* “የህዝብ ድምፅ የማያከብር ድርጅት ኣያሸንፍም ! (ድምፂ ህዝቢ ዘይኽብር ውድብ ኣይዕወትን።)
ሰበር ዜና
።።።።።።
በትግራይ ማእከላዊ ዞን የ ሰብዓ እምባ ስነይቲ ወረዳ ነበር ህዝብ “የወረዳ ኣስተዳደርነት ይመለስልን” የሚል ጥያቄ ለ20 ዓመት ጠይቆ ምላሽ ባለ ማግኘቱ ዛሬ ሚያዝያ 16 / 08 / 08 ዓ/ም የተቃውሞ ሰልፍ ኣካህደዋል።
የእምባ ስነይቲ ህዝብ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ከነበሩ መፎክሮች
* “የህዝብ ድምፅ የማያከብር ድርጅት ኣያሸንፍም ! (ድምፂ ህዝቢ ዘይኽብር ውድብ ኣይዕወትን።)
*”የወረዳ ኣስተዳደራችን ይመለስልን የሚል የህዝብ ጥያቄ የማይመልስ ድርጅትና መንግስት ከወረዳ እስከ ፌደራልውክልናችን ኣንስተናል !” ( ወረዳና ይመለሰልና ዝብል ሕቶ ህዝቢ ዘይምልስ ውድብን መንግስትን ካብ ወረዳ ክሳብ ፌደራል ውክልናና ነልዕል ኣለና።)
* “የህዝብ ድምፅ ይከበር !” (ናይ ህዝቢ ድምፂ ይከበር።)
ወዘተ የሚሉ መፈክሮች በመያዝ በየወረዳው ማእከል በሆነችው ነበለት ከተማ ሰለማዊ ሰልፍ ኣካሂደዋል።
የክልሉ ኣመራሮች ከዓመታት በፊት ጥያቄ ኣነሱ የተባሉ ከ100 በላይ ሰዎች ከሁለት ዓመት እስከ ኣራት ዓመት የእስር ቅጣት ጨርሰው መውጣታቸው ይታወቃል።
የማእከላዊ ዞን ሃላፊዎች ለ70 እምባ ስነይቲ ህዝብ “የደርግ ናፋቂዎች” የሚል ቅጥያ ሰጥተውታል።
በ09 / 08 /09 ዓም ከሰለማዊ ሰልፍ ከማካሄዳቹ በፊት እናነጋግራቹ ብለው ከክልል የሄዱት ኣመራሮች ከ225 በላይ ህዝብ ኣግተው መዋላቸው ይታወቃል።
በዚህ መሰረት ህዝቡ ከወረዳ እስከ ፌደራል መንግስት የነበራቸው ውክልና በይፋ ኣንስተናል ብለው በሰለማዊ ሰልፋቸው ገልፀዋል።
ተመሳሳይ የወረዳና የዞንነት ጥያቄ ከበርካታ የትግራይ ኣከባቢዎች ሲነሳ መቆየቱ ይታወቃል።
* የበሰበሰ ድርጅት የህዝብ ድምፅ ኣያከብርም !
#Tigray_Ethiopia_Prorest
ነፃነታችን በእጃችን ነው።
የህወሓት ዛቻና ፕሮፖጋንዳ
=============
ህወሓት በእምባስነይቲ ህዝብ ላይ ዛቻዋና የማንበርከክ ፕሮፖጋንዳ እያሰራጨች ነው።
ዓፈናው በመጣስ ከ30 ሺ የሚበልጥ ህዝብ በሰለማዊ ሰልፉ ተሳታፊ ሆኖዋል።
ዛሬ እሁድ 16 / 08 / 08 ዓ/ም የትግራይ 70 እምባስነይቲ ወረዳ ነበር ዋና ከተማ ነበለት የተካሄደው የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ከፍተኛ የመንግስት የዓፈና ጥረት ሰብሮ የተካሄደ ነው።
የህወሓት መሪዎች ሰልፉ ለመከልከልና ጥያቄው ለማፈን የተለያዩ ዛቻዎች እያሰራጩ ይገኛሉ።
* በኣራት ኣቅጣጫ በተለይ ከነበለት ራቅ ያሉ ቀበሌዎች የሚመጡ መንገድ መዝጋትና እንዳይሳተፉ መንገድ የመዝጋት ጥረት ኣድርጎ ነበር።
* በየቀበሌው እየዞሩ ሰልፉ የጠላታችን ዓረና እጅ ኣለበት።
* ከኣዲስ ኣበባ ጀምሮ እስከ ቀበሌዎች የተዘረጋ የዓመፅ እንቅስቃሴ የተደረገበት መስመር ኣውቀነው ስላለን እያንዳንዱ ቅጣቱ እንሰጠዋለን።
* ድርጊቱ የጠላት በርካታ ብር የወጣበት ስለሆነ በቅርብ ቀን እናጋልጡዋለን።
* እያንዳንዲ በዓመፁ እንቅስቃሴ የተሳተፈ ሰው ሁሉ በቅርብ ግዜ ኣይቀጡ ቅጣት ይቀጣል።
* በየቀበሌው ያሉ የሰልፉ መሪዎችና ኣስተባባሪዎች ተለቅመው ይቀጣሉ።
* ህገ ወጥ ሰልፉና ዓመፁ ለህዝባችን የማይመለከት ጥያቄ ሲሆን ሰላማችን ለማደፍረስ ጠላቶች ያቀነባበሩት ሴራ ነው። ወዘተ የሚሉ ክሶችና ዛቻዎች በካድሬዎቻቸው ኣማካኝነት ወደ ህዝቡ እያሰራጩ ይገኛሉ።
የህወሓት መሪዎች የእምባስነይቲ ወረዳ ህዝብ ህገ መንግስታዊ መብቱ በመጠቀሙ ከፍተኛ የሽንፈት መንፈስ ተጠናውቶባቸው ይገኛል።
በ2002 ዓ/ም ሃገራቀፍ ምርጫ ዓረና_መድረክ ወክሎ ለፌደራል ምክርቤት ተወዳዳሪ የነበረውና በህወሓት ቅጥረኞች የተገደለው ጀግናው ኣረጋዊ ገብረዮውሃንስ የትውልድ ኣገር ነው።
በኣከባቢው የነበረው የህዝብ ጥያቄ መመለስ ኣለበት የሚል ኣቋም ይዞ ህዝቡ ከጫፍ እስከጫፍ ያንቀሳቀሰው ሲሆን በእንቅስቃሴ ደንግጠው በግፍ ገድለውታል።
በኣረጋዊ ግድያ ክፉኛ ያዘነው ህዝብ ድምፅ ሳይሰጥ ቀርተዋል። በዚህ ምክንያት ህዝቡ ዓረና የሚል ቅጥያ ሰጥተውት ቆይተዋል።
በዛሬው ሰለማዊ ሰልፉ ” የወረዳ ኣስተዳደራችን ይመለስልን የሚል የህዝብ ጥያቄ የማይመልስ ድርጅትና መንግስት ከወረዳ እስከ ፌደራል ያለው ውክልናችን በይፋ ኣንስተናል ” ሲል ኣውጀዋል።
የህወሓት መሪዎች ከዚ በፊት በ1996 በተምቤን የተካሄደ ሰለማዊ የተቃውሞ ሰልፍ እጅ ነበራቸው ያሏቸው ሰዎች ከፍተኛ ግፍ እንደፈፀሙባቸው ይታወሳው።
ህዝቢ ይስዕር !
ነፃነታችን በእጃችን ነው።