ከአቢይ አፈወርቅ

prof-mesfin-sydny1ዕውቁ የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና ምሁር ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም ባለፈው እሁድ ኦክቶበር 26 ቀን በሲድኒ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጋር ደማቅ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ልዩ የምስጋና ስጦታም ተበርክቶላቸዋል። በዕለቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ተገኝተው አዳራሹ በመሙላቱ የተወሰኑ ታዳሚዎች ከፊትና ከኋላ ባሉ በረንዳዎች ላይ ተደርድረው ፕሮግራሙን ለመከታተል መገደዳቸው ይህ ሪፖርተር ተመልክቷል።

ፕ/ሩ ገና ወደ አዳራሹ ሲገቡ የተሰበሰበው ህዝብ በጭብጨባና እልልታ ነበር የተቀበላቸው። በአገር ባህል ልብስ ያሸበረቁ ህጻናትም የእቅፍ አበባ አበርክተውላቸዋል። እኚህ ባለፉት 3 ፈላጭ ቆራጭ አገዛዞች ውስጥ በማናቸውም ዓይነት አስጊ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነው ሳይቀር የሚያምኑበትን በድፍረት በመግለጽ የሚታወቁት የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች በልዩ ክብር ከተቀበሏቸው የሲድኒ ነዋሪዎች ጋር ለ3 ሰዓት ተኩል ያህል የዘለቀ ቆይታ አድርገዋል።

በመግቢያ ንግግራቸው ላይ ያለፉትን የህይወት ጉዞ በመጠኑ የዳሰሱ ሲሆን ስለ አገር ፍቅር፣ ስለመቻቻልና በተለይም በወቅቱ ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ እየፈጸማቸው ስላሉት አስከፊ ወን ሎች ሰፊ ትንታኔ ሰጥተዋል። ለ45 ደቂቃ ያህል የዘለቀውንና አዳራሹን ኮሽታ በማይሰማበት ‹ተመስጦ› ያሰመጠውን መሳጭ ንግግራቸውን ተከትሎ አጭር ዕረፍት ከተወሰደ በኋላ ለ2 ሰዓታት ያህል የዘለቀ የጥያቄና መልስ ፕሮግራም ተካሂዷል። በወቅቱ በርካታ ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን ፕሮፌሰሩም ዘና ብለው እያዝናኑና መንፈስን እያነቁ ሲመልሱ አምሽተዋል።

ፕ/ር መስፍን አዳራሹን ሙሉ ለሙሉ የተቆጣጠሩት ሲሆን በመግቢያ ንግግራቸውም ሆነ በጥያቄና መልስ ፕሮግራሙ ላይ ታዳሚውን የሚያስቁ ቀሎችን ጣል ከማድረግ  ምሮ በከፍተኛ ጭብጨባ የታ ቡ ጠንካራ መልዕክቶችም አስተላልፈዋል።

እንደዚህ ዘጋቢ ምልከታ ከሆነ እሁድ ሲድኒ ብርቁን የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቿን በከፍተኛ ክብር ተቀብላቸዋለች። ፕ/ር መስፍንም በርግጥም መከበርና መወደድ የሚገባቸው ብርቅዬ የአገር አባት መሆናቸውን በሞግች፣ መሳጭና አስተማሪ ገለጻዎቻቸው አሳይተዋል።

የሲድኒ ማህበረሰብን ወክለው ከ40 ዓመታት በፊት የፕ/ሩ ተማሪ የነበሩት ዶ/ር ብር ኑ ወ/ኪዳን ከትምህርት ቤት ትዝታቸው ተነስተው ስለ ፕ/ር መስፍን ያላቸውን ትውስታና ምስክርነት በሚያስደስት ሁኔታ አቅርበዋል። 2 የሲድኒ ነዋሪዎችም ግሩም ግጥሞች አቅርበዋል።

prof-mesfin-sydny2የፕ/ር መስፍን የአውስትራሊያ ጉብኝት ዓይነተኛ አላማ በህይወት ዘመናቸው የግል ምቾታቸውን ንቀው ለሚወዷት አገራቸውና ለህዝብ ጠበቃ ሆነው የከፈሉትን ዋጋና ያበረከቱትን አስተዋጽዖ ዕውቅና ለመስጠትና ምስጋና ለማቅረብ የታቀደ ሲሆን እርግጥም የሲድኒ ነዋሪዎች በቃላትም ሆነ በተግባር ፍቅር፣ አክብሮትና ምስጋናቸውን በወጉ ማቅረብ ችለዋል።

የተዘጋጅላቸውን በልዩ ዲዛይን የተቀረፀና የረጅም ዘመን አገልግሎታቸውን የሚዘክር ልዩ የህይወት ዘመን አገልግሎት ሽልማት በሲድኒ ነዋሪ የኢትዮጵያ ልጆች ስም ከኮሚኒቲው ፕ/ት ከአቶ አያሌው ሁንዴሳ እጅ ተቀብለዋል። በርካታ ሰዎች ምሽቱ እጅግ አስደሳች እንደነበር የተሰማቸውን ገልጸውልኛል። ይህን መሰል ‹የህይወት ዘመን አገልግሎት ልዩ ሽልማት› በሲድኒ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያን የተበረከተለት የመ መሪያው ኢትዮጵያዊ ፕ/ር መስፍን መሆናቸውንም ለመረዳት ተችሏል።

ፕ/ር መስፍን ለአንድ ሳምንት የዘለቀውን የሲድኒ ቆይታቸውን አጠናቀው  ሙስ ኦክቶበር 30 ቀን 2014 ዓ.ም፣ ወደ ሜልበርን ተመልሰዋል። ሜልበርን የሚገኘው ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ቡድን በሲድኒ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጋር በመተባበር ባቀረበላቸው ልዩ ግብዣ ወደ አውስትራሊያ የመጡት ፕ/ር መስፍን ቀደም ሲል በሜልበርን ተገኝተው ኦክቶበር 19 ቀን ደማቅ ህዝባዊ ውይይት ማካሄዳቸው ይታወሳል። በተመሳሳይ መልኩም በአዴላይድና በኦክላንድ (ኒውዝላንድ) ተገኝተው ከኢትዮጵያዊያን ጋር እንደሚወያዩ የተያዘው መር  ግብር ያስረዳል።

Leave a Reply