(ዘ-ሐበሻ) የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ አዘጋጅ ሆኖ በሃገር ቤት መረጃን ለሕዝብ ሲያደርስ የቆየው ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ዛሬ በደህንነት ኃይሎች ታፍኖ ተወስዶ መታሰሩ ተሰማ:: ከሃገር ቤት የመጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ሕወሓት የሚመራው መንግስት ሰሞኑን ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ በተነሳው የሕዝብ ቁጣ በመደናገጥ በርካታ አክቲቭስቶችን እያሰረ ይገኛል::

ኦህዴድን ጥርስ ያለው አንበሳ በማስመሰል በየሚዲያው እንዲነገር በማድረግ ሕዝቡን ያደናገረው ሕወሓት የሚመራው መንግስት በተለይ ሰሞኑን በኦሮሚያ የተነሳውን የሕዝብ ቁጣ ለማረጋጋት የኦህዴድ ባለስልናት እንደ አባዱላ ገመዳ ያሉት በየሚዲያው በማቅረብ የመንግስትን ፖሊሲ እንዲተቹ በማድረግና ከሕዝብ ጎን እንደቆሙ በማስመስል ፕሮፓጋንዳቸውን ከሰሩና ሕዝብን የማረጋጋት ሥራ በኋላ ቀስ በቀስ አክቲቭስቶችን ማሰራቸውን ቀጥለዋል::

ትናንት አቶ በቀለ ገርባ የታሰሩ ሲሆን እስካሁን ድረስም ከ3000 በላይ ሰው በዚሁ በኦሮሚያ ከተቀሰቀሰው የሕዝብ ቁጣ ጋር ተያይዞ ታስረዋል::

ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው መንግስትን በፌስቡክ እንዲሁም በነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ደባውን ሲያጋልጥ የቆየ ሲሆን በመጨረሻም ከቤቱ ወደ ሥራ ሊሄድ ሲውጣ ደህነነቶች እና ፖሊሶች አፍነው ወስደው ማዕከላዊ አስረውታል::

በሌላ በኩልም የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሆኑት ቴዎድሮስ አስፋው ከቤቱ እንዲሁም አቶ ዳንኤል ተስፋዬ ከፍርድ ቤት ታፍነው ተወስደው ታስረዋል::

Source   =   Zehabesha

 

 

Leave a Reply