ከዛሬ 14 / 07 / 2008 ዓ/ም ረፋድ የጀመረው የባለ ባጃጆች ኣድማ “እንደ ሚኒባስ ታክሲዎች ታፔላ ኣበጅታቹና በስምሪት ብቻ መስራት ኣለባቹ” የሚል ኣዲስ ኣሰራር በመቃወም የተመታ ኣድማ ነው።

ዛሬ እሮብ መቐለ ከተማ ባጃጆች ምንም ዓይነት እንቅሴቃሴ ኣይታይባቸውም።

ከሁለት ሺ ኣምስት መቶ በላይ የሆኑት ባለ ባጃጆች “እምቢ ለመብቴ” ብለው በውሳኔያቸው ፀንተዋል።

መቐለ ከተማ ከፍተኛ የህዝብ ትራንስፖርት ችግር ተከሰቶ ይገኛል።

የዓረና የህዝብ ግኑኝነት ሓላፊው ዓንዶም ገብረስላሴና (Amdom Gebreslasie ) የድርጅቱ ፅህፈት ቤት ሓላፊ ዘነበ ሲሳይ (ZENEBE SISAY) በፖሊሶች ታስረው ተወስዶዋል፡፡ ከኣስር ደቂቃ በፊት የትግራይ ክልል ልዩ ሓይል ፖሊስ ለሁለቱም በመቐለ ወደ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ ተወስዷል፡፡

 

 

 

Leave a Reply