Written by
በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ትግሉ መለሰ እንደገለፁልን፤ በዩኒቨርሲቲው፤ ካለፈው እሮብ ጀምሮ የተቀሰቀሰው ረብሻ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን ጠቁመው የረብሻው መነሻ ምክንያት ግን እስካሁን አለመታወቁን ገልፀዋል፡፡ ተማሪዎቹ ቀደም ሲል ከአዲስ አበባ በኦሮሚያ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ ያነሱትን ጥያቄ ተከትሎ ለተቀሰቀሰው ረብሻ ጥያቄያቸው በመንግስት ምላሽ በማግኘቱ ተቋርጦ የነበረ ሲሆን አሁን በድጋሚ ረብሻ ለመቀስቀስ የሚያስችል አንዳችም ምክንያት አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በተማሪዎች ላይ ምንም አይነት የኃይል እርምጃ አለመውሰዱንም አቶ ትግሉ ገልፀዋል፡፡
በቦንብ ፍንዳታው ሳቢያ በተማሪዎቹ ላይ ደረሰ ስለተባለው ጉዳት ጠይቀናቸው፤ “ይኼ ዩኒቨርሲቲውን የሚመለከት አይደለም፤ የፀጥታ ኃይሎችን ጠይቁ፡፡ በቦንብ ፍንጣሪው ግን አደጋ የደረሰው በአንድ ተማሪ ላይ ብቻ ነው እሱም የከፋ ጉዳት አይደለም” ሲሉ ምላሽ ሰጥተውናል፡፡ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ከመምህራንና ከተማሪዎች ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት እያደረጉ መሆኑን የጠቆሙት የፅ/ቤት ኃላፊው፤ ረብሻው የከፋ ችግርና ጉዳት ሳያስከትል እንዲቆም ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ መሆኑን ገልፀው ይህም ውጤት እያስገኘ ነው ብለዋል፡፡
አዲስ አድማስ