ኦሮሚያ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ዩኒቨርሲቲዎችና ወለጋ ሆሮ ጉዱሩ ውስጥ ዛሬም ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ግጭቶች እንደነበሩ፣ ጉዳቶች መድረሣቸው ተሰምቷል፡፡

ሰሎሞን አባተ, ጃለኔ ገመዳእስክንድር ፍሬው

በሌላ በኩል ደግሞ “ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነች” ሲሉ ለቪኦኤ መግለጫ የሰጡት የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና የርስ በርስ ግጭት እንዳይነሣ እንደሚሠጉና ኦሮሚያ ውስጥ እየታየ ያለውን ሁኔታ ያነሣሣውና እያቀጣጠለ ያለው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳይ ብቻ ነው ብለው እንደማያስቡም አመልክተዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ እየታየ ባለው የሁከትና የግጭት ሁኔታ ተቃዋሚዎችን እየከሰሰ ያለው የገዥው ኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ተቃውሞውና የተከተሉትም የመቆራቆስ ምልልሶች ከተጫሩ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር ተገናኝቷል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Leave a Reply