በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ላይ ባለፈው እሁድ ተኩስ እንደነበር ታውቋል

በወታደራዊ ስልጠና ላይ የነበሩ ወጣቶች በወታደራዊ መኪኖች ተጭነው ያልፉ በነበረበት ወቅት አንዳንዶቹ ዘለው ለማምለጥ ሲሞክሩ የጸጥታ ሃይሎች ተኩስ እንደከፈቱባቸው ምንጮች ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ጠቁመዋል።

በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ላይ ባለፈው እሁድ ተኩስ እንደነበር ታውቋል። በወታደራዊ ስልጠና ላይ የነበሩ ወጣቶች በወታደራዊ መኪኖች ተጭነው ያልፉ በነበረበት ወቅት አንዳንዶቹ ዘለው ለማምለጥ ሲሞክሩ የጸጥታ ሃይሎች ተኩስ እንደከፈቱባቸው ምንጮች ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ጠቁመዋል።

የኤርትራ መዲና አስማራ ከተማ /ፋይል ፎቶ/

የኤርትራ መዲና አስማራ ከተማ /ፋይል ፎቶ/

በተኩሱና ተያይዘው በደረሱ ጉዳቶች የሞቱና የቆሰሉ ሰዎች እንዳሉ በተለያዩ የተቃዋሚዎች ሚድያ እየተገለጸ ነው። የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ስለሞቱትም ሆነ ስለቆሰሉት ሰዎች በነጻ ምንጭ ማረጋገጥ አልቻለም።

ስለ ጉዳዩ ከኤርትራ ባለስልጣኖች ምላሽም ለማግኘት ሞክረን አልተሳካልንም።

ፋይል ፎቶ - ወጣቶች በወታደራዊ መኪኖች ተጭነው እ.አ.አ. 2000

ፋይል ፎቶ – ወጣቶች በወታደራዊ መኪኖች ተጭነው እ.አ.አ. 2000

Source – VOA Amharic

The post በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ላይ ባለፈው እሁድ ተኩስ እንደነበር ታውቋል appeared first on ሳተናው .

Leave a Reply