በጋምቤላ ክልል 270ሺ በላይ የደቡብ ሱዳን ኑየር እና 7ሺ የሙሩሌ

ብሔር ስደተኞች በአኝዋክ ዞን በሚገኙ አምስት የተለያዩ የስደተኛ ጣቢያዎች ይገኛሉ።

የሰሞኑ አጀንዳ

ጋምቤላ‬
Gambella‬
.
~~ በጋምቤላ ክልል 270ሺ በላይ የደቡብ ሱዳን ኑየር እና 7ሺ የሙሩሌ ብሔር ስደተኞች በአኝዋክ ዞን በሚገኙ አምስት የተለያዩ የስደተኛ ጣቢያዎች ይገኛሉ።

~~ ከጋምቤላ ከተማ በ48ኪሜ በምትገፕው ኢታንግ ሁለት መጠለያዎች ሲኖሩ ከ80ሺ በላይ ስደተኞች ይገኛሉ።

~~ የዚህ ሳምንት (ሀሙስ)ግጭት የተነሳበት ከጋምቤላ ከተማ ወደ አዲስ አበባ መንገድ ላይ በ18ኪሜ ርቀት ላይ ብቻ በሚገፕውና በውስጡም 38,470 የኑየር ስደተኞችን በያዘው የጃዊ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ ነው።

~~ የግጭቱም መነሻ አንድ የACF የእርዳታ ሰጭ መኪና በሁለት ስደተኞች ላይ የሞት አደጋ በማድሱ ነው። አደጋውን ተከትሎ ከ11- 19 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ደገኞች በስደተኞቹ ኑየሮች ተገድለዋል። በጋምቤላ “ደገኞች/Highlanders” ማለት ፡ ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ እና የደቡብ ክልል ብሔሮች ማለት ነው።

~~ በጋምቤላ ዙሪያ ወረዳ በሚገፕው የጃዊ ካምፕ ከ12 በላይ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ለስደተኞቹ ከጋምቤላ ከተማ የተሻለ የውሃ አቅርቦት መስጠትን ጨምሮ እለታዊ የምግብ ፣ የጤና እና የት/ት አገልግሎቶችን ለስደተኞቹ ይሰጣሉ።

~~ በደቡብ ሱዳን ኑየር ስደተኞች ጥቃት የተቆጡ ደገኞች በጋምቤላ ከተማ “ሜንላንድ” አካባቢ በወሰዱት የአፀፍ እርምጃ ከ3 በላይ ኑየሮች ተገድለዋል። በጥቃቱ አኝዋኮችም ከደገኞቹ ጎን ቆመዋል። Mainland ማለት በዋነኝነት የኑየር ቢሔሮች የሚኖሩበት የከተማዋ ክፍል ሲሆን የደገኞቹ ወደ ጃዊ ካምፕ የበቀል ጉዞ በመከላከያ ሰራዊት እንዲቆም ባይደረግ በስደተኞቹ ላይ የከፍ አደጋ ይደርስ ነበር።

~~ ሁሉም NGOs ከጃዊ የስደተኞች ካምፕ የወጡ ሲሆን፤ ደገኞችም ከጋምቤላ ከተማ ማንኛውንም ለስደተኞቹ የሚደረግ አቅርቦት ውሀን ጨምሮ እንዳይደርሳቸው ላለፍት ሁለት ቀናት አድርገዋል። ክልከላውን የተላለፍ የእርዳታ ድርጅቶች መኪኖችና ቢሮዎች ላይም ጥቃት ሰንዝረዋል።

~~ የወቅቱ የጋንቤላ ፕሬዘዳንት Gateluak Tutkoat የኑየር ብሔር ተወላጅ መሆን ተከትሎ ነዋሪው በፕሬዘዳንቱ መኪና ላይ ጥቃት ፈጽሟል።

~~ ዛሬ (እሁድ) አመሻሽ ሁከቱ በመጠኑ ጋብ ያለ ሲሆን ፤ ተጨማሪ አራት መኪና የፌደራል ፓሊስ ዛሬ ከሰአት ወደ ከተማዋ ገብቷል።

~~ የስደተኞች ካምፕ በጣም ከድንበር ርቀውና ወደ መሀል ለከተማዋ እስከ 18ኪ.ሜ ቅርብ ሆነው እንዲገነቡ ቦታዎችን ያመቻቸው የወቅቱ የኑየር ተወላጅ ፕሬዘዳንት ላይ ብዙ ጥያቄዎች ይነሳሉ። ሁሉም (270ሺ) ኑየር ስደተኞች የሰፈሩት በአኝዋክ ወረዳዎች ላይ ብቻ መሆኑም እንደዚው።

ሚያዝያ 16/2008 ዓ.ም
አማን ሁኑ

Leave a Reply