ሰሞኑ የኦሮሞ ህዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት በማድረግ የኦፌኮ_መድረክ ምክትል ሊቀ መንበር ኣቶ በቀለ ገርባ የሚገኙባቸው በመቶ የሚቆጠሩ ወጣቶችና ፖለቲከኞች እያሰረ መሆኑ፣ ትናንት ደግሞ የኦፌኮ_መድረክ ዋና ፀሓፊ ኣቶ በቀለ ነጋ ድብደባና ዛቻዎች እንደ ደረሳቸው ፤ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረው ወጣት ዮናታን ረጋሳና እንደ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው የመሳሰሉ የሰማያዊ ፖርቲ ወጣት ኣባላት እንደታሰሩ ይታወቃል።

ተረኛው የጅምላ እስራት የሚፈፀምባት ክልል ደግሞ ትግራይ እንደሆነች የህወሓት ከፍተኛ ኣመራሮች ተሰብስበው ውሳኔ ላይ መድረሳቸው መረጃው ደርሶናል።

የትግራይ መንግስት የእስራቱ ውሳኔ እንዲወስን ኣስገድደውኛል ብሎ የተወያየባቸውና የዓረና ወጣቶችና የፌስቡክ ኣክቲቪስቶች ኣስቀድሞ ካላሰረ በክልሉ ህዝባዊ እምቢተኝነት ሊያጋጥም ይችላል ብሎ ለመስጋት ምክንያቴ ብሎ ያቀረባቸው ነገሮች የሚከተሉት ናቸው።

፩) የወጣቶችና ሙሁራን ተጋሩ( የህወሓት፣ የዓረና ኣባላትና የፓርቲ ኣባልነት የሌላቸው ወጣቶች) ከፍተኛ የለውጥ ፍላጎት መኖር።

፪) የዩኒቨርስቲ፣ ኮሌጆችና ሁለተኛ ደረጃ ተመርቀው የስራ ኣጥነት ዕጣ እንደሚጠብቃቸውና የተስፋ መቁረጥ የወለደው ከፍተኛ የለውጥ ፍላጎት ማሳደር።

፫) የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ በመላ ትግራይ የመልካም ኣስተዳደር እጦት ዋነኛ ምንጭ መሆን፤ የሙስናና የፍትህ ማጣት ምክንያት መሆኑ።
የገጠር ወጣት ኣርሶ ኣደሮች በተለይ ከ40 ዓመት በታች ያለው መሬት ኣልባ በመሆኑ ከዓረና እየመጣ ያለው የመሬት ፖሊሲ ለውጥ ተቀባይነት እያገኘ መሄድ የወለደው ግፊት።

፬) በየከተማውና በየገጠሩ እየተጠራቀመ ያለው የዲግሪና የዲፕሎማ ምሩቅ ወጣት፣ በ10 12 እየወደቀ ያለስራ የተቀመጠው ወጣትና ወላጆች ከፍተኛ የለውጥ ፍላጎት መኖር።

፭) እየተባባሰ ያለው የኑሮ ውድነት፣ በየቦታው እየተበራከተ ያለው ዘረፋ( ሀንግ)፣ ስርቆትና ህገወጥነት እየተስፋፋ በመምጣቱና በህዝቡ እንቅስቃሴ ኣሉታዊ ተፅእኖ መፍጠር።

፮) በክልሉ ኣጋጥሞ ያለው ኣሰቃቂ ድርቅ ለ1.2 ሚልዮን ህዝብ ለረሃብ ከማጋለጡ በዘለለ ከፍተኛ የእርዳታ እጥረት በማጋጠሙና ከቁጥጥር ውጭ የመሄድ ኣዝማምያ መታየት መጀመሩ።

፯) ህወሓት ሙሉ በሙሉ ከህዝቡ መነጠል፦ ህወሓት ከትግራይ ህዝብ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ መነጠሉ ከ12ኛ ጉባኤው በኋላ እየተካሄደ ባለው የህዝባዊ ስብሰባዎች በግልፅ ቋንቋ ፊት ለፊት እየተነገረው ይገኛል። በጉባኤው ሂደትና ውጤት ከኣባላቱ ከፍተኛ ተቃውሞና በድርጅቱ ተስፋ መቁረጥ ኣስከትሎበታል።

ኣንድ ነባር የማእከላይ ኮሚቴ ኣባልና ከፍተኛ የክልሉ ስልጣን የተሾሙት ሴት ኣመራር ” ምነው በ12ኛ ለቴድሮስ ሓጎስና ለትርፉ ኪዳነማርያም የደረሳቸው የመውረድ እጣ ለኔ በሆነ ” ፀፀት የተሞላበት ምኞት ሲያሰሙና በወቅታዊ ሁኔታ ሲማረሩ ተሰምተዋል። እንደሚታወቀው ኣቶ ቴድሮስና ወይዘሮ ትርፉ (የኣቶ ኣባይ ወልዱ ሚስት) ከህወሓት ስራ ኣስፈፃሚ ኣባልነት ወደ ተራ ኣባልነት እንዲወርዱ መደረጋቸው የሚታወስ ነው)። ኣሁን የነሱ ውድቀት ለኔ በሆነ የሚል ሞኞትና እነሱም ሁሉም ነገር ለበጎ ነው የሚል ኣባባል በነሱ እንደደረሰ የተገነዘቡ ይመስላሉ።

እነኚህ በክልሉ ያሉ ኣስጨናቂ ክስተቶችና በሃገር ደረጃ ያለው ፖለቲካዊ ውጥረት እንዳይከሰት ኣስቀድሞ ለመከላከል የወጣው መላ የዓረና ወጣቶችና ተጋሩ የፌስቡክ ኣክቲቪስቶች ኣስቀድሞ ማሰር ነው።

በህወሓት 12ኛ ጉባኤ በርካታ የትግራይ የፌስቡክ ኣክቲቪስቶች በነ ኣቶ ኣባይ ወልዱ በከፈቱት የስም ማጥፋት ዘመቻ የተበሳጩት የኣሸናፊው ኣንጃ ኣመራሮች የፌስቡክ ኣክቲቪስቶች ኣይቀጤ ቅጣት እንደሚቀጡ ዝተው እንደነበር ይታወሳል።

ተሰብሳቢዎቹ የዓረና ወጣቶችና ኣክቲቪስቶች በማሰር ሃሳባቸው ልዩነት ሳይፈጥሩ ውሳኔ ላይ የደረሱ ሲሆኑ ለእስራቱ የሚሰጠው ምክንያት ግን ልዩነት ፈጥረዋል። በማሳሰርያ ምክንያት ላይ ሁለት መላዎች ቀርበው ነበር።

ሀ) ህገመንግስቱ ለመናድ፣ ህዝቡ ለዓመፅ በማነሳሳት፣ ኣሸባሪነት ወዘተ የሚሉ ለ24 ዓመታት ተቃዋሚዎች ያሳሰሩ ዝውቱር ክሶች እናቅርብ የሚል ቀርቦ ነበር።
ይሄ ሃሳብ የተለመደ ተግባር በመሆኑ በክልላችን ያልጠበቅነውና ያልታሰበ ተቃውሞ ሊያስነሳብን ይችላል በሚል ምክንያት ውድቅ ተደርገዋል። ህወሓት እነ ቐሺ ብርሃኑ ቖባዕ፣ ወይዘሮ ኣልጋነሽ ገብሩና ሌሎች የእግሪ ሓሪባ ኑዋሪ የዓረና ኣባላት ኣርሶ ኣደሮች በ”ኣሸባሪነት” እንደወነጀሏቸው ዓይነት መሆኑ ነው።

ለ) በደረቅ ወንጀል ከሶ ማሰር፦ ይሄ ሃሳብ መታሰር ኣለባቸው የተባሉት የዓረና ወጣት ኣባላትና ሌሎች ህወሓት የሚቃወሙ ተጋሩ ወጣት የፌስቡክ ኣክቲቪስቶች ደረቅ ወንጀል እንደሰሩ ኣስመስሎ በማቅረብ እስራቸው የፖለቲካ እስራት እንዳልሆነ በማስመሰል ሊነሳ የሚችለው ህዝባዊ ተቃውሞ መቀነስ የሚል እሳቤ ኣንግቦ የቀረበና ተቀባይነት ያገኘ ነው።

በዚህ መሰረት ይሄ እቅድ ተግባራዊ የሚደረገው ተፈላጊዎች ወደ ወንጀል እንዲገቡ በማድረግ፣ ካልሆነም የውሸት ደረቅ ወንጀል ክስ ኣቅርቦ በማስር ተገባራዊ ይደረጋል።

ስለዚ እያንዳንድሽ በ12ኛ የህወሓት ጉባኤ የነ ኣባይ ወልዱ የተቃወምሽ፣ የለውጥ ፍላጎት ያለሽና ሃሳብሽና ህወሓት የምትቃወሚ ትግራዋይ ሁላ ደረቅ ወንጀል ተዘጋጅቶልሻል።

በዚህ ስብሰባ ስለ ዓረና ፖርቲና እንቅስቃሴም ውይይት ተደርጎ ውሳኔ ቀርቦበታል።

1) የድርጅቱ ወጣት ኣመራሮች በደረቅ ወንጀል ከሶ ማሰር።

2) በዓረና ኣባላት የድብደባና ማስፈራርያ ዛቻዎች በማካሄድና በእያንዳዱ ኣባል ስጋት መፍጠር።

3) ከህዝብ የሚያደርጋቸው ግንኙነቶች ማስተጓጎል፦ ድርጅቱ በኣባላቱ እስራትና ድብደባ ምክንያት ራሱን ማጨናነቅ( ቢዚ ማድረግ)ና ስራው ማስተጓጎል።

4) ከዚህ የዘለለ የህግ ከለላ ተጠቅሞ ሰርጎ ገቦች በማዘጋጀት ማዳከም ብሎም ማፍረስ የሚሉ ወጥመዶች በዓረና_መድረክ ላይ እየተዘጋጁ ናቸው።

የህወሓት የደረቅ ወንጀል የፈጠራክስ ሲነገረኝ ኣንዲት ነገረኛና የጠብ ሱስ ያላት ሴት ፀሎት ትዝ ኣለኝ። ሴትዮዋ ጠብና ጠባጫሪነት ነጋ ጠባ የምትወድና በሱስ ደረጃ የሚያስቸግራት ሲሆን ” እዛ ማዶ ጠብ ያለበት ቦታ ጋር ኣድርሰኝ” ብላ ትፀልያለች።

እና ህወሓትም ጠብ ፍለጋ፣ ህዝባዊ ተቃውሞ ፍለጋ ህዝቡ ኣንድ ዓመት ድርቅ ሊቋቋም የማይችል የወደቀ ፖሊሲዋ ያስከተለው ረሃቡ እንዳይችል በነገር እየቆሰቆሰችው ትገኛለች።

የህወሓት መንግስት የዓረና ኣባላት በመሆናቸው ብቻና ህጋዊ መብታቸው በመጠየቃቸው ብቻ እንደ ኣብራሃ ደስታና ወይዘሮ ኣልጋነሽ ገብሩ የመሳሰሉ በርካታ ኣባላቶቹ በውንጀላ ታስረው ይገኛሉ።

 

Amdom Gebreslasie's photo.

Leave a Reply