May 27, 2016

ይድረስ ለመላው የአማራ ህዝብ ! የህወሃትን ወረራ በፋሽስት ጣሊያን ሚዛን መዝነው !

ፋሽቱና ወራሪው የጣሊያን መንግስት በ1888 ዓ.ም እና በ1928 ዓ.ም እየተመላለሰ የቋመጠላትን ወድ ሃገራችንን እጅ ሊያደርግ ባህር ተሻግሮ ወደ ግዛታችን ሲመጣ ከመደበኛ ጦሩ በተጨማሪ ለወረራ ያሰለፋቸውን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወዶ ዘማች ወጣቶች
“ጠይሟና ውቧ የአቢሲኒያ ልጃገረድ ከማይጠገበው የለምለሚቱ ኢትዮጵያ ፀሃያማና ነፋሻ አየር ጋር እጆቿን ዘርግታ በናፍቆት እየጠበቀችህ ነው!” የሚል መዝሙር እያዘመረ ነበር።

በእነዚያ ፋሽስት መሪዎቹ የእርጎ ባህር ተታሎ በጉጉት ወደ ቅድስት ሃገር ኢትዮጵያ የተመመው የጣሊያን ወጣት ግን ወደ ለምለሚቱ የኢትዮጵያ ግዛት በወረራ ሲገባ ያስተናገደው፤ በነፋሻማው የኢትዮጵያ አየር ፋንታ እንደ እሳት የሚፋጅና መተንፈሻ የሚያሳጣው የኢትዮጵያ ልጆች የአልደፈርም ባይነት ቁጣ፣ በኢትዮጵያዊት ቆንጆ ኮረዳ እቅፍ ፋንታ በአንገቱ ላይ የጀግኖች አባቶቻችንን የጎራዴ ስለት ነበር።

እነሆ ይህ የአባቶቻችን ታሪካዊ ድልና የፍሽስቱና የወራሪው የጣሊያን ሽንፈት በዘመኑ በአውሮፓውያን የቅኝ ግዛት ወረራ ስር ወድቀው ለነበሩ ጥቁር ህዝቦች በሙሉ የነጻነትና የአሸናፊነት ተስፋን ሲፈነጥቅ ለተስፋፊና እብሪተኛ ወራሪዎች ደግሞ ዘመን የማይሽረው የውርደትን ማቅ አውርሷቸው አልፏል።

እነሆ በእኛ ዘመንም ከቀደመው የአትንኩኝ ባይነት ታሪካችንና “ከዕርስቴ በፊት አንገቴን ለሰይፍ” ከሚለው ማንነታችን መማር የተሳነውና በተስፋፊነትና በወረራ እብሪት ከፋሽስቱ ጣሊያን የተጣባው የትግራይ ነጻ አውጭ ቡድን ልክ እንደ ጌቶቹ የጣሊያን ወራሪ ሃይል “አማራ”ን ማጥፋትና ከአማራ ህዝብና ሃገር በሚዘረፈው ሃብትና መሬት “ታላቂቷንና የበለጸገች ትግራይ”ን አወርስሃለሁ እያለ የትግራይን ህዝብ ቀስቅሶ “አማራ ገዳይን” እያዘመር በመላው የአማራ ህዝብ ላይ በተለይም በጎንደር በወሎ ህዝብ ላይ ይልቁንም በወልቃይት በጠገዴና በጠለምት ማህበረሰብ ላይ የፈጸመው ወረራና ፋሽስታዊ ግፍ እነሆ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ ተሸጋግሯል።

የአማራ ህዝብ ሆይ!

የዛሬው ህወሃትና የቀደመው የጣሊያን ወራሪ ሃይል ለአማራ ህዝብ አንድም ሁለትም ናቸው!

ሁለቱም ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ድንበርህን በእብሪትና በማን አለብኝነት ጥሰው በወረራ ግዛትህ ሲይዙ፦ አንተን አጥፍተው

1ኛ. ከህይወትህ አብልጠህ የምትሳሳላቸውን ሚስትህንና ልጃገረድ ልጆችህን እንደ እቃ ለመቀራመት ፣

2ኛ. በጀግኖች አባቶችህ አፅም የከበረውን ለም እና ታሪካዊ ዕርስትህ ለመውረስ፣

3ኛ. የሃይማኖት መሪዎችህን፣ ሊቃውንቱንና አባቶችህን፣ ከፓትሪያርክ እስከ ዲያቆን ለማሰር፣ ለማሰደድና፣ ለመግደል፣

4ኛ. ታሪካዊና ቅዱሳን ገዳማቱን ለማፍለስ የማንነትህንና የታሪክህ መሰረት ለማጥፋት፣

5ኛ. አባቶችህ አይሆኑ ሆነው ባቀኗትና በክቡር ህይወታቸው መስዋዕትነትና ታላቅ ተጋድሎ አንድነቷንና ዳር ድንበሯን አስከብረው ባቆዩልህ ታላቋና ገናናዋ ኢትዮጵያ ሃገርህ ላይ ባይተዋርና መፃተኛ፣ የምትሳደድና ተሸማቃቂ ሆነህ እንድትኖር መታተራቸው፣

6ኛ. ይልቁንም ጣሊያን የጀመረውንና በአባቶቻችን ታላቅ ተጋድሎ የከሸፈውን ኢትዮጵያውያንን በዘር ከፋፍሎ እርስ በእርስ የማባላቱንና ሃገርን የማፍረስ እኩይ ሴራ ዛሬ ህወሃት እውን ሊያደርግ 25 አመት ሙሉ መዋተቱ አንድ ሲያደርጋቸው፤

የሚለያቸውና ሁለት የሚያደርጋቸው ደግሞ ፍሽስት ጣሊያን ሃገሩ አውሮጳ፣ ቋንቋው ጣሊያንኛ፣ ቆዳው ነጭ መሆኑና የትግራይ ነፃ አውጭ ቡድን ሃገሩ ኢትዮጵያ፣ ቋንቋው ትግርኛ፣ ቆዳው ጥቁር መሆኑ ብቻ ነው።

አማራ ሆይ!

እንግዲህ ወራሪውና ተስፋፊው የትግራይ ነፃ አውጭ ቡድንና ፋሽስቱ ጣሊያን በሃሳብም ሆነ በምግባር አንድ ናቸውና ትላንት አባቶችህ ጣሊያንን በመዘኑበት ሚዛን አንተም ዛሬ ህወሃትን በዚያው መዝነው!

ይህን ታሪካዊ ጥሪ በምናቀርብልህ ሰአት አይበገሬው የወልቃይት ወገንህ ለአለፉት 36 ዓመታት ተስፋፊውንና ወራሪውን የህወሃት አስተዳደር በመቃወም ሲያደርግ የቆየውን ፍትሃዊ ትግል ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር እራሱ በመረጣቸው ሽማግሌዎች እራሱን ወደ ማስተዳደር ተሸጋግሯል። ይህ ፍትሃዊ እርምጃ የህዝባችን ትግል የደረሰበትን ከፍተኛ የእድገት ደረጃ የሚያመላክትና በምንያህል ታላቅ ወኔና ፍፁም ቁርጠኝነት ዘሩን ከጥፋት ለማዳን በአንድነት እንደተነሳ ያረጋገጠበት በመሆኑ የአባቶቹ ልጅነቱን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል። እኛም ወገኖቹ በዚህ ታሪክ ሲዘክረውና ለልጅ ልጅ ሲያወርሰው በሚኖረው ተጋድሎው በእጅጉ ኮርተናል።

ስለሆነም ጀግኖች አባቶቻችን ፋሽስቱንና ወራሪውን ጣሊያን ሰራዊት እንዴት እንደ ታገሉትና ሃገርና ትውልድን ከውርደትና ከጥፋት እንዴት እንደታደጉና አኩሪ ታሪካቸውን በወርቅ ቀለም እንዴት እንደፃፉ ታውቃለህና ዛሬ በእኛው ዘመን በመልክ እኛን፣ በሃሳብና በምግባር የቀደመው ጣሊያንን መስሎና አክሎ ሃገርና ትውልድን ሊያጠፋ፣ ታሪክህንና ማንነትህን ሊያጎድፍ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ድንበርህን ተሻግሮ የመጣውን ተስፋፊውን፣ ወራሪውንና፣ ፋሽስቱን የትግራይ ነፃ አውጭ ቡድን ታሪካዊና ለትውልድ የሚሻገር ትምህርት ለመስጠት እየታገለ ከሚገኘው የወልቃይት የጠገዴና የጠለምት ወገንህ ጎን በመሰልፍ ታሪካዊና ትውልዳዊ ድርሻህን ትወጣ ዘንድ ወንድማዊ ጥሪ አቅርበንልሃል!

ጎንደር ሆይ !

ታላቁ መጽሐፍ “በጎች እረኛቸውን ያውቁታል፣ በፊታቸውም ይሄዳል እነርሱም ይከተሉታል” እንዲል፤ አንተም መሪህንና አለቃህን ታውቃለህና በመሪ በመሪህ እየሆንክ ክተት!

– የፋሽስቱና የባንዳው ህወሃት ወራሪና ተስፋፊ ሃይል ዕርስትህን ለቆ እስኪወጣ ድረስ ባገኝህበት ሁሉ ተፋለመው!
– በመካከልህ ለጠላት ያደረ ሹልኪት ባንዳ እንዳይኖር ውስጥህን ፈጥነህ አፅዳ!
– ለሃገርህ፣ ለሚስትህ፣ ለልጅህ፣ለራስህና፣ ለመጭው ትውልድ ክብርና ህልውና ስትል ዛሬውኑ ተነስ !
– ወልቃይት ትጣራለችና ዛሬ ነገ ሳትል ፈጥነህ ድረስ!
– አደራ ታሪክህን እንዳታበላሽ ሆነህ ቆርጠህ ተነስ!

ድል ለአማራው ህዝብ!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
ልሳነ ግፉዓን

ግንቦት 18/ 2008 ዓ.ም

Leave a Reply