Bulldozers clearing Mursi land in Mago National Park, where communities are being evicted from their land to make way for sugar plantations.
© E. Lafforgue/SurAid donnervival

Representatives of some of Ethiopia’s biggest aid donors have announced that they will send a team to the southwest of the country to investigate persistent reports of human rights abuses amongst the tribes living there.

Survival International, the global movement for tribal peoples’ rights, has exposed how the tribal people of the Lower Omo Valley are being persecuted and harassed to force them off their land to make way for cotton, oil palm and sugar cane plantations.

Many other organizations have published similar reports.

The plantations are made possible by the Gibe III hydroelectric dam, which is itself the subject of huge controversy.

The dam, which is nearing completion, will have a serious impact on the livelihoods of 500,000 tribal people, including those living around Kenya’s Lake Turkana.

It is also projected to have catastrophic environmental consequences for the region, which is home to renowned UNESCO World Heritage sites on both sides of the border.

Survival and other NGOs have repeatedly denounced the eviction of hundreds of Bodi and Kwegu and continue to receive reports that people are being intimidated into leaving their lands for resettlement camps.

Daasanach are being forced off their land to make way for infrastructure development such as this giant pump at Omorate, which will facilitate irrigation of the plantations.

Daasanach are being forced off their land to make way for infrastructure development such as this giant pump at Omorate, which will facilitate irrigation of the plantations.
© E. Lafforgue/Survival

The Ethiopian government has not sought or obtained the indigenous peoples’ free, prior and informed consent to move from their lands, in breach of the guidelines for resettlement drawn up by the Development Assistance Group (DAG), a consortium of the largest donors to Ethiopia, including the US, the UK, Germany and the World Bank.

DAG provides significant financial assistance to the local administration responsible for the forced evictions.

DAG has decided to return to the Lower Omo later this year to investigate the situation, even though the evictions continue regardless of past donor visits, the findings of which have often not been published.

This decision follows mounting worldwide concerns. European parliamentarians from ItalyGermany and the UKhave asked questions in the European Parliament, and MPs in the UK and Germany have raised their concerns with various ministries. Parliamentary questions have also been tabled in the UK.

In February the US Congress ruled that US taxpayers’ money not be used to fund forced resettlements in Lower Omo.

Following a lawsuit brought by Friends of Lake Turkana, the Kenyan courts have ruled that the Kenyan government must release all information about the deals it has made with Ethiopia about buying electricity generated by the Gibe III dam.

Earlier this year, a UNESCO report recommended that Lake Turkana be inscribed on the List of World Heritage in Danger.

Share this news story

The Omo Valley tribes

A massive hydroelectric dam and associated land grabs for plantations threaten the tribes of the Lower Omo River

The tribes have lived in this area for centuries and have developed techniques to survive in a challenging environment.

They have not been consulted about the dam or the plantations and stand to lose their livelihoods based on the river’s natural flood cycle.

Act now ↓ Donate →

The Lower Omo River in south west Ethiopia is home to eight different tribes whose population is about 200,000.

They have lived there for centuries.

Young Mursi shepherds looking after livestock, Ethiopia.

Young Mursi shepherds looking after livestock, Ethiopia.
© Ingetje Tadros/ingetjetadros.com

However the future of these tribes lies in the balance. A massive hydro-electric dam, Gibe III, is under construction on the Omo.

When completed it will destroy a fragile environment and the livelihoods of the tribes, which are closely linked to the river and its annual flood.

Salini Costruttori, an Italian company, started construction work on the Gibe III dam at the end of 2006, and has already built a third of it. The government says over 50% has been built.

The Karo (or Kara), with a population of about 1000 - 1500 live on the east banks of the Omo River in south Ethiopia. Here, a Karo mother sits with her children.

The Karo (or Kara), with a population of about 1000 – 1500 live on the east banks of the Omo River in south Ethiopia. Here, a Karo mother sits with her children.
© Eric Lafforgue/Survival

However, China’s largest bank, the Industrial and Commercial Bank of China (ICBC), has agreed to fund part of the construction of the dam, and in 2012, the World Bank agreed to fund the power transmission lines.

After carrying out preliminary evaluation studies, both the European Investment Bank (EIB) and the African Development Bank (AfDB) announced in 2010 that they were no longer considering funding Gibe III.

In March 2011, the Ethiopian government withdrew its request for aid credit from the Italian government. The request had raised great concern amongst many Italian NGOs, which urged the Italian Foreign Minister not to support the controversial dam.

Survival and various regional and international organizations believe that the Gibe III Dam will have catastrophic consequences for the tribes of the Omo River, who already live close to the margins of life in this dry and challenging area.

 Download International Rivers Factsheet (PDF)

Land grabs and forced resettlement

In 2011 the government began to lease out vast blocks of fertile land in the Lower Omo region to Malaysian, Italian, Indian and Korean companies to plant biofuels and cash crops such as oil palm, jatropha, cotton and maize. It has started to evict Bodi, Kwegu, and Mursi people from their land into resettlement areas to make way for the large state-run Kuraz Sugar Project, which could eventually cover 245,000 hectares. The Suri who live west of the Omo are being forcibly resettled to make way for the ‘Koka’ oil palm plantation.

Communities’ grain stores and their valuable cattle grazing land have been destroyed. Those who oppose the theft of their land are routinely beaten and thrown in jail. There have been numerous reports of rape and even killings of tribal people by the military, who patrol the region to guard the construction and plantation workers.

The Bodi, Mursi and Suri have been told they have to give up their herds of cattle, a vital part of their livelihood, and may only keep a few cows in the resettlements, where they will become dependent on government aid to survive.

Hundreds of kilometers of irrigation canals will follow the dam construction, diverting the life giving waters to the plantations.

Download Human Rights Watch Report ‘What will happen if hunger comes’.

No environmental or social impact assessments of the impact of the plantations and irrigation scheme have been carried out, nor have there been any consultations with indigenous people.

Despite meeting Mursi and Bodi community representatives and hearing their accounts of serious human rights abuses, the UK and USA, the two largest donors to Ethiopia, have failed to investigate these allegations.

Download Oakland Institute’s Omo Land Deal Brief.

Ways of life

The Lower Omo Valley is a spectacularly beautiful area with diverse ecosystems including grasslands, volcanic outcrops, and one of the few remaining ‘pristine’ riverine forests in semi-arid Africa which supports a wide variety of wildlife.

Excited Hamar women blowing their horns and shouting taunts to the Maza men who will whip them. Women regard the scars as a proof of devotion to their husbands.

Excited Hamar women blowing their horns and shouting taunts to the Maza men who will whip them. Women regard the scars as a proof of devotion to their husbands.
© Ingetje Tadros/ingetjetadros.com

The Bodi (Me’en), Daasanach, Kara (or Karo), Kwegu (or Muguji), Mursi and Nyangatom live along the Omo and depend on it for their livelihood, having developed complex socio-economic and ecological practices intricately adapted to the harsh and often unpredictable conditions of the region’s semi-arid climate.

The annual flooding of the Omo River feeds the rich biodiversity of the region and guarantees the food security of the tribes especially as rainfall is low and erratic.

They depend on it to practice ‘flood retreat cultivation’ using the rich silt left along the river banks by the slowly receding waters.

They also practice rainfed, shifting cultivation growing sorghum, maize and beans on the flood plains. Some tribes, particularly the Kwegu, hunt game and fish.

Cattle, goats and sheep are vital to most tribes’ livelihood producing blood, milk, meat and hides. Cattle are highly valued and used in payment for bride wealth.

Tribal song from the Omo Valley. Recording by Daniel Sullivan.

They are an important defence against starvation when rains and crops fail. In certain seasons families travel to temporary camps to provide new grazing for herds, surviving on milk and blood from their cattle. The Bodi sing poems to favourite cattle.

Young Hamar boys painted with white ash, Omo Valley, Ethiopia. The Gibe III dam that is being constructed will destroy their people's livelihood.

Young Hamar boys painted with white ash, Omo Valley, Ethiopia. The Gibe III dam that is being constructed will destroy their people’s livelihood.
© Magda Rakita/Survival

Other peoples, such as the Hamar, Chai, or Suri and Turkana, live further from the river but a network of inter-ethnic alliances means that they too can access the flood plains, especially in times of scarcity.

Despite this co-operation there are periodic conflicts as people compete for natural resources. As the government has taken over more and more tribal land, competition for scarce resources has intensified. The introduction of firearms has made inter-ethnic fighting more dangerous.

No voice

For years the tribes of the Lower Omo Valley have suffered from the progressive loss of access to and control of their lands. Two national parks were set up in the 1960s and 1970s where they are excluded from managing the resources. Tourists can go on safari and hunt for game on tribal lands yet the tribal peoples themselves are banned from hunting. This has resulted in increased malnutrition.

A Hamar family sit outside their home, Omo Valley, Ethiopia. The Gibe III dam that is being constructed will destroy their people's livelihood.

A Hamar family sit outside their home, Omo Valley, Ethiopia. The Gibe III dam that is being constructed will destroy their people’s livelihood.
© Magda Rakita/Survival

In the 1980s, part of their territory was turned into a state-run irrigated farm and recently the government has begun leasing out huge tracts of tribal land to foreign companies and governments so that they grow cash crops including biofuels.

The tribal peoples who have been using the land for generations to grow their own subsistence crops and to graze their livestock, have had no say in the matter.

Although the Ethiopian Constitution guarantees tribal peoples the right to ‘full consultation’ and to ‘the expression of views in the planning and implementations of environmental policies and projects that affect them directly’, in practice consultation is rarely carried out fully and appropriately.

The Lower Omo Valley peoples make all public decisions after extensive community meetings among all adults. Very few speak Amharic, the national language, and literacy levels are the lowest in the country which means they have little access to information about developments which affect them.

Now the people live in fear – they are afraid of the government. Please help the pastoralists in southern Ethiopia, they are under big threat.OMO TRIBESMAN

USAID official who visited the Lower Omo in January 2009 to assess the impacts of the Gibe III dam reported that the indigenous communities knew either nothing or virtually nothing about the project.

With the aim of limiting debate on controversial policies and restricting awareness of human rights, the government published a decree in February 2009 stating that any charity orNGO which receives more than 10% of its funding from foreign sources (which is virtually every charity in Ethiopia) cannot promote human and democratic rights.

In July 2009, the Southern Region’s Justice Bureau revoked the licences of 41 local ‘Community Associations’, accusing them of not co-operating with government policy. Many observers believe the revocation is really an attempt by the government to stamp out discussion of and opposition to Gibe III.

Gibe III dam

In July 2006 the Ethiopian government signed a contract with the Italian company Salini Costruttori to build GibeIII, the biggest hydro-electric dam in the country. In violation of Ethiopia’s laws, there was no competitive bidding for the contract.

Kwegu men, fishing on the Omo River, Ethiopia.

Kwegu men, fishing on the Omo River, Ethiopia.
© Survival International

Work started in 2006 with a budget of 1.4 billion euros. Half of the dam has already been built and costs are escalating.

The dam will block the south western part of the Omo River which runs for 760 kms from the highlands of Ethiopia to Lake Turkana in Kenya. The Lower Omo Valley is a UNESCO World Heritage site, in recognition of its archaeological and geological importance. Here the Omo flows through the Mago and Omo National Parks, home to several tribes.

Ethiopian environmental law stipulates that an environmental and social impact assessment (ESIA) must be carried out before any project is approved. Despite this, the Ethiopian Environmental Protection Agency (EPA) approved the ESIA retrospectively, in July 2008, two years after construction work started.

The ESIA was carried out by an Italian company, CESI, and paid for by EEPCo (Ethiopian Electric Power Corporation) and Salini, raising questions over its independence and credibility. Its report, published in January 2009, found in favor of the project, stating that the impact on the environment and tribes concerned will be ‘negligible’ and even ‘positive’.

During dry periods the Nyangatom dig deep into the land in order to extract water. Kibish river bed, Ethiopia.

During dry periods the Nyangatom dig deep into the land in order to extract water. Kibish river bed, Ethiopia.
© Serge Tornay/Survival

According to independent experts, the dam, plantations and irrigation canals will have an enormous impact on the delicate ecosystem of the region by altering the seasonal flooding of the Omo and dramatically reducing its downstream volume. This will result in the drying out of much of the riverine zone and will eliminate the riparian forest. Indigenous people such as the Kwegu who rely almost exclusively on fishing and hunting will be destitute.

If the natural flood with its rich silt deposits disappears, subsistence economies will collapse with at least 100,000 tribal people facing food shortages. The potential for inter-ethnic conflict will increase as people compete for scarce and dwindling resources.

በኢንጂነር ይልቃል አምባገነናዊ መዳፍ ሥር የወደቀው ሰማያዊ ፓርቲ

Wednesday, 25 June 2014 13:03

       ታህሳስ 24 2004 ዓ.ም የሰማያዊ ፓርቲ መሥራች ጠቅላላ ጉባዔ የተካሔደበት ቀን ነው። በፕሮግራሙ ማብቂያ ላይ ከተጋባዥ እንግዶች መካከል ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም የመዝጊያ ንግግር እንዲያደርጉ ከመድረኩ ተጋበዙ። ቃል በቃል ባይሆንም እንዲህ አሉ። “በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ማሳካት ያቃተን ትልቅ ነገር ቢኖር ለሥልጣን ልጓም ማበጀት አለመቻላችን ነው። እዚህ ፓርቲም ለስልጣን ጥም ልጓም ማበጀት ካልቻላችሁ ይህ የስልጣን ጥም እያደር ይመጣል። . . ዛሬ አይደለም እያደር ይመጣል።” ብለው ነበር። እውነት ነው ጋሽ መስፍን፤ይሄ የስልጣን ጥም በሽታ አድሮ በሰማያዊ ፓርቲያችን መጥቷል። ነገር ግን ምነው ታዲያ ይሄ የስልጣን ጥም ልጓም እንዴት እንደሚበጅ ሳያሳዩን ቀሩ?!
በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ የግለሰቦች የሥልጣን ጥም መገራት ሳይችል ሲቀር የፖለቲካ ፓርቲዎች ስራ አምባገነኖችን ማምረት ይሆንና ጥሩ ግለሰቦችንና ድርጅቶችን ማጣታችን አይቀሬ ይሆና። በሰማያዊ ፓርቲም ውስጥ የተከሰተው ይሄ ነው። አንድ ቀን ነው ከኢ/ር ይልቃል ጋር ቢሮ ውስጥ የፓርቲው አባላት ስለሚያደርጉት ውስን ተሳትፎና በጥቂት የፓርቲው ሰዎች ላይ ስለወደቀው የሥራ ጫና ተቀምጠን እያወራን ነው። በመሀል በህይወቴ የማልረሳውን ነገር ምርር እያለ ነገረኝ። ‹‹አሁን እኔ አምባገነን ብሆን ምን ይፈረድብኛል? ለካ ሰዎች ወደው አይደለም አምባገነን የሚሆኑት ብቻቸውን የሚከፍሉት መስዋትነት ቢበዛ እንጂ!›› እኔ ግን ሰዎች እንዴት አምባገነን እንደሚሆኑ በራሱ በኢ/ር ይልቃል እና በሰማያዊ ፓርቲ አይቻለሁ። የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት በተደጋጋሚ ለፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በተለይም ለኢ/ር ይልቃል ጌትነት ህገወጥ የሆነ አሰራሩን እንዲያስተካክል ከዚህ በፊት የተሰሩ ስህተቶችንም እንዲያርም ቢያሳስብም ይሄን ተደጋጋሚ ማሳሰቢያ ችላ በማለት ወይም የፓርቲውን ምክር ቤትና አባላት በመናቅ በህገወጥ አሰራሩ ቀጥሎበታል። የፓርቲው አባላትም ነገሩን በሆዳቸው ይዘው ከዛሬ ነገ ስህተቱን ያርማል፣ ፓርቲውንም ወደ ትክክለኛ አሰራር ይመልሳል በሚል ተስፋ ቢጠብቁም ችግሩ እየባሰና ከቁጥጥር ውጪ እየወጣ ይገኛል። የፓርቲው አባላትም ለሶስት ዓመት ያክል በትዕግስት ከወያኔና ከፓርቲው ሊቀመንበር ህገወጥ አሰራር ጋር እኩል መታገላቸውንም ቀጥለዋል። የመሰታወት ቤት ላይ ድንጋይ አይወረወርም እንዲሉ የፓርቲው አባላት ባልጠነከረና ምንም አደረጃጀት በሌለው ፓርቲያቸው ላይ በአደባባይ ሃሳብ መወርወር ፓርቲውን ፍርስርሱን ያወጣው መስሏቸው ከወያኔ በላይ ራሳቸውን በራሳቸው አፍነው ነገሩን ወዲያና ወዲህ ሲሉት ከርመዋል። ሃሳባቸውን በአደባባይ አውጥተን እንግለጽ ቢሉ እንኳን ፓርቲውን እንደ ግል ንብረታቸው የሚያሽከረክሩት ጥቂት ግለሰቦች ጥርሳቸውን ስለሚነክሱባቸውና ከፓርቲው ስለሚያገሏቸው በብዕር ስም ለመጻፍ ይገደዳሉ። ለዚህ ማሳያም በቅርብ ለሰማያዊ ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተልኮ በነበረው የሰሜን አሜሪካ የጉብኝት ግብዣ እኔ ነኝ የምሔድ፣ እኔ ነኝ የምሄድ በሚል የስራ አስፈጻሚ አባል እስከማገድ ድረስ የዘለቀውን ግጭት በሰንደቅ ጋዜጣ የሰማያዊ ፓርቲ አባል በብዕር ስም ስለጻፈ ብቻ ሰማያዊ ፓርቲ እንዴት በአንድ እግሯ እንደቆመች ማየት በቂ ነው። ይህ አፈና ደግሞ ነገሩን እያለዘበው ሳይሆን እያባሰው ይገኛል።
ስለሆነም በፓርቲው ውስጥ ታፍነው ያሉ ሃሳቦችን ወያኔ የሚያውቃቸውን ነገር ግን ህዝብ የማያውቃቸውን የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች እንዲያውቁት እና እንዲወያዩበት የፈለኩትን እውነታ እንደሚከተለው በዝርዝር አስፍሬዋለሁ
1. በኢ/ር ይልቃል አማካኝነት በተለያዩ ሚዲያዎች ከተሰራጩ የሰማያዊ ፓርቲን አቋም የሚጻረሩ ሀሳቦች መካከል፣ ሰማያዊ ፓርቲ  በኢትዮጵያ ውስጥ ፓርቲ አለ ብሎ አያስብም፤ ከፓርቲዎችም ጋር አብረን አንሰራም የሚለው ይገኝበታል። ኢ/ር ይልቃል ይሄን የተናገረው ሰማያዊ ፓርቲ ሲመሰረት አንድነትና መኢአድ ፓርቲ ድራሻቸው ይጠፋል፣ ሰማያዊ ፓርቲ ደግሞ ብቻውን ነጥሮ ይወጣል በሚል የግሉ እሳቤ ነበር። ነገር ግን እሱ እንደተመኘው ሳይሆን ቀረና አንድነትና መኢአድ ካንቀላፉበት ተነስተው እንደገና አንሰራሩ። ይህ ብቻ እንዳይመስላችሁ፤ ኢ/ር ይልቃልን እንቅልፍ የነሳው ከሰማያዊ ፓርቲ አባላት የተነሳው ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር አብረን እንስራ የሚለው ጥያቄ መበርከቱ እንጂ። ታዲያ ለስለስ ባለ አነጋገር ሰማያዊ ፓርቲ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ከ ዶ/ር ነጋሶ ጋር ቡና እንደሚጠጣ ከኢ/ር ኃይሉ ሻወል ጋር ስልክ እንደሚደዋወል ይገልጽ የነበረው ወይም በማስመሰል ይገለጽ የነበረው ተቀይሮ በቁጣና በግልፍተኝነት ከሰማያዊ ፓርቲ በስተቀር ፓርቲ የለም፤ አንድነቶችም አምባገነናዊ አሰራር አላቸው። መኢአድ ቢሮው ብቻ ነው አፉን ከፍቶ የቀረው በማለት የሰማያዊ ፓርቲንና የሌሎች ፓርቲዎች ግንኙነትን በማሻከር የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ጥያቄን በማፈንና ተስፋ በማስቆረጥ ከፓርቲዎች ጋር አብረን እንስራ የሚሉትን የፓርቲውን ብዙሃን ጸጥ በማስባል በዙሪያው ባሰባሰባቸው ጥቂት ግለሰቦች አማካኝነት የሰማያዊ ፓርቲ ግንኙነት የባሰ እንዲሻክርና መልሶም እንዳያገግም በተለያዩ ጋዜጦችና በፌስቡክ አማካኝነት የጉንተላና የስድብ ዘመቻ አስከፈተ። በተለይ ደግሞ በአንድነት ፓርቲ ላይ (ልብ በሉ ይህ ዘመቻ የሚመራው በራሱ በይልቃል አማካኝነት ነው) ታዲያ ለምንድነው ከተወሰነ ጊዜ በሁዋላ በቀጥታ በራሱ አንደበት ሲሰነዘሩ የነበሩ ዘለፋዎችንና ጥላቻዎችን በተዘዋዋሪ በሌላ አባላት እንዲባሉ የፈለገው? የሱ ስም እንዳይጠፋ ነው? እኔ የፓርቲው አባላት አንድነትና መኢአድ ላይ ዘመቻ እንዲከፍቱ አላደረኩም ብሎ ይክድ ይሆን? እውነት እንደዛ ከሆነስ ለምን እሱ በሚመራው ፓርቲ ውስጥ ያሉ አባላት ከፓርቲው አቋም ውጪ በሆነ መልኩ ከሌላ ፓርቲ አባላት ጋር አፍእላፊ ሲካፈቱ ተዉ እኛ የራሳችንን ሥራ እንስራ ትግላችን ከወያኔ ጋር እንጂ ከአንድነት ፓርቲ ጋር አይደለም በማለት ፋንታ በተሳደቡት ቁጥር ልክ ውለታ የሚመስል ነገር ያደረገላቸው? ከሁሉም በላይ ደግሞ የሚገርመው በመሰዳደብ ሥራ ላይ በህቡዕ የመደባቸው ወጣቶችን እንደዚያ ሲያበረታታቸውና ሲደግፋቸው ምነው ሰማያዊ ፓርቲ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ለማደስ የሚሯሯጡ አባላት ላይ ጥርሱን መንከሱና እነሱን ከፓርቲው ለማባረር ወይም ከፓርቲው ለማራቅ ደፋቀና የሚለው? የምታስታውስ ከሆነ? አንድ የፓርቲ አባል ለምንድነው ሰማያዊ ፓርቲ ምንም አይነት ግንኙነት ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ግንኙነት እንዳይኖረው የምትፈልገው ብሎ ሲጠይቅህ ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ምን ፓርቲ አለ ብለህ ነው ነበር ያልከው›› እኔ ግን ትክክለኛ ምክንያቱን ልንገረው ከጠቅላይ ሚኒስትር ውጪ ምክትል ጠ/ሚም ሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመሆን እቅድ በጭንቅላታቸው የሌለው ኢ/ር ይልቃልና ጥቂት ጓደኞቹ ሰማያዊ ፓርቲ ከሌላ ፓርቲዎች ጋር ግንኙነት እንዲኖረው የማይፈልጉበት ምክንያት ይህ ግንኙነት እያደገ ሔዶ ወደ ውህደት ቢያመራ ኢ/ር ይልቃልና ጓደኞቹ በዛ ውህድ ፓርቲ ውስጥ የሥራ አስፈጻሚን ቦታ ላናገኝ እንችላለን፤ እንዲሁም ያን ውህድ ፓርቲ ልክ እንደ ሰማያዊ ፓርቲ በአንድ ጣታችን ላናሽከረክረው እንችላለን፣ ይህም ለስልጣን መወጣጫ የሆነውን መሰላላችንን ያሳጣናል በሚል ተልካሻ ምክንያት የሀገራቸውንና የህዝባቸውን ነጻነት ገና ባልመጣ ሥልጣን ስለለወጡት እንጂ! ልብ በሉ ሰማያዊ ፓርቲ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ያለውን ግንኙነት የሚፈጸመው በፓርቲው ምክርቤት ሆኖ ሳለ ኢ/ር ይልቃል ባልታዘዘውና እንዲያስፈጽም ባልተሰጠው የፓርቲዎች ግንኙነት ዙሪያ ባሰራጨው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ፓርቲው እጅግ ዋጋ ከፍሎበታል። ነገር ግን እውነታው በወቅቱ ሰማያዊ ፓርቲ በፓርቲዎች ግንኙነት ጉዳይ በፓርቲው ደንብና መመሪያ በሚያዘው መልኩ ይፈጸም ከማለት ውጪ ሌላ ምንም ዓይነት ውሳኔ እንዳላስተላለፈ እንዲታወቅ እፈልጋለሁ። ስለሆነም በታፈነው የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ስም እንዲህ እላችኋለሁ። እስከዛሬ በሰማያዊ ፓርቲ ስም ሲነገር የነበረው ሰማያዊ ፓርቲ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር አብሮ መስራት አይፈልግም የሚለው ሃሳብ በፍጹም ፓርቲውን የማይወክል ሃሳብ ሲሆን ሰማያዊ ፓርቲ ለኢትዮጵያችን ነጻነት የሚበጅ እስከሆነ ድረስ ውህደትን ጨምሮ በማንኛውም መልኩ ከፓርቲዎች ጋር አብሮ እንዳይሰራ የሚያግደው ምንም ምክንያት እንደሌለ እንዲታወቅ እፈልጋለሁ። በሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በኢ/ር ይልቃል ጌትነትና በአንዳንድ የፓርቲው አባላት እንዲሁም በወያኔ ሰርጎ ገቦች አማካኝነት ሲሰነዘሩ ለነበሩ ጉንተላዎችና መረን የለቀቁ ንግግሮች በ ሰማያዊፓርቲ ቅር የተሰኛችሁ የአንድነት የመኢአድ እንዲሁም የሌሎች ፓርቲዎች አባላትና ደጋፊዎችን የበደሉትን አይደለም፤ የበደሏቸውን ይቅር በማለት በሚታወቁት በሰማያዊ ፓርቲ አባላት ስም ይቅርታ እጠይቃችኋሁ። ይቅርታዬን ከተቀበላችሁኝ ዘንዳ ለ 23 ዓመት ረግጦ የገዛንን አምባገነን ቡድን ያለማንም አጋዥ እዚህ ጋር በቃህ እንደምንለው እርግጠኛ በመሆን ሰማያዊ ፓርቲን መስርተን ለሶስት አመታት ያህል ስንታገል ቆይተናል። ነገር ግን የወያኔን ለዓመታት የፈረጠመ ክንድ በጥላቻ የደደረ ልብንና በኢሰብዐዊነት የታሰረ ዓይኑን ታግሎ መጣል አይደለም፣ መግፋት ትልቅ ፈተና እንደሆነ አይተናል። በጀመርነው የትግል አማራጭም ሀገራችንን ነጻ ለማውጣት ምናልባት 20 እና 30 አመታት ሊፈጅ እንደሚችል ተገንዝበናል። ታዲያ እስከመቼ ነው መሬታችንን በሽፍቶች እያስቆረስን ስናሸጥ የምንኖረው? እስከመቼስ ህዝባችን በአምባገነናዊ ስርአት ታፍኖ ይኖራል? እስከመቼ ነው ወጣቶች በአቅመ ደካማ ወላጆቻቸው ሲጦሩ የሚኖሩት? እስከመቼ ነው እውነትን ያሉ ዜጎች ሲታሰሩ፣ ሲገደሉ፣ ሲሰደዱ የሚኖሩት? እስከመቼ ነው ጀግኖቻችን እንደበግ እየተጎተቱ እስርቤት ሲጋዙ የምንመለከተው? መቼ ነው ሃይማኖታችንን በነጻነት የምናራምድባት ሃገር የምንመሰርተው? ይሄን አምባገነን ቡድን ቀይረን በሰላም ውለን የምንገባባትን፣ ልጆቻችንን በነጻነት ት/ቤት ልክን ጥሩ እውቀት የምናስገበይባትን፣ ነግደን ምናተርፍባትን የሃገሪቷ ሃብት ፍትሃዊ በሆነ መልኩ የተከፋፈለባትን ለጥቂት አምባገነን ግለሰቦች የቆመ ሳይሆን ሃገሩን የሚወድ ለሀገሩ ዘብ የሚቆም የመከላከያ ሰራዊት የምንገነባበትን፣ ሃገራችንን እንድንመሰርት የሌሎችን ፓርቲዎች ትንፋሽ መዋስ ግድ ብሎናል። ከነገወዲያ ስለሚመጣው ሥልጣን ሳይሆን ነገ በሃገራችን ስለሚሰፍነው ነጻነት አብረን እንድንታገል ጥሪዬን አቀርባለሁ።
ሰማያዊ ፓርቲ አዲስ የኢትዮጵያ ህገመንግስት እያረቀቀ ነው፤ በአንድ ሳምንት ውስጥ ለውይይት ይቀርባል በማለት ኢ/ር ይልቃል ከተናገረ ዓመት ሊሞላው ነው። ነገር ግን እስካሁን ድረስ ለህዝብ ለውይይት የቀረበ ረቂቅ ህገመንግስት የለም። ታዲያ ለህዝብ ሊቀርብ የነበረው ረቂቅ ህገመንግስት የት ገባ? ነገሩ ወዲህ ነው፤ ሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የወደፊቱ የኢትዮጵያ ህገመንግስት በዚህ መልኩ ቢሆንስ በማለት ያዘጋጁትን የህገመንግስት ረቂቅ ዶሴ ሰማያዊ ፓርቲ እንዲወያይበትና ሃሳብ እንዲሰጥበት እንዲሁም እንዲያጠናክረው ወደ ሀገር ቤት ይልኩታል። ይህ ዶሴ በእጁ የገባው ኢ/ር ይልቃል ከፓርቲዎች ጋር የገባበት አጉል ቀድሞ ጎል የማስቆጠር ፉክክር አጣድፎት ኖሮ ከስራ አስፈጻሚ ጓደኞቹ ጋር ሳይመክር እንዲሁም የፓርቲውን ምክር ቤት ፍቃድ ሳይጠይቅ ሰማያዊ ፓርቲ አዲስ የህገመንግስት ረቂቅ አዘጋጅቷል በሳምንት ጊዜ ውስጥም ህዝብ ጠርተን ለውይይት ይፋ እናደርገዋለን ብሎ በሰንደቅ ጋዜጣ አወጀ። የፓርቲው የስራ አስፈጻሚና የምክር ቤት አባላትም እንደሌላው ህዝብ ሁሉ ከጋዜጣ አነበቡት፤ የጅብ ችኩል.. ይሉዋችኋል ይሄም አይደል? ህገመንግስት እንዴት እንደሚዘጋጅና እንደሚጸድቅ የማያውቅ ፓርቲና መሪ በሚልም ሰማያዊ ፓርቲ መሳቂያ መሳለቂያ ሆነ። ኢ/ር ይልቃልም ታዲያ እኔ ፓርቲ መምራት እንጂ ህግ ማወቅ አይጠበቅብኝም ብሎ ግግም አለ። ታዲያ ምን ነበረበት ቀድሞ ከጓደኞቹ ምክር ቢጤ ቢጠይቅ ኖሮ? ነገሩም ሁለተኛ እንዳይነሳ ተብሎ ተደባብሶ ቀረ። ይሄው አመት ሊሞላውም አይደል?
ሌላ ጊዜ ደግሞ የሙስሊሞች ጥያቄ ፖለቲካዊ እንጂ ሀይማኖታዊ አይደለም አለ። ኢ/ር ይልቃል ህግ አለማወቁ አይደለም የሚያስጨንቀኝ። ነገር ግን ሰማያዊ ፓርቲ ተወያይቶ ያላስተላለፈውን ሀሳብ ከየት እያመጣ እንደሚዘባርቅ እንጂ! የሙስሊሞች ጥያቄ ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ወይስ ሀይማኖታችንን ካለመንግስት ጣልቃገብነት እንምራ የሚል ጥያቄ ውስጥ አልገባም። ይሄን መቼም አንድ የሶስተኛ ክፍል ተማሪ ይመልሰዋል ብዬ እገምታለሁ። ይህ የኢ/ር ይልቃል አባባል ብዙ የሙስሊም እምነት ተከታዮችን ቅር ያሰኘ እንደነበረ አስታውሳለሁ። ነገር ግን በዚያኑ ሰሞን የሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ሃላፊ የሆነው አቶ ይድነቃቸው ከበደ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄ ፖለቲካዊ ሳይሆን ሃይማኖታዊ ነው በሚል ያቀረበው ግለ-ሀሳብ ኢ/ር ይልቃል የተናገረው የግሉን ሃሳብ እንጂ የሰማያዊ ፓርቲን አቋም እንዳልሆነ ለብዙዎች ግልጽ እንዲሆንላቸው ሆኗል። በወቅቱ በአቶ ይድነቃቸው ጽሑፍ ኢ/ር ይልቃል ቅሬታ እንደተሰማው በግል አጫውቶኛል።
ኦሮምኛ ቋንቋ በላቲን ሳይሆን በግዕዝ ነው መጻፍ ያለበትም አለ። አሁንም ኢ/ር ይልቃል ለምን የማያውቀውን ነገር ዝም ብሎ እንደሚናገር ባይገባኝም በአንድ መጽሄት ላይ የኦሮምኛ ቋንቋን ለመጻፍና ለማንበብ የሚያገለግለውን ቁቤን ኢህአዴግ የፈጠረው የሚያስመስልና ኦሮምኛ በግዕዝ ቢጻፍ የተሻለ እንደሆነ ተናገረ። ጋዜጠኛውም ቁቤኮ ኢህአዴግ ከመምጣቱ 30 ዓመት በፊት የተፈጠረ ነው፤ ሰማያዊ ፓርቲስ መቼ ነው የዚህ አይነት ውሳኔ ላይ የደረሰው ብሎ አልሞገተውም። የኢ/ር ይልቃል ንግግር ያቃጠላቸው የኦሮሞ አክቲቪስቶችም ጸረ ሰማያዊ ፓርቲ ዘመቻ እንዲከፍቱ ምክንያት ሆናቸው። ነገር ግን ይህ የሰማያዊ ፓርቲ አቋም አልነበረም።
አማራ የሚባል ብሔር የለም በሚል ኢ/ር ይልቃል በብዙ መድረኮች ለይ የፕ/ር መስፍንን አባባል እየተዋሰ ወይም እየቀዳ ሲናገር ገጥሟችሁ ይሆን ይሆናል። አማራ የሚባል ብሄር የለም ብሎ የተናገረውም ከጋሽ መስፍን በቀዳት አባባል ነው። ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም ፈላስፋ ናቸው። አማራ የሚባል ብሔር የለም ሲሉ ምክኒያታዊ በሆነ ትንተና ያቀረቡትን ጽሁፍ አይቼዋለሁ። ነገር ግን የአማራ ህዝብ ከቀዬው እየተፈናቀለ ነው፣ ከሀገሩ እየተሰደደ ነው ሲለን ይቆይና ወደ በኃላ ደግሞ አማራ የሚባል ብሔር የለም የሚለን ኢ/ር ይልቃል ለምንድነው አማራ የለም የምትለው ብላችሁ ብትጠይቁት የለም አልኳችሁ የለም ነው! ካላመናችሁኝ ፕ/ር መስፍንን ሄዳችሁ ጠይቋቸው ከማለት ውጪ ምንም አይነት ተጨባጭ ምክኒያታዊ ትንተና አያቀርብላችሁም። ለማንኛውም ሰማያዊ ፓርቲ አማራ የሚባል ብሄር የለም የሚል አቋም እንዳልያዘ እንድታቁልኝ እወዳለሁ።
2. የሰማያዊ ፓርቲ የቁልቁለት ጉዞ ለምን?
በአመት የ 26 ሚሊዮን ብር በጀት ያጸድቅ የነበረው ፓርቲ ካለምንም እቅድና በጀት መመራት መጀመሩ 60ና ሰባ ሺህ ህዝብ አደባባይ ይዞ ሰልፍ ይወጣ የነበረው ፓርቲ 400 እና 500 ሰው ይዞ መውጣቱ ሰማያዊ ፓርቲ የተያያዘውን የቁልቁለት ጉዞ የተመለከቱ ብዙ ሰዎች የራሳቸውን ግምት ሲወረውሩ ይስተዋላሉ። ነገር ግን ትክክለኛውን ምክንያት ይረዱ ዘንድ እንደሚከተለው በዝርዝር አስቀምጬዋለሁ።
ሀ. በ ኢ/ር ይልቃል አጉል ማበጥና ማናለብኝነት ቅር የተሰኙ ነባር የፓርቲው አባላት ፓርቲውን በሙሉ ልባቸውና በሙሉ አቅማቸው ማገልገል ማቆማቸው፣
ለ. በ ኢ/ር ይልቃል የሚመራው የሰማያዊ ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሰማያዊ ፓርቲ ለዓመታት ያክል እንደ ድርጅት ቀጥ ብሎ እንዲቆም የሚያስችል መሠረታዊ መዋቅሮችን መዘርጋት አለመቻሉ ለቁልቁለቱ ጉዞ ዋነኛ ምክንያቱ ነው ብዬ እገምታለሁ። ሰማያዊ ፓርቲ ከተመሰረተ ሶስት አመት ሊሞላው ነው። ነገር ግን በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ኢ/ር ይልቃል የመሠረተው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በአዲስ አበባ እንኳን አንድ ክፍለከተማ ማደራጀት አለመቻሉ አነጋገሪ ነገር ሆኗል፣
ሐ. በኢ/ር ይልቃል የሚመራው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መርህን የተከተለና ተጠያቂነት ያለበትን አሠራር መዘርጋት አለመፈለጉ (በተለይም በገንዘብና ንብረት አጠቃቀም ዙሪያ)፣
ኢ/ር ይልቃል ከ አንድነት ፓርቲ የወጣሁት ከፓርቲው ተባርሬ ሳይሆን በአንድነት ፓርቲ ውስጥ በነበረው መርህንና ህግን የጣሰ አሠራር ደስተኛ ባለመሆኔ ነው ይላል። አንድነት ፓርቲ ውስጥ ይባል የነበረው ህገወጥ አሠራር እውነትም ኖሮ ከሆነ ግን አሁን ሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ ከሰፈሰነው የረቀቀ ህገወጥ አሰራር አይብስም። ህገወጥ አሠራርን ተጠይፎ መርህ ይከበር ብሎ ከአንድነት ፓርቲ እግሩን ነቅሎ ከወጣ ሰው ግን አንድነት ፓርቲ ውስጥ አለ ከሚለው ህገወጥ አሠራር የረቀቀ ህገወጥ አሠራር ይገነባል ብሎ መገመት ደግሞ በጣም ከባድ ነበር። በአሁኑ ወቅት የሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ ስላለው ሚስጥራዊ አሠራርም ይሆን ግልጽ አሰራር ለማወቅና የስራው አካል ለመሆን ወሳኙ ነገር በፓርቲው ውስጥ የሚኖርህ የሀላፊነት ደረጃ ሳይሆን ለኢ/ር ይልቃል የምታሳየው የአጎብዳጅነት ደረጃ ነው። ይህም ጉዳይ ያሳሰባቸው የፓርቲው ኦዲትና ምርመራ ኃላፊዎች ይህ የሎሌነት ባህል እንዲቆም ለፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባላት በምክርቤት ስብሰባ ላይ አሳስበዋል። የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ግልጽነት ስለጎደለው የገንዘብ አጠቃቀምና አጠቃላይ አሠራር ጥያቄ ያነሱ እንደሆነም በፍጥነት በኢ/ር ይልቃል አማካኝነት ከፓርቲው የሥራ ሀላፊነታቸው ይታገዳሉ። በቦታቸውም የኢ/ር ይልቃል አጎብዳጅ ሎሌዎች ይተኩባቸዋል። ይሄም የኢ/ር ይልቃል ቀኝ እጅ ከሆነው የብሔራዊ ም/ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰኢድ ኢብራሂም ውጪ እውን አይሆንም ነበር።
የፓርቲዎችንም የገንዘብና የንብረት አጠቃቀም እንዲመረምር ሥልጣን የተሰጠው ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎች ከሚፈራርሱበት መንገድ ውስጥ ዋንኛው የሆነው የገንዘብ ጉዳይ እንደሆነ ስለሚያውቅ ነገሩን እያራገበ ዝም ከማለት ውጪ ምንም ዓይነት የማስተካከያ እርምጃ እንደማይወስድ ከበፊትም ጀምሮ ይታወቃል።
አንድን ድርጅት ድርጅት ከሚያሰብለው ነገር ዋነኛው የድርጅቱ መዋቅርና ውስጣዊ አሰራር ነው። ነገር ግን ሰማያዊ ፓርቲ መዋቅሩም ድርጅታዊ አሠራሩም አንድ ይልቃልና በዙሪያው ያሰባሰባቸው ግለሰቦች ሆነዋል። በአጠቃላይ ሰማያዊ ፓርቲ ከነበረው ድርጅታዊ አሰራር ወጥቶ ወደ ቤተዘመድ ማህበርነት መቀየሩ ለቁልቁል እድገቱ መሰረት ነው። የሰማያዊ ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በፓርቲው ብሔራዊ ም/ቤት ተጠያቂነት ቢኖርበትም የስራ አሥፈጻሚ ኮሚቴው በተለይም ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ከራስ ጸጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ ድረስ የተነከረበት ህገወጥ አሰራር በፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት እንዳይጋለጥበት ፓርቲው ከተመሰረተ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ አንድም ዝርዝር የንብረት አጠቃቀም የፋይናንስና የስራ አፈጻጻም ሪፖርት ማቅረብ አልፈለገም። እስከዛሬ የቀረቡት ሁለት ሪፖርቶችም ከአንድ ገጽ ያልበለጡ ከስምንት መስመር ያላለፉ ናቸው። የመጀመሪያውን እቅድና ሪፖርት እንደምሳሌ ማየት እንችላለን። የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው ነባራዊ ሁኔታ እንዲሁም ከፓርቲው አቅም አኳያ ገምግሞ በአንድ አመት ውስጥ 26 ሚሊዮን ብር እንደሚሰበስብና 73 ሺህ አባል እንደሚመለምል በመላው የኢትዮጵያ ክፍለሀገሮችም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን እንደሚከፍትና አደረጃጀቱንም እንደሚዘረጋ በአመታዊ እቅዱ ላይ አስፍሮ ለብሔራዊ ም/ቤቱ እንዲያጸድቅለት ማቅረቡ የሚታወስ ሲሆን በዓመቱ መጨረሻ ግን የሰበሰበው 300 ሺህ ብር ሲሆን የመለመላቸው አባላት ቁጥርም ከ 980 አይበልጡም። ነገር ግን ኢ/ር ይልቃል በተለያዩ ሚዲያዎች 40ሺህ አባላት አለን ብሎ ህዝብን አታሏል። ወያኔን ታግሎ መጣል የሚቻለው ደግሞ ህዝብን በውሸት በመደለል ሳይሆን ባለው አባል ተጨባጭ ስራን በመስራት ነው ብዬ አስባለሁ። በአሁኑ ሰዓት አጠቃላይ የአባላቱ ቁጥር 4 ሺህ እንደሆነ አውቃለሁ። ኢ/ር ይልቃል ሰማያዊ ፓርቲን እየገደለው ቁልቁል እየቀበረው ይገኛል። አሁንም የሰማያዊን መዳከም ሊያምን አልፈለገም። 170 ሺህ ብር የወጣበት ሰላማዊ ሰልፍም 400 ሰዎች ብቻ ሲገኙም አልደነገጠም። አሁንም ከሰማያዊ በቀር ሌላ ፓርቲ አልተፈጠረም ማለቱን ቀጥሎበታል። ሰማያዊ ፓርቲ ሌሎች ፓርቲዎችን ጥሎ እያደገ ነው ይላችኋል። እንዴት፣ የታለ እድገቱ ብላችሁ ብትጠይቁ ደግሞ ይሄው የአለም አቀፍ አምባሳደሮች ጠርተው እያናገሩኝ፣ የእንግሊዝ አምባሳደር ምሳ እየጋበዘኝ ብፈልግ የአሜሪካ ቪዛ በ 30 ደቂቃ እያሰራሁ ይላቹሃል። ሰው ሁሉ መንገድ ላይ ሠላም እያለኝ፣ አሜሪካ አገር እነሜሮን ጌትነት የሰለጠኑትን ዓይነት ስልጠና እየተጋበዝኩ ይላችኋል። የለም፣ የለም እኛ ያልነው የሰማያዊ ፓርቲን ዕድገት እንጂ የግል ስኬትህን አልጠየቅንህም ብትሉት ሰማያዊ ፓርቲን እንደ ግል ንብረቱ የሚያየው ኢ/ሩ ጓዴ ቱግ ቱግ ይላል። እኛ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሰፋ የሰማያዊ ፓርቲን አደረጃጀትና የትግል እድገት እንጂ የኢ/ር ይልቃል የግል ስብዕናና እድገት አንፈልግም።
3. ወያኔ አንድነት ፓርቲ እንዲጠፋ ከሚፈልገው በላይ ኢ/ር ይልቃል አንድነት እንዲጠፋ ይፈልጋል
ኢ/ር ይልቃል ሰማያዊ ፓርቲን የሚቀላቀሉ አዳዲስ አባላትን የሰማያዊ ፓርቲን ፕሮግራም ከማስተዋወቅ ይልቅ በአንድነት ፓርቲ ጥላቻ ይሰብካቸዋል። ምን እንደሚያስነካቸውም አላውቅ፤ እነሱም ጸረ አንድነት ፓርቲ ሆነው ሌሎችን መስበክ ይጀምራሉ። የአንድነት ፓርቲ አባላት በማህበራዊ ድረ-ገጾች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እየተከታተሉም ስድቡን ያጧጧፉታል። የዚህ አይነት ሰዎች ሎሌ ለመሆን ካላቸው አባዜ በመነሳት ብቻ እንጂ በውስጣቸው ምንም ክፋት ኖሮ አይደለም። አንድነትንም ለምን እንደሚቃወሙ ብትጠይቋቸውም ዓይናቸውን ከማጉረጥረጥ በቀር ምንም ምክንያት ሊነግሯችሁ አይችሉም። ኢ/ር ይልቃል ለወያኔ የአባልነት መዋጮ የሚከፍልበትን ደረሰኝ ከኪሱ ባላገኝም ለወያኔ ያለምንም ክፍያ የመከፋፈሉን ሥራ እያቀላጠፈለት እንደሆነ ግን ማየት ይቻላል።
• በሴቶች ታላቁ እሩጫ ሾላ አካባቢ የሚገኘው እስር ቤት ታስረው የነበሩ አባሎቻችንን ለመጠየቅ ሄደን ከእስር ቤት ስንወጣ እኔ፣ አቶ የሺዋስ አሰፋ(የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ም/ር ቤት ም/ል ሰብሳቢ) ኢ/ር ይልቃልና ዮናታን ተስፋዬ (የወጣቶች ጉዳይ ሰብሳቢ) ሆነን በአቅራቢያው ባለ አንድ ሬስቶራንት ተቀምጠን ፖለቲካችንን ስንሰልቅ በመሀል ኢ/ር ይልቃል ከተለያዩ የውጭ ሀገር አምባሳደሮች ጋርና ከተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የነበረውን ውሎ ፍንክንክ እያለ ሲተርክልን ቆየ። እኔም ያላንዳች መቼም እንዲህ እንዳልተፍነከነከ ገብቶኛል። ቢዘገይም እንዲያ ያፍነከነከውን ነገር አደራ ለማንም አይነገርም ብሎ እንዲህ ነገረን ‹‹ከቆየንበት ስብሰባ ስንበተን የመኢአድ ፕ/ት የሆኑት አቶ አበባው መሀሪ ወደኔ መጡና አንድነትና መኢአድ እያደረጉት ባለው የውህደት ጉዞ ደስተኛ እንዳልሆኑ፣ ውህደቱም ይሳካል ብለው እንደማያስቡ ነገሩኝ አለ።›› በሰአቱ የፓርቲዎች ውህደት መስተጓጎል በሚዲያ አልወጣም ነበር። እኔን ጨምሮ ብዙ ህዝብ የፓርቲዎችን ውህደት በጉጉት ስንጠባበቅ ስለነበር በሆዴ ይቺ ይቺ የፓርቲዎቹ ውህደት እውን እንዳይሆን ሌት ከቀን ደፋ ቀና ሲሉ የነበሩት የወያኔና የኢ/ር ይልቃል ምኞት ነች ብዬ አለፍኳት። ነገር ግን በሳምንቱ ጓድ አበባው መሀሪ በጋዜጣ ብቅ ብለው ጨዋታው ፈረሰ ዳቦ ተቆረሰ ብለው በሚዲያ ለፈፉ። ኢ/ር ይልቃል የነገረንም እውነት ሆነ። እሱም አላልኳችሁም፤ ውህደት የሚባል ነገር አይሰራም እኮ በሚል ሰማያዊ ፓርቲ ኩሽና ውስጥ ከበሮ አስደለቀ። ህዝቡም እርር ኩምትር ቅጥል አለ፣ እኔም እንደዚሁ።እንዲህ የሆንኩት ምንም እንኳን የሰማያዊ ፓርቲ አባል ብሆንም ወያኔን ታግሎ የሚጥል ትልቅ ፓርቲ ቢመሰረት ምኞቴ ነበርና ነው።
• ሰማያዊ ፓርቲ የ 33 ፓርቲዎችን ስብስብ ለምን መሠረተ?
በሰማያዊ ፓርቲ ሀሳብ አፍላቂነት በመድረክ በተለይም በአንድነት ፓርቲ አሰባሳቢነት የተመሠረተው የ33ቱ ፓርቲዎች ስብስብ አላማ የወያኔ መጠቀሚያ የሆነው ምርጫ ቦርድ ነጻና ገለልተኛ የሆነ ምርጫ እንዲያካሂድ ለማስገደድና ካለ ምንም ቅድመሁኔታ የ33 ፓርቲዎችን ጥያቄ እንዲመልስ ለማድረግ ነበር። ከምርጫ ቦርድ ጋር የነበረው ጉዳይ ባይሳካም ፓርቲዎች ባንድለይ ሲቆሙ ሊፈጥሩ የሚችሉትን ሀይል አይተንበታል። ነገር ግን በኢ/ር ይልቃል ሌሎችን ፓርቲዎች የማንቋሸሽ ዘመቻ ያልተደሰቱት የ33ፓርቲዎች ስብስብ ፓርቲዎች ሰማያዊ ፓርቲ በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጠን እንፈልጋለን ብለው ቢጠይቁም ምንም ማብራሪያ ከሰማያዊ ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባለማግኘታቸው ሰማያዊ ፓርቲን ከስብስቡ እንዲያግዱ ተገድደዋል። ሰማያዊ ፓርቲ ከስብስቡ ከመታገዱ በፊትና የ33ቱ ፓርቲዎች ስብስብ በተጧጧፈበት ወቅት ነው፤ እኔና ኢ/ር ይልቃል የቢሮው በር ተቆልፎብን በር ላይ ቆመናል። ይሄኔ የኢ/ር ይልቃል ስልክ ጠራ። የወቅቱ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ነበሩ ሰማያዊ ፓርቲ ምርጫ ውስጥ ገባ ተብሎ ሰምቼ ነው አሉት። ኸረ በፍጹም! አለ ኢ/ር ይልቃል። ብቻ አውርተው ስልኩ ተዘጋ። አየህ አንድነቶች ከኛ ጋር ያላቸውን ፉክክር አለኝ። እኔ እኮ ወደ ምርጫ ብንገባ አንድነትም ወደ ምርጫ ይገባል፤ እኛ ገና አቅም ስላልገነባን ይሄን ምርጫ በአድማ ብናልፈው የ2007 ምርጫ ላይ አንድነት ከኛ ጎን የሚቆምበት ትከሻ አይኖረውም ብሎ የውስጡን ጥላሸት አሳየኝ። በ2007 ምርጫ አንድነት፣ ሰማያዊ፣ መኢአድና አረና ፓርቲ ተዋህደው አዲሱን ቅንጅት እንደሚያሳዩን እገምታለሁ። ነገር ግን በዚህ አዲስ ውህደት ውስጥ ኢ/ር ይልቃል የልደቱን፣ ሰማያዊ ፓርቲ ደግሞ የኢዴፓን ሚና እንዳይተኩ እሰጋለሁ። በ1997 ለቅንጅት ፓርቲ መፍረስ ከመኢአድ ፓርቲ ወጥተው ኢዴፓን በመሰረቱ ግለሰቦችና በመኢአድ ፓርቲ አባላት መካከል የነበረው የማይሽር መቋሰል ዋንኛ ምክንያት ነበር። አሁንም ሰማያዊ ፓርቲ ኢ/ር ይልቃልን መስከረም ላይ በሚደረገው የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ መቀየር ካልቻለ የኢትዮጵያን የባርነት ጊዜ በአንድ ግለሰብ አማካኝነት ማራዘም ይሆናል። ከዘር፣ ከሀይማኖትና ከፖለቲካ አመለካከት የጸዳ የሀገር ፍቅርን ለልጆቻችን እናስተምር።

Leave a Reply