ፕ/ር /ጌታቸው ኃይሌ

Monday, 28 Mar 2016 10:35 PM

“የክርስቲያኖቹ መጽሐፍ “ግብር ለሚገባው (ሹም) ግብር ገብሩ” ይላል። ግብር ለማይገባው እንደወያኔ ላለ ገዢ ግን ግብር ስለማይገባው አንዲት ቀይ ቤሳ አታቅምሱት ማለቱ ነው። ጊዜ ስለሰጠው ቀምቶ ይወስዳል። ግን ብዕሬ ስቦኝ ነው እንጂ ለማለት የፈለግሁት እንኳን “አድናቆት ለሚገባቸው የኦሮምኛ ተናጋሪ የጎሳ ፖለቲከኞች አድናቆት ስጧቸው” ለማለት ነበር።

ታሪኩ እንዲህ ነው፤ ኢጣልያ ሰሜን ኢትዮጵያን ቆርሳ ወስዳ በቁራሹ ውስጥ ያሉትን የተለያየ ስም ያላቸውን ወረዳና አውራጃዎች ሰብስባ አንድ ራሷን የቻለች ሀገር ለማድረግ “ኤርትራ” የሚል ስም አወጣችለት። ከ1890 ዓ. እ. ጀምሮ ብዙዎቹ ክፍለ ሀገሮች አንድ ሀገር ሆኑ። ከኢትዮጵያ የመገንጠል ሐሳብ በውስጣቸው የሠረፀባቸው የዚያ አካባቢ ልጆች በአንድ ስም ለመጠራት አመቻቸው። ኢጣልያ ያንን አካባቢ ወስዳ አንድ ሀገር እስክታደርገው ድረስ ነዋሪዎቹን ከኢትዮጵያዊነት በቀር “ማን” የሚያደርጋቸው ሌላ ነገር ወይም ምክንያት አልነበራቸውም። በሀገር ደረጃ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ በጎሳ ደረጃ በየራሳቸው ስም የሚጠሩና ወደብዙ ጎሳ የሚዘረዘሩ ዘጠኝ ጎሳዎች ናቸው። አሁንም በዚያው ደረጃ አሉ። የኢጣልያ አገዛዝ ስማቸው ኢትዮጵያዊ ከመባል ኤርትራዊ ወደመባል ለወጠው እንጂ የውስጥ የጎሳ መታወቂያቸው እንዳለ ነው። ከኢጣልያ ግዛት ሲወጣና ከኢትዮጵያ ጋር ሲደባለቅ እልል ያለው ሕዝብ ስሙንም ሆነ መገንጠሉን መውደዱን ለማመን ያስቸግራል። ተደባብሶ ከዚህ ደረሰ እንበል። — [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—–

Leave a Reply