Written by  አለማየሁ አንበሴ

9 ኢትዮጵያውያን በደቡብ ሱዳን ስደተኞች ተገደሉ

           ከጋምቤላ ከተማ 14 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ጃዊ ስደተኞች ካምፕ የተጠለሉ ደቡብ ሱዳናውያን 9 ኢትዮጵያውያንን ከትናንት በስቲያ መግለደላቸው ተገለፀ፡፡ በስደተኞቹ ጥቃት የደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን በካምፑ ውስጥ በግምበኝነትና በቀን ሠራተኝነት ይሰሩ እንደነበረ ምንጮች ለአዲስ አድማስ ጠቁመዋል፡፡ ለግድያው ሰበብ የሆነው በአካባቢው የረድኤት ስራዎችን የሚሠራ ACF የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ተሽከርካሪ ሁለት ስደኞችን ገጭቶ ጉዳት በማድረሱ እንደሆነ ምንጮች ተናግረዋል። መንግስት በበኩሉ፣ በኢትዮጵያውያኑ ላይ የተፈፀመውን ግድያ እያጣራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በስደተኞች ካምፑ ከ270 ሺህ በላይ ደቡብ ሱዳናውያን ተጠልለው እንደሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
አዲስ አድማስ

Leave a Reply