ያስታወቁት የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ፣ ታኅሳስ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. መታሰራቸው ታወቀ፡፡
አቶ ዮናታን ታኅሳስ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. በመደበኛ የማስተማር ሥራቸው የጠዋቱን ክፍለ ጊዜ አስተምረው እንደጨረሱ ለዕረፍት ወጣ ብለው ሳይመለሱ መቅረታቸውን፣ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የቅርብ ጓደኞቻቸው ገልጸዋል፡፡
አቶ ዮናታን ያለወትሯቸው ለዕረፍት እንደወጡ ሳይመለሱ ቢቀሩም ብዙም ትኩረት እንዳልሰጡት የገለጹት ጓደኞቻቸው፣ አመሻሹ ላይ ቤተሰቦቻቸው በሞባይል ስልካቸው ሲደውሉ ዝግ እንደሆነ ነግረዋቸው የት እንደሄዱ ወይም አብረዋቸው ከሆኑ እንዲነግሯቸው ሲጠይቋቸው እነሱም መደናገጣቸውን ተናግረዋል፡፡ በጋራ ወደሚያውቋቸው ሁሉ ሲደውሉ ‹‹የለም፣ አላየነውም፣ አልተደዋወልንም…›› ከሚሉ መልሶች ውጪ ዓይተናቸዋል የሚል ሳያገኙ እንደቀሩ አስረድተዋል፡፡
አቶ ዮናታን ታኅሳስ 19 ቀን 2008 ዓ.ም. በፖሊሶች ታጅበው ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሄደው እንደነበርና ቤታቸው መፈተሹም ታውቋል፡፡ በምን ምክንያትና ለምን እንደታሰሩ ግን ገና አለመታወቁን፣ አሁን የሚገኙት በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ (ማዕከላዊ) መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
አቶ ዮናታን ከሰማያዊ ፓርቲ ለምን እንደለቀቁ በተለያየ ጊዜያት ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡