የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እስር ያሳስበኛል ብሏል
በኢትዮጵያ ሃሳባቸውን በነፃ የመግለፅ መብታቸውን በመጠቀማቸው ለእስር የተዳረጉ ጋዜጠኞች ከእስር እንዲፈቱ ሰሞኑን የአሜሪካ መንግስት ጥሪ ያቀረበ ሲሆን በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ የተፈረደበት የሶስት ዓመት እስር በእጅጉ ያሳስበኛል አለ፡፡
የአሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ መ/ቤት ባወጣው መግለጫ፤ ሃሳብን በነፃ የመግለፅና የፕሬስ ነፃነት የዲሞክራሲ አንኳር እሴቶች መሆናቸውን በመጠቆም፤ ዲሞክራሲያዊ ነኝ የሚል መንግስት ይህን መብት የማስከበር ኃላፊነት አለበት ብሏል፡፡
ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለውን የኢኮኖሚ ዕድገትና አፍሪካ ውስጥ ግጭቶችን ለመፍታት የምታካሂደው ጥረት በአርአያነት እንደሚጠቀስ መግለጫው አውስቶ፤ ይህንንም በመስከረም ወር ፕሬዚዳንት ኦባማ ከጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በተወያዩበት ወቅት በይፋ መናገራቸውን አስታውሷል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግስት፣ የታሰሩ ጋዜጠኞችን በመፍታት፣ ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብትንና የፕሬስ ነፃነትን የሚያስከብር አርአያነት እንዲያሳይ የአሜሪካ መንግስት ጠይቋል፡፡
የ “ፋክት” መፅሄት አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ የ “ፍትህ” ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በነበረ ጊዜ በተለያዩ ህትመቶችና ባወጣቸው ፅሁፎች “ህዝብን ለአመፅ አነሳስተሃል፤ ሃሰተኛ ወሬዎችን አሰራጭተሃል” በሚል በርካታ ክሶች እንደቀረቡበት የሚታወስ ሲሆን፤ ሰሞኑን የ3 ዓመት እስር የ10ሺህ ብር ቅጣት ተወስኖበታል፡፡ ጋዜጠኛው በጠበቃው አማካይነት ይግባኝ እንደሚጠይቅ አስታውቋል፡፡
ከስድስት ወር በፊት አንድ ላይ የታሰሩ ዘጠኝ ጋዜጠኞችና የኢንተርኔት ፀሐፊዎችን ጨምሮ፤ ኢትዮጵያ በአለም ደረጃ በርካታ ጋዜጠኞችን ለእስርና ለስደት በመዳረግ ተጠቃሽ ሆናለች በማለት አለማቀፍ የሰብአዊ መብትና የፕሬስ ነፃነት ተቋማት በተደጋጋሚ መንግስትን ይኮንናሉ፡፡
በጋዜጠኛነት ሙያው የታሰረና የተሰደደ ጋዜጠኛ እንደሌለ የሚናገረው መንግስት በበኩሉ፤ ጋዜጠኞች የታሰሩት የወንጀል ድርጊት ፈጽመዋል በሚል እንደሆነና ጉዳያቸው በፍ/ቤት ውሳኔ እንደሚያገኝ ይገልፃል፡፡
U.S. Deeply Concerned by Sentence of Ethiopian Journalist
Press Statement
Department Spokesperson
The United States is deeply concerned by the October 27 sentencing of Ethiopian journalist Temesgen Desalegn to three years in prison for “provocation and dissemination of inaccurate information.” Freedom of expression and freedom of the press are fundamental elements of a democratic society, and the promotion and protection of these rights and freedoms are basic responsibilities of democratic governments.
As President Obama stated during his meeting in September with Ethiopian Prime Minister Hailemariam, it is important that Ethiopia’s progress and positive example on economic development and regional conflict resolution extends to civil society as well. We urge Ethiopia to make similar progress with regard to respect for press freedom and the free flow of ideas and reiterate our call for the Ethiopian government to release journalists imprisoned for exercising their right to freedom of expression.