አለማየሁ አንበሴ

አራት ተማሪዎች ክፉኛ ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል

በዲላ ዩኒቨርስቲ ከትናንት በስቲያ ምሽት 3 ሰዓት ገደማ በተከሰተ የቦንብ ፍንዳታ የሁለት ተማሪዎች ህይወት ማለፉንና አራት ተማሪዎች በጽኑ መቁሰላቸውን ምንጮች ለአዲስ አድማስ ጠቆሙ፡፡
በዩኒቨርስቲው የኢንጅነሪንግ ት/ት ክፍል፣ ቤተመጽሐፍትና በተማሪዎች ማደሪያ ዶርም መካከል ባለ ቦታ ላይ ቦንብ  ሳይሆን እንዳልቀረ በተጠረጠረው ፍንዳታ፣ አንድ ተማሪ ወዲያውኑ ህይወቱ ሲያልፍ አንደኛው በአቅራቢያ ወደሚገኝ የጤና ተቋም ከተወሰደ በኋላ ህይወቱ ማለፉን ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡
በትናንትናው ዕለት የዩኒቨርስቲው አስተዳደርና የከተማው ፖሊስ አባላት በጉዳዩ ላይ የተወያዩ ሲሆን ፖሊስ አደጋውን እያጣራ እንደሆነ ታውቋል።
ከሁለት ሣምንት በፊት ከማስተር ፕላኑ ጋር በተያያዘ በዩኒቨርሲቲው ግቢ ተቃውሞ ተነስቶ ለሁለት ቀናት ትምህርት ከተቋረጠ በኋላ ዳግም መቀጠሉን ያስታወሱት ምንጮች፤ አምስት ተማሪዎች የዲስፒሊን ቅጣት ተላልፎባቸው ከዩኒቨርሲቲው መባረራቸውን ገልፀዋል፡፡

ምንጭ – አዲስ አድማስ

Leave a Reply