ጌታቸው ረዳ

ኢትዮ- ሰማይ አዘጋጅ

(Editor- Ethio Semay)

ከጥቂት ቃናት በፊት ኦ! ሲሳይ አገና!ኦ! በሚል ርዕስ በሰብአዊ መብት መጋፋት ወንጀል ከሚጠየቁት አንዱ የሆነ የኢሳያስ ሹመኛ የማነ ገብረአብ ኢሳት ጋር ከሲሳይ አገና ስላደረገለት ቃለ መጠይቅ የጻፍኩትን ትችት እንዳስነበብኩዋችሁ ይታወሳል። በወቅቱ የኤርትራን የውሸት ነፃነት ትግል የመሩ መሪዎች ማንነትና መነሻ ምክንያታቸው እዘረዝራለሁ ብየ ነበር። ሆኖም በእዛው አርዕስት እመለሳለሁ ያልኩት በዚህ አስደንጋጭ በሆነ የቪዲዮ ማስረጃ፤ ኤርትራዊያን ከ350 እስርቤቶች በላይ ታጉረው እየተገረፉና እየተሰቃዩ የሕሊና መቃወስ እንዴት እየደረሰባቸው እንዳለ በቀጥታ ከእስር ቡቶች በምስጢር የተቀዳውን ስዕለ ድምፅ/ቪዲዮ እንድታዩት አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘሁት ይህንን አቅርቤላችኋለሁ።

በነገራችን ላይ ጣሊያኖች መጀመሪያ ወደ ኤርትራ ሲገቡ ‘ሌጋው ሽቦ’ እያሉ ከረኖች በአማርኛ ሲጨፍሩ እንድታደምጡ የለጠፍኩትን ቪዲዮ እንደወደዳችሁት ተስፋ አለኝ። አመርኛ፤ ሃይለስላሴ አመጣብን የሚሉት ውሸት የሚንድ፤ የጥንት ቋንቋቸውም መኖሩ ማስረጃ ነው።

ወደ ጉዳያችን እንግባ። ጉንበት 7 የተባለው እጅግ አሳፋሪ የሆነ የኢሳያስ አፈወርቂ መልዕክተኛ ድርጅት፤ የኢሳያስ አፈወርቂ ዕድሜ ያርዝምልን ብላችሁ ኢትዮጵያዊያን ለኢሳያስ ለሻዕቢያ የፌርማ ድጋፍ አሰባስቡ ብሎ ኤርትራ ውስጥ ያሉ የሰው ልጆች ሁሉ ስቃይ እንዲራዘም የባንዳ መልዕክታቸው ለኢትዮጵያዊያን ዜጎች በዩ ቱብ እና በዘሐበሻ እና በመሳሰሉ የግንቦት 7 ሚዲያ ዘርፎች ማስተላለፋቸው ይታወሳል፡ ይህንን የኢሳያስ ማንነትና የኤርትራ ነፃነት ያስከተለው መዘዝ እንድታዩት ለእነ ንአመን ዘለቀ እና ሲሳይ አገና ፤ ካሳ ከበደ፤ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ፤ብርሃኑ ነጋ፤….(ሁሉም የግንቦት 7 እና የኢሳያስ አዳማቂዎች) ተከታታይ መልስ ይኼውና ቪዲዮውን በጥሞና እምባችሁን እየተቆጣጠራችሁ (ደግ ይሁኑ፤ የኢትዮጵያ/የአማራ ሕዝብ ግፍና እርግማን ነው፤ እራሰቸው ያመጡት መዘዝ ነው ብላችሁ፤ ደስታ የሚሰማችሁ ካላችሁም ፤በእርጋታ ስሜታችሁን እየተቆጣጠራችሁ) በጥሞና ተመልከቱት። …… (Read more pdf)

https://www.youtube.com/watch?v=mo1UpyxQ9yo

Leave a Reply