Saturday, 19 March 2016 11:00

Written by  አለማየሁ አንበሴ

      የአውሮፓ ኤምባሲዎች ከፓርቲ መሪዎች ጋር በሚያካሂዱት ውይይት፤ የሰማያዊ ፓርቲ መሪ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ በቅርቡ የተከሰቱ ግጭቶችንና ወቅታዊ ጉዳዮችን በመጥቀስ ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ መሆኗን እንደተናገሩ ገለፁ፡፡
የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ምክትል ኃላፊን ጨምሮ የእንግሊዝ፣ የጀርመን፣ የፈረንሳይና የሌሎች የአውሮፓ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች፣ በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ጥያቄዎች እንዳቀረቡላቸው ኢ/ር ይልቃል ጠቅሰው በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በወልቃይት፣ በደቡብ ኦሞና በኮንሶ ስላለው አለመረጋጋት ገለፃ ሰጥቻለሁ ብለዋል፡፡
በኦሮሚያ በተፈጠረው አለመረጋጋትና ግጭት፣ ከ260 በላይ ሰዎች መገደላቸውን በስም ዘርዝሬ  አቅርቤያለሁ ያሉት ኢ/ር ይልቃል፤ በወልቃይትም ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የሚደረጉ  ጥረቶች ለሀገሪቱ ጠቃሚ እንዳልሆኑ በኮንሶ፤ የአስተዳደር ጥያቄዎች በአግባቡ እንዳልተስተናገዱም መናገራቸውን ገልፀዋል፡፡
የሰማያዊና የመድረክ ፓርቲዎች በፀረ ሰላምነት ተፈርጀው ስለላ እንደሚካሄድባቸውና ብዙ አባላት እየታሰሩ መሆናቸውን የተናገርኩት በፍ/ቤት የሚቀርቡ ማስረጃዎችን በመጥቀስ ነው ያሉት የፓርቲው መሪ፤ በኢትዮጵያ የመድብለ ፓርቲ ፖለቲካ መዘጋቱንም  ገልጫለሁ ብለዋል፡፡
በድርቅ 18 ሚ. ህዝብ ለችግር እንደተዳረገ ያወሱት ኢ/ር ይልቃል፤ ኢህአዴግ ሀገሪቱን መምራት አልቻለም በማለት ብሄራዊ ውይይት እንደሚያስፈልግ መናገራቸውን ገልፀዋል

Leave a Reply