(ዳዊት ከበደ ወየሳ)
ስለበርናርድ (በርኒ) ሳንደርስ ብዙ ማለት ይቻላል። ጥሩ ሯጭ አትሌት ነበር። የሊብራል ሶሻሊስት ፓርቲን ከመሰረቱት እና ከመሩት ወጣት አሜሪካውያን አንዱ ነው። ከዚያም አልፎ ተርፎ በቬርሞንት ክፍለ ግዛት፣ የበርሊንግተን ከንቲባ እስከነበረበት ግዜ ድረስ ብዙ ታሪክ አለው። አሁን ደግሞ ዲሞክራት ፓርቲን በመወከል ከሂላሪ ክሊንተን ጋር ፍልሚያ ገጥሟል። ይሄን ሁሉ ነገር ወደ ጎን ትተን፤ ሰሞኑን ከቺካጎ አካባቢ ስለተገኘው አስገራሚ ፎቶ እናውጋ።
ፎቶው እንደአሜሪካ አቆጣጠር በ1963 ዓ.ም ላይ የተነሳ ነው። ይህ ፎቶ እስከቅርብ ግዜ ድረስ ለህዝብ ይፋ አልሆነም ነበር። ሰሞኑን በርኒ ሳንደርስ በወጣትነቱ በቺካጎ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበረበት ወቅት ያደርግ ስለነበረው እንቅስቃሴ በሰፊው ይወራ ጀመር። በዚህም ምክንያት ጋዜጠኞች ወደ ኋላ ተመልሰው በቺካጎ ትሪቡን ላይ የታተሙ ጽሁፎችን እና ፎቶዎችን ማየት ከመሩ። በርግጥም በርኒ በዚያን ወቅት እድሜው 21 ቢሆንም ለጥቁሮች እኩልነት የቆመ አክቲቪስት መሆኑን ተረዱ። ይህን የሚያረጋግጥላቸው ፎቶ ቢፈልጉ አላገኙም። ነገር ግን በጥቁር እና ነጭ ፊልም ተነስተው፤ ፊልሙ ጠቁሮ… ያልታጠቡና ያልታተሙ ምስሎችን አገኙ።
ከድሮዎቹ ፊልሞች መካከል አንዳንዶቹ ወረቀት ላይ ሲታተሙ፤ የአሁኑ በርኒ ሳንደርስ በወጣትነቱ ዘመን ስብሰባዎችን ሲመራ፤ እንዲሁም ለጥቁሮች ነጻነት ባደረገው ትግል ምክንያት መታሰሩን የሚያሳዩ ፎቶዎች ተገኙ። በርኒ ሳንደርስ በዚያን የተማሪነት ዘመኑ፤ የዘር መድልዎን የሚቃወመው የቺካጎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ኮንግረስ መሪ በመሆን አገልግሏል። ይህን በጥቁር አሜሪካኖችን ላይ የሚደረገውን አድልዎ በግልጽ መቃወም ብቻ ሳይሆን፤ ተማሪዎችን በመቀስቀስ ሰላማዊ ተቃውሞዎችን መርቷል።
በዚያን ዘመን… በ1963 የቺካጎ የትምህርት ሃላፊ የነበረው ቤንጃሚን ዊሊስ፤ ጥ

የጥቁሮች መብትት ተከራካሪው በርኒ ሳንደርስ በቺካጎ ፖሊሶች ተይዞ ሲወሰድ - 1963።

የጥቁሮች መብትት ተከራካሪው በርኒ ሳንደርስ በቺካጎ ፖሊሶች ተይዞ ሲወሰድ – 1963።

ቁሮች ወደ ነጮች መማሪያ እንዳያልፉ የሚከለክል የብረት አጥር ሲያሰራ፤ ብዙ ነጮች ያጨበጨቡለትን ያህል ጥቂት ነጮች ድርጊቱን ተቃውመዋል። ከነዚያ ጥቂት ነጮች መካከል የአሁኑ በርኒ ሳንደርስ አንደኛው ነበር። እናም በፊልም ማህደር ውስጥ የተቀመጡት ፊልሞች ሲታጠቡ፤ በወቅቱ ጋዜጣ ላይ ያልታተሙ የበርኒ ሳንደርስ ፎቶዎች ቁልጭ ብለው ወጡ። እነዚህ ፎቶዎች በቅርቡ ከታተሙ በኋላ በቺካጎ ዩኒቨርስቲ እና ሌሎች ተማሪዎች – ዘንድ መነቃቃት ተፈጥሯል።

ፎቶው ይፋ እንደወጣ፤ የበርኒ ሳንደርስ የምርጫ ዘመቻ ሃላፊ የሆነው ታድ ዴቪን እንዲህ ብሏል። “ፎቶውን ለበርኒ ስናሳየው፤ በትዝታ ወደ ኋላ ተመለሰ። እናም ‘አዎ በእርግጥም በፎቶው ላይ ያለሁት እኔ ነኝ’ አለን” ብሏል። በነገርዎ ላይ በርኒ ሳንደርስ በወቅቱ ጥቁሮችን በመደገፉ፤ ከታሰረ በኋላ $25 ዶላር እንዲከፍል ቅጣት ተጥሎበት፤ $25 ዶላር ከፍሎ ከቺካጎ እስር ቤት ተለቋል።
በቺካጎ… የሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ዝግጅቱን ከማደረጉ በፊት፤ በተለይ የቺካጎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተቃውሞ ለማድረግ በማህበራዊ ድረ ገጾች ሲነጋገሩ ነበር። እናም የታሰበው እና የተፈራው አልቀረም። በዶናልድ ትራምፕ ሜዳ ላይ፤ የበርኒ ሳንደርስን ፎቶ እና አርማ ይዘው “በርኒ! በርኒ! በርኒ!” እያሉ ሲጨፍሩ ተስተውለዋል። በአሁኑ ወቅት የቺካጎ ተማሪዎች “በርኒ ሳንደርስን እንደ ቼ ጉቬራ ወይም እንደ ማርቲን ሉተር ኪንግ፤ የማህበራዊ ደህንነት ትግል ያፋፋመ ጀግና ነው” እስከማለት እየደረሱ ናቸው። በቺካጎ የተቀጣጠለው እሳት ወደ አካባቢው ክፍለ ግዛቶች እየተዛመተ፤ በርኒ ሳንደርስ እየገነነ እንዲወጣ እያደረገው ነው።
በርኒ ሳንደርስ በ1960 ቺካጎ ዩኒቨርስቲ ገብቶ፤ በ1964 በፖለቲካ ሳይንስ የተመረቀ ሲሆን፤ እስካሁን ድረስ ከኪስ ቦርሳው የማይለየው ነገር ቢኖር፤ የቺካጎ ዩኒቨርስቲ የተማሪ መታወቂያው መሆኑን፤ ጋዜጠኞች በመገረም እያወሩ ናቸው። እናም ለአሜሪካ ፕሬዘዳንትነት እጩ ሆነው ከሚወዳደሩት፤ በእድሜ ሸምገል ያለው በርኒ ሳንደርስ፤ በወጣትነት ዘመኑ ታዋቂ ሯጭ አትሌት፤ የጥቁሮች መብት ተከራካሪ፤ የሶሻሊስት ፓርቲ መሪና በቬርሞንት ክፍለ ግዛት፣ የበርሊንግተን ከተማ ከንቲባ ነበር። ከሁሉም የሚገርመው ነገር ከሃምሳ አመታት በፊት፤ “ሃብታሞች የበለጠ ሃብታም፤ ደሃው ደሞ ይበልጥ እየደኸየ ነው። አብላጫው ህዝብ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ አይደለም። ይህን መለወጥ አለብን።” የሚለውን የሶሻል ዲሞክራት አስተሳሰብ አንድም ግዜ ለውጦ አያውቅም። ይህን አቋም በመያዝ ነው – አሜሪካን ለመለወጥ እጩ ፕሬዘዳንት ሆኖ ለውድድር የቀረበው – ሴኔተር በርናርድ (በርኒ) ሳንደርስ። መልካም እድል።

Leave a Reply