ዜና | 27.04.2016 | 16:37

አዲስ አበባ-የቀድሞዉ የጋምቤላ ርዕሠ መስተዳድር ተፈረደባቸዉ

ሕዝብን በማጋጨት፤የአሸባሪ ቡድን አባል በመሆንና መግለጫ በመስጠት የተከሰሱት የቀድሞዉ የጋምቤላ ርዕሠ-መስተዳድር አቶ ኦኬሎ ኦኳይ እና ስድስት ተባባሪዎቻቸዉ ከሰባት እስከ ዘጠኝ ዓመት የሚደርስ እስራት ተበየነባቸዉ።አቶ ኦኬሎ ኦኳይ በሥልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ከሌሎችቹ  ጋር በመሆን በ1996 በአኝዋክና በኑዌር ጎሳ አባላት መካከል የተነሳዉን ግጭት አባብሰዋል፤ ግጭቱን የሚያባብስ መግለጫ ለዉጪ መገናኛ ዘዴዎች ሰጥተዋል። ከሐገር ከወጡ በኋላም የጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ጋሕነን) የተባለ አሸባሪ ቡድን ባለሥልጣን በመሆን ሰርተዋል የሚል ክስ ተመስርቶባቸዉ ሲሟገቱ ነበር።ዛሬ አዲስ አበባ ያስቻለዉ የፌደራል  ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ ኦኬሎንና ሁለተኛዉን ተከሳሽ አቶ ዴቪድ ኡጁሉን እያንዳዳቸዉ በዘጠኝ ዓመት እስራት እንዲቀጡ ወስኗል።ፍርድ ቤቱ የተቀሩት አምስት ተከሳሾች እያንዳዳቸዉ በሰባት ዓመት እስራት እንዲቀጡ ፈርዷል።በ1996ቱ የጋምቤላ ግጭት ከአራት መቶ በላይ ሰዎች ተገድለዋል።ኦኬሎ ከግጭቱ በኋላ ኖርዌ በስደት ይኖሩ ነበር።የተያዙት ግን ደቡብ ሱዳን ዉስጥ ነዉ። የአቶ ዖኬሎን አጠቃላይ መረጃውን ይህን ይጫኑ“Okello-Okuay

Leave a Reply