በዚያ የግፍ ዘመን ኢትዮጵያውያን ጀግኖች የሚዋጉት ሁለት ዓይነት ጦርነት ነበር፤ ከፋሽስት ወራሪ ኃይልና ከአገር ውስጥ ጎጠኞችና ጠባቦች ጋር። ጦርነቱ በፋሽስቱ ኃይል አሸናፊነት መጠናቀቁን ተከትል ኢትዮጵያውያን ማዕከላቸውን ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ጎሬ ከተማ በማድረግ ጦርነቱን ለመቀጠል ወጥነው በሚንቀሳቀሱበት ወቅትም ቢሆን በጅማና አካባቢው የጠባብ ብሔረተኞች ጥቃት አልተለያቸውም ነበር።2 በአማራ ሕዛብ ላይ በጣሉያኖች የተጀመረው ዘመቻ በዘመናችን መልኩን ቀይሮና ተሻሽል በ”አማራው ገዥ መደብ” ስም ተግባራዊ በመደረግ ላይ ነው። ኦነጎች ለሥልጣን በበቁባት አጭር ጊዜ ውስጥ ከሕወሓትና ሻዕቢያ ጋር ተባብረው በዚህ ህዝብ ላይ በበደኖ፣ በአርሲ፣ በወለጋና በሌሎች አካባቢዎች የፈጸሙትን ዘግናኝ እልቂት ማንም ሊረሳው አይችልም። እነዚህ ጠባብ ብሔረተኛ ድርጅቶች “ነፍጠኛ፣ ትምክህተኛ” ወዘተ. እያሉ የሚወነጅሉት “ገዥ መደቡን ነው” ይበለ እንጂ ዓላማቸው ምንና በማን ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ በጣም ግሌጽ ነው፡፡ ……. ( ሙሉውን ከዚህ ላይ ያንብቡ, pdf )
Source Welkait.com