ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ- የዘመናዊት ኢትዮጵያ አስተዳደር ቋሚ መሠረት ጣይ ፡- ዝክረ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ከልደት አስከ ሕልፈተ ሕይዎት።

ሞወዐድ (ማክሰኞ፣ መጋቢት ፲፫ ቀን፪ሽህ፰ ዓም) ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ (ልዩ ዕትም)

መግቢያ፦

ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ ለኢትዮጵያ ክብር፣ ነፃነት፣ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ማንነት ሲሉ፣ እጃቸውን ለእንግሊዝ ጦር መሪ ጄኔራል ናፒየር ከሚሰጡ ሞትን በመምረጥ ሽጉጣቸውን ጠጥተው ለኢትዮጵያዊነት ዳብሮ መቀጠል የተሰው ሰማዕት ንጉሠ ነገሥት መሆናቸው ዓለም ያወቀውና ያደነቀው አንጸባራቂ የታሪካችን አንዱ አካል ነው። ቴዎድሮስ ከእርሳቸው የነበሩት ንጉሦች መሠረታቸውን ይፋት፣ ሐረርና አዳል ባደረጉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ጋር ባደረጉት ተከታታይ ጦርነቶች፣ ተያይዞም ከግራኝ ጋር በተካሄደው እጅግ አውዳሚ አሥራ አምስት ዓመታት ያስቆጠረ ጦርነት፣ በኋላም የግራኝን እግር በመከተል በተከሰተው የጋላ (ኦሮሞ) ወረራ የሕዝቡ አንድነት ላላቶ፣ የኢኮኖሚ አቅሙ መድቀቅ የተነሳ በተፈጠረው ሁለንተናዊ ድክመት የተከሰተውን የዘመነ መሣፍት አገዛዝ ዘመን የተፈጠሩ የዚያን ወቅት ኅብረተሰብ ልጅ ናቸው። ቴዎድሮስ አገሪቱ በየአካባቢው የጦር አበጋዞች ተሸንሽና፣ የዘውዱ የአንድነት ምልክትነቱና የሥልጣን ምንጭነቱ ጥያቄ ውስጥ ወድቆ ከ70 ዓመታት ላላነሰ በዘለቀው «ዘመነፍዳ» የብላ ተባላ ዘመን፣ በቆራጥነት ታግለው፣ የአገሪቱን አንድነት ትናሣዔ ያበሰሩ ጀግና መሪ መሆናቸው ማንም ሊጠራጠረው ያልቻለ ሥብዕና ባለቤት ናቸው። ለዘመናዊ ኢትዮጵያ አስተዳደር ጽኑ መሠረት የጣሉ፣ ከሁሉም በላይ የዘውዱንና የንጉሠ ነገሥቱን መብትና ሥልጣ መልሶ ተገቢ ቦታውን እንዲይዝ ያደረጉ ራዕየ ሠፊ፤ ብልኅ፣ አስተዋይ፣ ቆራጥና ጀግና ንጉሠ ነገሥት መሆናቸው ይታወቃል።

ይህ ደረቅ ሐቅ ይሁን እንጂ፣ ኢትዮጵያውያን ባለመታደል ይሁን፣ ወይም በእርግማን፣ ወይም በሌሎች በቅጡ በማናውቃቸው ምክንያቶች ለትውልድ ተከታታይነትና ቀጣይነት በሚያገለግሉ መልካም ሥራዎች ላይ መጨመር፣ መልካም የሠሩ ሰዎችን ማሰብና ማሞገስ፣ ባህላችን ባለመሆኑ፣ የዚህ ጀግና መሪ ራዕይ ቀጣይነት አጥቶ፣ እርሳቸው በከፍተኛ መስዋዕትነትና ወደር በሌለው ጀግንነት የገነቡት አንድነት ዛሬ ከ156 ዓመት በኋላ ወደኋላ ተጉዘን በቋንቋ ልዩነት ከዘመነ መሣፍንት በከፋ መልኩ ተከፋፍለን ስንናከስ ማየት ከችግርነቱ አልፎ፣ ባህላችን እየሆነ መምጣቱ ከማሳዘን አልፎ ያሳፍራል ። በዚህ ሁኔታ ከቀጠልን ኢትዮጵያ እንደ አገር፣ ኢትዮጵያዊነት እንደ ዜግነት መታወቂያነት የመቀጠላቸው ሁኔታ ምንም ዓይነት ማስተማመኛ ነገር የለም። ይህ ልዩነት ካለበት ካሁኑ ሁኔታ ሠፍቶ፣ ኢትዮጵያውያን ለመግባባት እንደ አፍሪካ ኅብረት፣ ተመድ ስብሰባዎች አስተርጓሚ የሚያስፈልገን ብቻ ሳይሆን፣ ባንድ አዳራሽ ለመሰብሰብ የምንችልበት ሁኔታ ሩቅ እንደሆነ የልዩነት ጉዞአችን ፍጥነት አመላካች ነው።   ……. ( ሙሉውን ከዚህ ላይ ያንብቡ, pdf )

ምንች   ወልቃይት ዶት ኮም

 

One Response

Leave a Reply