የሚሊዮኖች ድምጽ እንደዘገበው ከሁመራ በቅርብ እርቀት የምትገኘው በአከር ከተማ በደረሰን መረጃ ሕዝቡ በጉልበት አታስገድዱን እኛ ጎንደሬወች ነን በማለት ከሕወሃት ጋር ከትላንት ማምሻዉን ጀምሮ እንደተፋጠጡ ዘገባዎች ይጠቁማሉ። በአዲ ጎሹ በኩል ከትግራይ ወደ ወልቃይት የሚያስገባው አውራ ጎዳና እና እንዲሁም በተጨማሪ በዳንሻ በኩል ከሁመራ ወደ ጎንደር ፣ ከሰረቋ አርማጭሆ የሚወስዱት መንገዶች በሕዝቡ እስከ ትላንት ማምሻዉን ድረስ ተዘግተው ነበር።
ከአካባቢው የደረሰ መረጃ እንደሚጠቁመው በአገር ሽማግሌዎች ጣልቃ ገብነት ለጊዜው ከጎንደር ወደ ዳንሻ የሚወስደው መንገድ የተከፈተ ሲሆን፣ ይህ ከሽማግሌዎች ጋር የተደረገው መግባባት፣ ሕወሃቶች አፍነው የወሰዷቸውን የወልቃይት ማንነት ኮሚቴ አባላትን እንደሚለቁ ቃል ገብተው ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። ሆኖም ህወሃት በሕዝቡ ላይ የከፈተው የሽብር ተግባራት ካላቆመና ያሰራቸውን አያፈናቸው በአስቸኳይ ካልፈታ፣ በሽማግሌውች ተማጽኖ ለጊዜው የተከፈተው መንገድ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም በስፋት በማንኛው ጊዜ እንደገና ሊዘጉ እንደሚችሉ፣ ለአካባቢው ቅርበት ያላቸው የፖለቲክ ተንታኝ ይናገራሉ።
በወልቃይት ጠገዴ የተነሳው ተቃዉሞ፣ ሕወሃት የሕዝቡን ጥያቄ በማክበር በሰላም ካልፈታው፣ ወደ አልተፈለገ የለየለት የዘር ጦርነት እንደሚያመራና ከወልቃይት ጠገዴም አልፎም በቀላሉ ተቃዉሞው በሁሉም የአማራው ክልል ቦታዎች ሊዛመት እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ።
የዳንሻ ጎንደር መንገድ በሽማግሌዎች ተማጽኖ ቢከፈተም፣ የሰሮቋ አርማጭሆ መንገድ ግን እስከዚህች ደቂቃ ድረስ በሺ በሚቆጠሩ ገበሬዎች አማካኝነት እንደተዘጋ ነው!!