የተመጣጠነ አመጋገብ
በዚህ ክፍል እንዴት ጤናማ እና አስፈላጊ የሆኑ ምግቦችን መብላት እንደሚችሉ እንጠቁምዎታለን፡፡ ጤናማ አበላል ከመጠነኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጋር እንዴት ሕይወትዎን እና ጤናዎን ማሻሻል እንደሚቻል እናስረዳዎታለን፡፡ እነዚህን ነጥቦች ከተከተሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጤናማ ተመጋቢ ሆነው ሕይወት እና በክብደት ላይ ለውጥ ማየት ይችላሉ።
የተመጣጠነ አመጋገብ ጤናዎን ከመጠበቁ በላይ ለአንዳንድ በሽታዎች እንዳይጋለጡ ይረዳዎታል፡፡ የተመጣጠነ አመጋገብ ማለት ፍራፍሬዎች፣ አትክልተና ጥራጥሬዎች በብዛት መውሰድ እና የስብ (ፋት) ኮሌስትሮል የበዛባቸውን ምግቦች መቀነስ ነው፡፡
እንደ አሜሪካ የዳየት ተቋም ገለፃ፣ ለጤና ተስማሚ የሆኑ ምግቦች ማለት የተለያዩ ፍራፍሬዎች፣ አትክልት፣ ፋት ያልበዛባቸው ሥጋና የዶሮ ዘሮች፣ ጥራጥሬዎች፣ ቅባት ያልበዛበት ወተት እንቁላልና ለውዝ ናቸው፡፡ እነዚህ ምግቦች የቅባት ይዞታቸው ትንሽ ሲሆን ሰውነታችን የሚፈልገውን ቫይታሚን እና ንጥረ ነገሮች የያዙ ናቸው፡፡ ጤናማ ያልሆኑ ምግቦች ደግሞ ብዙ ቅባትነት ያላቸው በርገሮች፣የድንች ጥብስ፣ ኬኮች ወይም በካርቶን የታሸጉ ትኩስ ምግቦች ናቸው፡፡ እነዚህ ምግቦች የሶዲየም ይዘታቸው በጣም ብዙ ነው፡፡
ጤናማ አመጋገብ ማለት የአመጋገብ ስልትዎን በብልሃት መወሰን ማለት ነው፡፡ ቅባት፣ ካሎሪና ሶዲየም ያልበዛባቸው ምግቦች በብዛት አላማዎት መሆን አለባቸው፡፡ ጤናማ አመጋገብ ማለት የሚመገቡትን የምግብ መጠንም ይጨምራል፡፡ በሚበሉት ሳህን ላይ የሚያስቀምጡት ምግብ ብዛት ያስተውሉና ይጠንቀቁ፡፡
አመጋገብዎን በተመለከተ እነዚህን ለመከተል ይሞክሩ
- የተለያዩ ዓይነት ምግቦች ይመገቡ
- የሰውነት እንቅስቃሴ ያድርጉ
- ስታርችን መሠረት ያደረገ ምግብ ዋና ምግብዎ ለማድረግ ይሞክሩ
- አትክልትና ፍራፍሬ በብዛት ይመገቡ
- ደረቅ ባቄላ፣አተር እና የመሳሰሉትን በየጊዜው ይመገቡ
- ሥጋ፣ዶሮ፣አሳ፣ወተት እና እንቁላል ሳይበዛ በየቀኑ መመገብ አይጎዳም
- ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች አልፎ አልፎ ብቻ ይመገቡ
- ጨው ይቀንሱ
- ውሃ በብዛት ይጠጡ (በቀን ከአራት እስከ ስምንት ብርጭቆ)
- መጠጥ አያብዙ