በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች ከጥር 6 እስከ ጥር 8 – 2008 የሚካሄድ ሕዝባዊ ተቃውሞ !!
#Ethiopia #AddisAbaba #FreedomVoice
=========== ተቃውሞዉ የሚገለፀዉ በኡኡታና በኳኳታ ይሆናል ። ==========
በተጠቀሱት ቀናቶች ሁላችንም በያለንበት ቦታ በመሆን የአገዛዝ ስርዓቱ በህዝብና በሃገር ላይ እየፈፀም ያለውን ወንጀል ፣ ህጋዊ ጥያቄ ባቀረቡ ዜጎች ላይ አየተወሰደ ያለዉን እስራት ና ግድያ ፣ የሃገራችን ድንበር ለሱዳን መንግስት ተቆርሶ መሰጠቱን እንቃወማለን ።
ኡኡታ ፦ ሁላችንም በያለንበት ( በመኖርያ ደጃፍ ፤ ጊቢ ዉስጥ ፣ በስራ ቦታ ፣ በመንገድ ላይ …..ወዘተ ኡኡታ ማሰማት )
ኳኳታ ፦ በአቅራቢያችን ድምፅ ማሰማት የሚችሉ ማንኛዉንም ነገሮች ማስጮህ ( ማብሰያ መመገቢያ ቁሳቁስ ፣ የቆርቆሮ የብረት አጥርና በር ፣ ተሽከርካሪዎች ፣ የተለያዮ ሰራዎች ማከናወኛ መሳሪያዎች ፣ በመንገድ በግርግዳ ተለጣፊ ወይም ተንጠልጣይ ማወስታወቂያዎች፣ የብረት ምሶሶዏችና ድልድዮች…….ወዘተ በመደብደብ በማጋጨት ማስጮህ )
እነዚህ ተግባራቶች በተመሳሳይ ሰዓት ከተለያየ ስፍራ ለመፈፀም የሚያመቹ ፣ አንድ ላይ መሰብሰብን የግድ የማይሉ ሲሆኑ ጨቋኙን የወያኔ ስርዓት ለማስዐገድ አንቅፋት የሆኑብንን ፍርሃትና መለያያትን በቀላሉ የምንሰብርባቸዉ እንዲሁም የእምቢተኝነት መግለጫዏች ናቸዉ።
የጊዜ ሰሌዳና ተግባር ፦
ጥር 6 ዐርብ ጠዋት 4 ሰዓት ከሰዓት በኃላ 7 ሰዓት ምሽት 2 ሰዓት ጀምሮ ከ 10-15 ደቂቃ ኡኡታ ….ኡኡታ
( የቀኑ መርሃ ግብር ከጁምዐ ሶላት በፊትና ሶላት ከተጠናቀቀ በኃላ ይሆናል )
ጥር 7 ቅዳሜ ጠዋት 4 ሰዓት ከሰዓት በኃላ 7 ምሽት 2
ሰዓት ጀምሮ ከ10-15 ደቂቃ ኳኳታ…..ኳኳታ
ጥር 8 እሁድ ጠዋት 4 ሰዓት ከሰዓት በኃላ 7
ሰዓት ጀምሮ ከ10-15 ደቂቃ ኡኡታ….ኡኡታ
( የቀኑ መርሃ ግብር የቤተክርስቲያኖች ፀሎት ከተጠናቀቀ በኃላ ይሆናል )
ጥር 8 እሁድ ምሽት ከ2 ሰዓት ጀምሮ ከ10-15 ኡኡታና ኳኳታ … ኡኡታ ኳኳታ በመቀላቀል እምቢተኝነታችንን ገልፀን የመጀመሪያዉ ዙር የተቃዉሞ መረሃ ግብራችን ይጠናቀቃል።
አስተባባሪ ኮሚቴው ።
==================== አንድ ነፃነቱን የሚወድ ኢትዮጵያዊ =================
ይህ ዘመቻ በቀን አንድ ብር እየጣልን #ለአንድ_ወር ይቆያል::የብር ተቃዉሞ በቀን 1 ብር ላይ ሁለታችን የተቃዉሞ ድምፃችን እናሰማ::
ሁሉም ነፃነት የናፈቀዉ በቀን አንድ ብር ላይ የሚከተሉትን በእስክሪብቶ ወይም በሀይላይት ማርከር የሚከተሉትን እየፃፈ ህዝብ በሚበዛባቸዉ ሁሉ እየጣለ ይዉጣ::
1. ወያኔ እንዲያቆም የምንፈልመልገዉን የተሰማንን በአጭሩ
2. መፃፍ ያለባቸዉ
##ወያኔ የአባቶቻችን ርስት ለሱዳን እንዳትሞክረዉ ዋ!
##በኦሮሞና አማራ ሶማሌ ወገኖቻችን ላይ ግፍክን አቁም ዋ! ዋ!
##መሬታችን ላይ እጅህን አንሳ!! በቃን ስልጣንህን ለህዝብ አስረክብ!! ዋ! ዋ!
##ፖሊስ ካድሬና ወታደር ወደቤተስብህ አብረህ ለነፃነት ቁም::
ዘረኛዉ ወያኔ በቃን:: የሚሉ ፅንሰ ሀሳቦችን እንጠቀም::
በምንችለዉ አቅም እንደየአቅማችን እናሳጥረዉ::
አንድ ብሩን ፅፈን ካዘጋጀን በሁዋላ ህዝብ የሚሰበሰብበት ቦታ ወስደን እንጣለዉ::
ይህን ተቃዉሞ ለቀጣይ ሰላሳ ቀናት… እንከዉን:: ነፃነታችን እስክናገኝ በተለያየ መልኩ ተቃዉሟችን ይቀጥላል::
ብሩን ጥሎ መሄድ ብቻ:: ብር ነዉና ማንም ያነሰዋል:: በነገራችን ላይ በወረቀት የብርን ኮፒ ፕሪንት መጠቀምም ይቻላል::
የሚጣልባቸዉ ቦታወች ህዝብ ቢያንስ ከአስር በላይ ከሚገኝባቸዉ እስከ ገበያ ሆስፒታሎች የማምለኪያ ቦታወች:: ገደብ የለዉም::
ተቃዉሞዉ ከሰኞ ጠዋት ከ25/04/2008 ጀምሮ ለአንድ ወር::