ሞትን የሚያስንቅ ክፉ ስርዓት

ወጣቱ ትውልድ ህወሓት የሚመራት ኢትዮጵያ ተጠይፎ የሞት መንገድ እንዲመርጥ የኑሮ ሁኔታው እያስገደደው ይገኛል።
የማይካድራ ወጣቶች ከጎሬበታቸውና ጓደኛቸው የሃዘን ዳስ ተነስተው ወደ የሞት መኣዱ ሰሃራ በረኻ መጓዙ ቀጥሎበታል። ትናንትናና ዛሬ ወጣቶች ሱዳን መግባታቸው ታውቀዋል።
በማይካድራ የመሰለ መላኩና ሰለሞን የተባሉ ሁለት ወጣቶች በሰሃራ በረሃ “በበውሃ ጥም ምክንያት” መሞታቸው ተከትሎ ሃዘን ተቀምጠው የነበሩ ጓደኞቻቸው ከሃዘኑ ተነስተው ወደ የሞት ማእከሉ ሰሃራ የሄዱ እንዳሉ ታውቀዋል።

የሑመራ ወጣቶች ከህወሓት መንግስት ምንም ዓይነት ትስስር ይሁን የጥቅም ግንኙነት እንደሌላቸው እየገለፁ ነበር።
በሑመራ የተካሄደ የወጣቶች ስብሰባ ተገኝተው ሃሳባቸው ሲገልፁ “እኛ ከህወሓት መንግስት ያገኘነው ጥቅም ወይም ትስስር የቀበሌ መታወቅያ ብቻ ናት። እሷም ደጅ ጠንተን ወይም በእጃችን ሂደን የምናገኛት ናት” ሲሉ በተስፋ መቁረጥ መንፈስ ገልፀዋል።
የህወሓት መንግስት ለወጣቱ ትውልድ ያለው ትርጉም ሞትን ረግጠህ ወይም ረግጦህ፤ ሞትን ንቀህ ወይም ንቆህ፣ ሞትን ኣሸንፈኸው ወይም ኣሸንፎህም ቢሆን መገላገሉ ብቻ የምያስመኝ ከሁሉም ችግሮች የከፈ ነገር መሆኑ የሚመሰክር ነው።
እንደሱ ባይሆን የማይካድራ ወጣቶች የጓደኞቻቸው ሞት የሚያውጅ የሃዘን ዳስ ሳይፈርስ በነሱ መንገድ ባልተጓዙ ነበር፣ ራሳቸው ከሰሃራ በረሃ ሙቀት፣ ተባዮች፣ ከኩላሊት ነጋዴዎች፣ ከዓሳ እራትነት ፊትለፊት ባልገጠሙ ነበር።
ህወሓት በትግራይ ፈጥሮት ያለው የኑሮ ሁኔታ ከሞትም የባሰ ነው። ለዚህም ነው ክፉውን ሞት ንቀው እጅግ በጣም ክፉውን ህወሓት ትተው እየሸሹ ያሉት።
* ወጣቶች ሆይ ወደ ልባቹ ተመለሱ ። ወላጆቻቹ መስዋእት ሆነው የገነቡት መንግስት ጠልታቹ የሞት ሲሳይ ከምትሆኒ እንደ ወላጆቻቺ ታግላቹ ኣስወግዱትና ትውልዳቹን ከእልቂት ኣትርፉ።
በምስሉ የምትመለከቱት ፎቶ ትናንት መርዶውን የተነገረው የሟች ወጣት ሰለሞን ምስልና በማይካድራ ሃዘን የተቀመጡ ወላጆች ምስል ነው።
ፈጣሪ የወጣቶችን ነፍስ በገነት ያኑርልን።
ኣሜን።

Amdom Gebreslasie

Leave a Reply