በመተከል ዞን ኦሜድላ ሰርገው የገቡ የሱዳን ወራሪ ወታደሮች 70 ኢትዮጵያውያን አፍነው ወሰዱ:: ባለፉት ሁለት ሳምንታት በምእራብ ኢትዮጵያ በቤንሻንጉል ጉምዝ የኢትዮ ሱዳን ድንበር አከባቢ አድፍጠው የነበሩ የሱዳን ወራሪ ወታደሮች ካለፈው አርብ ለሊት ጀምሮ ወደ መተከል ዞን ጎባ ኦሜድላ ድረስ ዘልቀው በመግባት በኢትዮጵያውያን ላይ ወረራ መፈጸማቸውን እና እስከ ትላንት ሰኞ ምሽት ድረስ ጥቃቱም መቀጠሉን የአከባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል:: በአከባቢው የሚገኘው የምእራብ እዝ ሰራዊት ከሕዝቡና አስተዳደሩ ሪፖርት ቢደረግለትን በቦታው ሳይደርስ ቀርቷል::

በኦሜድላ ዘልቀው የገቡት የሱዳን ወራሪ ወታደሮች የገበሬዎችን የእርሻ ምርቶች እና ቦታዎች በማቃጠል ቤቶቻቸውን በማፍረስ የገበሬውን ንብረቶች በመዝረፍ ቁጥራቸው ወደ ሰባ የሚጠጋ ኢትዮጵያውያንን አፍነው የወሰዱ ሲሆን እስካሁን የሞተ እና ያልሞተ ሰው ለመለየት ሕዝቡ ሽብር እና ሽሽት ላይ ስለሆነ ለማረጋገጥ አልተቻለም::

ኦሜድላ ጀግኖች አርበኞቻችን ጣሊያንን ካባረሩ በኋላ የቀድሞ ንጉስ የነበሩት ሃይለስላሴ ከነበሩበት እንግሊዝ ተነስተው በሱዳን በኩል በመግባት ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያን ባንድራ የሰቀሉበት አከባቢ ሲሆን የሱዳን ወራሪዎች አከባቢውን በመቆጣጠር ዘረፋ ማካሄዳቸው እና ኢትዮጵያውያንን ማፈናቸው በአከባቢው ከፍተኛ ስጋት ስለፈጠረ ሕዝቡ እየሸሸ መሆኑ ታውቋል::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

 

 

Leave a Reply