የግድያ ዛቻ በዓረና ኣባላት ላይ፥

**~*~*~*~*~*~*~**

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ራውያን ከተማ ኑዋሪ የሆኑት ኣቶ ሓዱሽ ገብረእግዚኣብሄር ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ስልክ እየደወሉ የግድያ ዛቻ እየደረሰባቸው ነው።

“ሰዎቹ ፅህፈት ቤቱ ዘግተህ ለመንግስት ይቅርታ ካልጠየቅህ በራስህ ሞት እንደፈረድክ ቁጠረው” የሚል ዛቻ እያደረሱባቸው ይገኛሉ።

ኣቶ ሓዱሽ ገብረእግዝኣብሄር ራውያን የሚገኝ የዓረና_መድረክ ፅህፈት ቤት ቤታቸው የሚገኝ በመሆኑና ራሳቸውም ኣባል በመሆናቸው በተደጋጋሚ ግዜ የግድያ ዛቻ እየደረሰባቸው ይገኛል።

የህወሓት ኣመራሮች በኣቶ ሓዱሽ ላይ ከሚያደርሱት ዛቻ በተጨማሪ በህጋዊ መንገድ ከ23 ዓመታት በፊት የተሰጣቸው፣ ህጋዊ ግብር እየከፈሉበት የመጡ፣ የባለቤትነት ደብተር እያላቸው፣ እያረሱት የቆየ መሬታቸው በመቀማት ለሌሎች ካድሬዎች ኣከፋፍለውታል።

ይህ የመሬት ቅምያ የተፈፀመው የዓረና_መድረክ ፅህፈት ቤት በቤታቸው ከተከፈተ በኋላ ነው።

ሌላ የዛቻና የፈጠራ ክስ የተፈበረከበት የራውያን ከተማ ኑዋሪ የሆነ ኣቶ ሓጎስ ኣፅበሃ ሲሆን “ህዝብ ኣሳድመሃል” የሚልና ሌሎች ክሶች ቀርበውበታል።

የህወሓት መንግስት በዓረና_መድረክ ንቅናቄና ህዝባዊ ድጋፍ ክፉኛ የደነገጠ መሆኑ የሚያረጋግጥ የሽፍታ ስራ ላይ ተሰማርተዋል።

የህወሓት መሪዎች በራውያን ፅህፈት ቤታችን ታፔላ በለሊት መጥተው በቀይ ቀለም ኣጥፍተውታል።
በፅሁፍ ላይ ቀለም በመጨመር እንዳይታይና እንዳይነበብ ኣድርገዋል።

Amdom Gebreslasie's photo.

ፅህፈት ቤቱ ሲከፈትም እኔ ዓምዶም ጨምሮ 17 ኣባላት ኣስረውን ነበር።

ከሳምንት በኋላም 6 ኣባላትና በፅህፈት ቤታችን ኣጠገቡብ ሻሂ ሲጠጡ የተገኙ 2 የኣከባቢው ኑዋሪዎች በማሰር በፅህፈት ቤቱ የተሰቀለው ባንዴራ ወስደውብናል።

ከዚ በፊትም በዞኑ ማይካድራ ከተማ ኑዋሪ የሆኑት ኣቶ ታደሰ ኣብራሃ የተለያዩ ዛቻዎች ሲያደርሱ ከቆዩ በኋላ በሰው እጅ ተገድለው ተገኝተዋል።
“መንግስት ግድያው ኣጣርቶ ወንጀለኛ ለፍርድ ያቅርብ” ብለን ስንጠይቅ ኣሻፈረኝ ማለቱ ይታወቃል።

የግድያ ዛቻ፣ የውሸት ክስ፣ ታፔላ ቀለም ጨምሮ ማጥፋት፣ ባንዴራ ቀምቶ መውሰድ ወዘተ የመሳሰሉ ወንጀሎች በህጋዊ መንገድ የሚታገል ሰላማዊ ድርጅት ዓረና_መድረክ መፈፀም ግሃድ ኣምበገነንነት ነው።

በምስሉ የምትመለከቷቸው የታፔላ ምስሎች የመጀመርያ ምስልና በቀለም ካጠፉት በኋላ ነው።

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

Leave a Reply