Friday, 01 Apr 2016 07:45 PM

ተወልደ በየነ

መስከረም 27-1982 ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ(ህ ው ሀ ት) ጋይንት አውራጃ ነፋስ መውጫ ከተማን በተቆጣጠረ በሳምንቱ (ጥቅምት 3 1982 ዓም) በነፋስ መውጫ ከተማ ለብዙ አመታት የመብራት አገልግሎት ይሰጥ የነበረን የመብራት ጄኔሬተር ተነቅሎ ወደ ትግራይ እንዲሄድ የተወሰነበት ጊዜ ነበር ።
ይህንን ድርጊት ባስፈፃሚነት ካከናወኑት ሰዎች መካከል ደግሞ የከተማይቱ አስተዳዳሪ (በወያኔ የመዋቅር አጠራር ክፍለ ህዝብ) ጎሊያድ የሚባል ሲሆን በኃላ ላይ ኮሎኔል የመሆን እድል አጋጥሙት ከእነ ጀኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳኤ ጋር በክፍፍሉ የተባረረ ግለሰብ ነበር ።
ጎሊያድ ጄኔሬተሩን ለምን ወደ ትግራይ እንደሚያስጭን ሲጠየቅ በወቅቱ የሰጠው ምላሽ << ከ40ቀን በኃላ የያኔው ኢሂዴን የበኃላው ብአዴን 9ኛ የምስረታ በዓሉን በዚሁ በነፋስ መውጫ ከተማ ስለ ሚያከብር የተሻለ የመብራት ጀኔሬተር ልናመጣላችሁ ስለሆነ እስከ ህዳር 11-1982 ዓም ታግሳችሁ ጠብቁ በሚል ረጅም አመት ለንፋስ መውጫ ከተማ ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከምሽቱ 4ሰዓት የመብራት አገልግሌት ይሰጥ የነበረው ይህ ጀኔሬተር ጥቅምት 3-1982 ከምሽቱ በግምት 1:30 ተጭኖ ወደ ትግራይ እንዲሄድ ተደረገ።
ይህ ጄኔሬተር ረጅም አመት ግልጋሎት በሰጠበት ከተማ ስራውን ያከናውኑ ከነበሩ የመብራት ኃይል ሰራተኞች << እንግዳው ይባል ነበር።ጄኔሬተሩን የሚያበራው እና የሚያጠፋው <<እንግዳው>> ስለነበር 12.00ስዓት ላይ ሲያበራ <<እንግዳው ቦግ ያርግህ >> 4.00 ሰዓት ላይ ሲያጠፋ ድርግም ያርግህ >> የሚሉ ምርቃት እና እርግማን ይወርዱበት ነበር።

ወደ ጀመርኩት የነፋስ መውጫ ታሪክ ልመለስ ።የመብራት ጄኔሬተር ያጣችው ነፋስ መውጫ ከተማ በ19 87 እስከ 1988 ከባህር ዳር የኤሌክትሪክ ማመንጫ ወደ አድዋ አልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ከተዘረጋው የመብራት መስመር ተጠቃሚ ሳትሆን ተዘለለች ።የኃይል ማመንጫው ገመድ በላይ ላይ አልፎ እየሄደ እያየች ብርሃኗን ተነጠቀች ። ከጊዜ በኃላም ወደ ትግራይ የተዘረጋው የመብራት ምሰሶ እየወደቀ እና እየተሰረቀ በማስቸገሩ ምሰሶውን የሚጠብቅ ቡድን ሲቋቋም ከከትማ ኗሪ ከሆኑት የአገር ሽማግሌዎች አንድ ግለሰብ( በቅርብ የምናው
ቃቸው) የቡድኑ አባል የመሆን እጣ ይገጥማቸዋል ። ታዲያ ከቀናት በአንዱ የምሰሶ ጥበቃ ላይ እያሉ አንድ ወዳጃቸው ያገኛቸውና ምን እያደረጉ እንደሆኑ ሲጠይቃቸው <<ትግሬን ቆሜ እራት እያበላሁ >> ብለው መለሱለት ወደ ሰሜን ኢትዬጽያ በድሮ ዘመን መብራት ይዞ ቆሞ ማብላት ከቆዩ ባህሎች እንዱ ነበር ።
እኝህ አዛውንት ይህን ታሪካዊ ንግግር ካደረጉ ከ4 አመት በኃላ በተቀሰቀስው የኢትዮ -ኤርትራ ጦርነት የተዋጊ ጦር ምልመላና የሰው ኃይል ፍለጋ ወደ ጋይንት አውራጃ ያመራ የወያኔ ስብስብ ቡድን ስብሰባ ይጠራል ።

የስብሰባው አላማ <<ለሀገራቸው አንድነትና ለድንበራቸው መከበር የሚሰው ልጆቻችሁን መርቃችሁ እንድትሰጡ ለመጠየቅ ነው የመጣነው>>በሚል የቡድኑ ሰብሳቢ ንግግሩን ሲጨርስ እኝህ አባት እጃቸውን በማውጣት << እኛንማ እንደ መብራቱ ዝለሉን >>እንጂ የሚል አስገራሚ ምላሻቸውን ሰጡ ።

ምንች   ሳተናዉ

Leave a Reply