Friday, April 1st, 2016
ማርች 30, 2016
በኢሳት ድህረ ገጽ የሚጻፍ ወይንም በሬዲዮ የሚነገር በትምህርት ሰጪነት መልክ ሊቀረጽ ይገበዋል ከዛም አንባቢው ወይም ሰሚው ባነበበውና በሰማው ላይ በመንተራስ በተራው ሓሳብ ሊሰጥ በሚችልበት መልክ ያዘጋጀዋል ማለት ነው:: የሁሉም የጋራ ችግር በሆነው ጉዳይ ላይ መፍትሔ ልሆን የሚችል ነገር በመሻት ወይም በመጠቆም መልክ ህብረተሰቡም ተሳታፊ ከመሆን ባሻገር ሁሉም ከቀረበው ሐሳብ ጠቃሚ ትምህርት የሚገበይ ይሆናል:: ስለሆነም ለህዝብ አይንና ጆሮ ሆኖ እየሰራ ያለው የኢሳት ማእከልም የዚህ ተጠቃሚ ነው የሚሆነው የሚል እምነት አለኝ:: በአርእስትነት የተጠቀምኩበትን “እውን ኢሳት ( የእትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን) ልማታዊ ጋዜጤኛ ያሰፈልገዎልን?” የሚለውን ቃላት ልጠቀም የገፋፋኝ የወያኔ የኮምንኬሽን ሚንስትሮች ከሲቢል ሰርቢስ የጋዜጠኝነት ሞያ ያልተላበሱትን በገፍ እያስመረቁ ያንን የተከበረ ሞያ መዛበቻ እንዳደረጉት ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያውቀው የአደባባይ ሚስጥር የሆነውን ለመውቀስ አይደለም::
ከዛ ባሻገር በኢትዮጵያኖች ትብብርና ድጋፍ ተመስርቶና ለህዝባችን ዓይንና ጆሮ ሆኖ እያገለገለ ያለው ኢሳት ሰሞኑን በዋሽንግተን ዲሲ ጆርጅ ታውን መሪየት ሆቴል ከማርች 26-27 2016 የተዘጋጀውና በኢትዮጵያ የወደፊት ሁኔታ በለውጥ፥ ዲሞክራሲና፣ የብሄራዊ አንድነት ላይ የሚመክር ስብሰባ ከቪዥን ኢትዮጵያ ጋር በመሆን ያዘጋጀውን ፕሮግራም በተለያዩ ሚዲያዎችና ድህረ ገጾች ለህዝብ ይፋ ሆነው እኔም እንደማንኛውም የዜና ተከታታይ በመከታተሌ ነው:: ለኔም ሆነ ምናልባትም ለሌሎች ሰዎች ቭዥታ የፈጠረው ጉዳይ ግን ከሞያዊ ስንመግባር ያፈነገጠና የአግላይነት የአግላይነት ባሕሪ የተጎናጸፈ የዜና ቅንብር ማቅረቡ ነው:: ይህንን ለማለት ያስደፈረኝ ማርች 26,2016 በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለውይይት ድርጅቶቻቸውን ወክለው ከቀረቡት እንግዶች ውስጥ 1ኛ የኢትዮጵያ የጋራ ትግል ሸንጎ(ሸንጎ) 2ኛ የኦሮሞ ዴሞክርቲክ ግንባርና 3ኛ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ተወካዮች ነበሩ: እነዚህም የቀረቡ ሰዎች ከዚህ በፊት ባልታየና ባልተላመደ ሁኔታ በመከባበርና በመደማመጥ ይዘውት የቀረቡትን የድርጅታቸውን እምነትና አቆም ለተስበሳቢው ህዝብ በንግግር ካስደመጡ ቦሃላ ከተስብሳቢውም ህብረተሰብ የተለያየ ጥያቄ ተነስተው እነዚህ ድርጅታቸውን ወክለው የቀረቡ ሰዎች መልሳቸውን ሲመልሱ ተደምጠዎል::
ይህ ሆኖ ሳለለ የኢትዮጵያኖች አይንና ጆሮ ነኝ እያለ ከቀን ወደ ቀን እያደገና እየጎለበተ ያለው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን (ኢሳት)ከቆመለት አላማ ጋር የምጋጭና አግላይነት የሚታይበት ስራ ሲሰራ መመልከት በጣም ያሳዝነል ከማሳዘንም አልፎ ሞያና ሞያተኛ መቼ ነው የሚገናኙት ከዛም ባለፈ ከፖለቲካ ነጻ የሆነና አላማውና ተገባሮቶቹ የሚጣጠሙ ነጻ ሚዲያ በእኔ እድሜ ይፈጠር ይሆን ያስብላል:: እርግጥ ነው “ጎባጣ አለቃ ያለው ታዛዥ አጎንብሶ ይሄዳል ይባላል” ምክንያቱም “አለቃውን ለመምሰል”: የኢሳት እድምተኞችና ወዳጆች; በገንዘባችሁም ሆነ በጉልበት የምታገለግሉ ሁሉ ይህ ሰው ምን ለማለት ፈልጎ ነው ምን አላማ ኖሮት ነው ይህንን ሁሉ ቃላቶችን በዚህ ትልቅ ተቆም ላይ ትችት ሊሰነዝር የተነሳሳው ልትሉኝ ትችሉ ይሆናል? እኔም ይህንን ትችቴን የኢሳት የበላይ ተጠሪዎችና የበታች ሰራቶኞችን ለመውቀስ ያነሳሳኝ ከላይ እንደጠቀስኩት ማርች 26-27 /22016 ኢሳት ከቪዥን ኢትዮጵያ ጋር ሆኖ ያዘጋጀው ስብሰባ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን በተላያዩ ድህረ ገጾች በተጨማሪ በእራሱ በኢሳት ድህረ ገጽ ላይ እንዲ ሲል በአማርኛም በእንግሊዘኛም ዘግቦታል::
1ኛ “የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባት የስራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት ሌንጮ ባቲ፣ በመንግስት የሚፈጸሙ የኢሰብዓዊ ድርጊቶች በዝርዝር ካስረዱ በኋላ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድነት በመሆን በስልጣን ላይ ያለውን ኢህአዴግ መስወገድ እንዳለበት ተናግረዋል።”
2ኛ “በሃገሪቱ እየተፈጸሙ ስላሉ ኢሰብዓዊ ድርጊቶች ሰፊ ሪፖርትን ያቀረቡት አቶ ነዓምን የኢህአዴግ መንግስት ፌዴራላዊ፣ ዴሞራሲያዊ ወይም ሪፐብሊክ ተብሎ ሊፈረጅ እንደማይችል አክለው ገልጸዋል”
በእንግሊዛኛው ድህረ ገጹ ላይ ደሞ 1ኛ “Representing Patriotic Ginbot 7 for Unity and Democracy, Neamin Zeleke, a member of the leadership said the TPLF Federal Democratic Republic is neither federal, nor democratic, nor republic.”
2ኛ “Lencho Bati, member of the executive committee, Oromo Democratic Front spoke on the need to create a national and common discourse that brings together all political organizations” የሚል ዘገብ ተዘግቦ ተመልክቻለው::
በጣም የሚያሳፍረውና ዘጋቢውም ሆነ የዘጋቢዊ የቅርብ አለቆች የእውቀት ማነስ አሊያም ለኢሳት የሚሰሩት ሞያቸውን ወደውና አክብረው ሳይሆን አለቆቻቸውን ከማስደሰትና የሚኖሩበትን ቤት ክራይ ከመክፈል በላይ የዘለለ የሚያስቡ ሆነው አላገኞህቸውም:: ምክንያቱም የኢሳት ዘጋቢዎች ከወያኔ ልማታዊ ጋዜጠኖች ጋር የሚያመሳስላቸው ከሞያቸው አፈንግጠው ወጥተው አግላይና ፖለቲካዊ ሜና መጫወታቸው ነው ይህንንም ላማስጨበጥ ይህ ትልቅ ምሳሌ ነው::ከአቶ ሌንጮ ባቲ እና ከአቶ ነዓምን ዘለቀ ትንታኔ በፊትን ከመድረኩ ቀርበው ትንታኔቸውን ያቀረቡት እንግዳ ያቀረቡት አርእስት “የሽንጎው እይታና ራዕይ” የሚል ስሆን አንግዳውም አቶ አክሊሉ ወንዳፈረው ይባላሉ ታዲያ በኢሳት ዛጋቢ በአማርኛውም ዘገባላይ ያላቀረበው ምናልባት የግዜ እጥረት ሆኖ ይሆናል ብዪ አስቤ ወደ እንግሊዘኛው ገጹ ላይ ተሸጋገርኩ እዛ ላይም የሌሎቹ ውንድሞቻች ስምና ድርጅት ጠቅሶ ሲዘግብ የሽንጎው ስምና የተውካይ ስም ሳይዘግብ አልፎል: ይህ ሁኔታ ለቡዙዎቻችን በስማ በለው ስንሰማና ስናይ የነበረውን ወቀሳ በራሱ ስንፍና ራሱን ያጋለጠ ይመስለኛል::
በመጨረሻም ይህንን በስንት ሙርሃኖች ድካም የተለያዩትን ድርጅቶችና ሃሳቦቻቸውን ወዳንድ መስመር ለማምጣት የተደረገ ትልቅ ስብሰባ ዋጋ ማሳነስ ነው: ከአንድ ጋዜጠኛና ከአንድ ትልቅ የሚዲያ ድርጅት የሚጠበቅም አይደለም:: እኔ እንደምገምተው የቪዥን ኢትዮጵያ መስራቾችና የስብሳባው መሪዎች ይህንን ዓይነት ውይይት እንዲ ጀመር ሲነሳሱ አንዱና ትልቁ አላማቸው አግላይ የሆና ፖላቲካንና ፖለቲከኞችን እንዲሁም አግላይ የሆን ሚዲያን ከስር መሰረቱ አንዲጠፋ ይመስለኛል: የዶ/ር ጌታቸው በጋሻውን ቃለ ምልልስ በVOA የሬዲዮን ፕሮግራም ላይ ማርች 29,2016 ሳዳምጥ በድካማቸው ምን ያህል እንደ ተደሰቱ በመግለጽ ቀጣይ ፕሮግራም እንዲኖር ህዝቡ ፍላጎት እንዳለው አበክረው ተናግረዎል: ታዲያ ይህንን የእሳትን መረን የወጣ አሰራር ምን ያህል ይሆን ስሜታቸው የሚነካው? አብሮኝ ይሰራል የሚሉት የሚዲያ ተቆም ፖለቲካዊና አግላይ ገጸ በሃሪ ይዞ ሲገኝ:: ለማጠቃለል እኔ እንደ አንድ ተራ ግለሰብ የኢሳትን ማንጅንግ ዲያሪክተር (ቦርድ ኦፍ ዳሪክተርን) የምጠይቀው 1ኛ የቪዥን ኢትዮጵያ መስራቾችና የስብሳባው መሪዎች 2ኛ ሸንጎውና “የሽንጎው እይታና ራዕይ” ያቀረቡትን ግለስብ 3ኛ ክእረፍት ግዜቸው በመሻማትና ለቭዥን ኢትዮጵያ ባላቸው ትልቅ አክብሮት የመጡትን የስብሰባውን ታዳሚ በሙሉ ይቅርታ መጠየቅ ይገባቸዋል: ይቅርታውም ያለፈውን ዘገባ ባወጡበት ድህረ ገጻች በሙሉ እንዲሆን እጠይቃለው: ምክትያቱም ስህተት ተሰርቶ ሲገኝ ይቅርታ መጠየቅ መልመድ አለበት ያለበለዚያ ግን አምባ ገነንነት አብሮ የሚፈጠር ሳይሆን በሂደት የሚለመድ ነው:: ሌላው ደሞ ይቅርታ መጠየቅ “የቤትን ቅሻሻ ጠርጎ እንደማውጣት ነው” ይባላል ያ ሳይሆን ቀርቶ የኢሳትን ማንጅንግ ዲያሪክተር ከአፈርኩ አይመልሰኝ ብሎ ይቅርታ ካልጠየቀ በቆሻሻ ላይ ቆሻሻ እየከመረ ይሄድና የት ይደርሳል የተባለ የሚዲያ ድርጅት እንደ ግማል ሽንት… ከማለት የሚያግደው የለም ባይ ነኝ::
በመጨረሻም እኔም በጹሁፌ ስህተት ሰርቼ አንባቢን አስቀይሜ ከሆነ ከወዲሁ ይቅርታ እጠይቃለው::
ቸር ይግጠመን::
Source = ZeHabesha