በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 6ኪሎ ካምፓስ ተማሪዎች የነበሩ ሁለት ሴቶች ምሽቱን በደህንነቶች ከዶርማቸው ታፍነው መወሰዳቸው በግቢው ውስጥ ተቃውሞ አስነስቷል። አራት ኪሎ አካባቢ ያሉ መንገዶች በወያኔ የጸጥታ ሃይሎች ተዘግተዋል። በሰሜን አዲስ አበባ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል። በአሁኑ ሰዓትም ዩኒቨርሲቲው በፖሊሶች ዙሪያውን ተከቦ ይገኛል።

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር እንደዘገበው፤
መንግስት ህዝብ ሳያምንበት ማስተር ፕላኑን ተግባራዊ አደርጋለሁ በማለቱ ተቃውሟቸውን ያሰሙት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደማይከፋፈሉና በአንድነት እንደሚቆሙ በሰላማዊ ሰልፍ ገለፁ፡፡ ተማሪዎቹ ዛሬ ዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ ‹‹ለአንድነት እንቆማለን፣ አማራን እንወዳለን፣ ጉራጌን እንወዳለን፣… አንከፋፈልም…..›› ሲሉ ከሌሎች ጋር ግጭት ውስጥ እንደማይገቡና በአንድነት እንደሚቆሙ አሳውቀዋል፡፡ ቪዲዮውን ይመልከቱ↓

 

Leave a Reply