉ በሽብር ድርጊት ላይ የተሰማሩ አሸባሪዎች በማለት የፈረጀ ሲሆን በቀጥታ ጦርነት አውጆባቸዋል::ከጦርነቱ ጎን ለጎን ጸጉረ ልውጥ ኦሮሚኛ ተናጋሪኦች በየከተማው አስርጎ በማስገባት በሌላው ብሄር ነዋሪዎች ላይ እርምጃ በመውሰድ ግርግር ፈጥሮ በመግደል እና በማፈስ ላይ ሊሰማራ ስለሆነ ሕዝቡ ይህንን አውቆ ከወያኔ እኩይ ድርጊት ራሱን ይጠብቅ ሲሉ ምንጮቹ አሳስበዋል::

እነዚህን ሰላማዊ ወገኖቻችንን የታጠቁ ወታደሮችን አዝምቶ በመግደል መሆኑ ሲታወቅ ሕዝቡም እምቢ ለመብቴ በማለት እየተጋፈጣቸው ይገኛል::የጸረ ሽብር ግብረ ሃይል እያለ ራሱን የሚጠራው ገዳይ ቡድን በሕዝቡ ላይ ከባድ ማስፈራሪያ በማድረግ ዜጎችን በገዛ አገራቸው ሽብርተኛ ብሎ በመወንጀል ጦርነት የከፈተ ሲሆን ነገን ከታሪክ ተጠያቂነት የማይድኑ የአገዛዙ መሪዎች/የጦር ወንጀለኞች ሀገሪቷን እያመሷት መሆኑን በተግባር እያሳየን ነው::

ይህ በእንዲህ እንዳለ በቡራዩ ውጥረቱ እንደቀጠለና የፌዴራል ፖሊስና የአገዛዙ ልዩ ኃይሎች ዲሽ በተሰቀለባቸው ቤቶች (በETV ምሬት ዲሽ ያልሰቀለ ስለማይኖር በየቤቱ ቢባል ይሻላል) እየገቡ ESAT የተሞላባቸውን እየመረጡ ቴሌቪዥኑንና ዲሹን እየወስዱ እንደሆነ ተሰማ። በዚህ ሂደትም የአካባቢው ፖሊሶች እንደተገለሉ ነዋሪዎቹ አያይዘው ገልፀዋል።እንደ አዲስ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ የምስራቅ ሀረርጌዋ አወዳይ በህዝብ ቁጥጥር ስርውላለች።በተደረገው ከተማዋን ከወያኔ የማስለቀቅ እልህ አስጨራሽ ትግል 3 ሰዎች መስዋዕትነትን ከፍለዋል።ሀረር መግቢያና ወደ ድሬዳዋ መገንጠያ መንገድ ሙሉ በሙሉ ተዘግቶዋል። ሁላችንም ከጀግኖቹ ጎን ልንቆም ይገባል::‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎OromoProtests‬ ‪#‎Freedom‬ ‪#‎Change‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Leave a Reply